አጋጣሚዎች
እስልምና ለሰው ልጆች መልካም የሆነን ነገር ሁሉ አቅፎ የያዘ ሃይማኖት ነው። የሰውን ልጅ ባለበት ቦታ እና ጊዜ ሁሉ የሚጠቅም አጠቃላይ እና ሁሉን አቀፍ መልዕክት ነው። ይህ ክፍል አንድ ሙስሊም ሰው በተለያዩ ሁኔታዎች እና አጋጣሚዎች የሚፈልጋቸውን ጉዳዮች የሚዳስሱ የተመረጡ ርዕሶችን አካቶ ይዟል።
ንኡስ ርእሶች
የክረምት ስንቆች
እስልምና ሁሉን አቀፍ ሃይማኖት ነው። ሁሉም ህይወት ከፈጣሪው ጋር የተቆራኘች ፣ አላማው እፁብ ድንቅ ፣ የቃላት ትርጉሙ ብሩህ ሲሆን ህይወትን በዚሁ መንገድ ይቀርፃል። በዚህም ምክኒያት አማኝን ሰው ወደ እዚያ የሚመራው የአምልኮ ተግባራት አለው።
የክረምት ወቅት ጋር በተያያዘ ንፅህና ፣ ሶላት ፣ አለባበስ እና ዝናብን የተመለከቱ ከብዙ ምዕራፎች ጋር የተቆራኙ የሸሪአ ብያኔዎች ያሉበት ወቅት ነው። የአሏህ ፈቃድ ከሆነ በዚህ ክፍል ውስጥ አንዳንድ የክረምት ስንቆች እናያለን።
የጉዞ ህጎች
እስልምና ከሁሉም የሰው ልጆች ሁኔታዎች ማለት ከጉዞ ፣ ከእንቅስቃሴው ፣ ከእርፍት ፣ ከሳቅ ከጨዋታ ጋር የተሳሰረ በመሆኑ የህይወት ሃይማኖት ያደርገዋል። ጉዞዎች የዚህ ማህበራዊ ህይወት አካሎች ናቸው። ታዲያ እነዚህ ጉዞዎች ሃያሉ አሏህን እንድናስታውስ ፣ ያዘዘንን እንድንሰራ ወይም የከለከለንን እንድንርቅ የሚፈልጋቸው ነገሮች ያሉበት ነው። እናደርጋለንም። በአሏህ ፈቃድ በዚህ ክፍል ውስጥ የተወሰኑትን የጉዞ ስንቆች እንዳስሳለን።
ወረርሽ እና በሽታ
ወረርሽኝ ሙስሊም የሆነን ሰውም ሆነ ሙስሊም ያልሆነን ሰው የሚያጋጥም የአሏህ ውሳኔ ነው። ነገርግን ሙስሊም ሰው የደረሰበትን ጉዳት የሚሳልፍበት መንገድ ከሌሎች ሰዎች የተለየ ያደርገዋል። ምክኒያቱም በሽታውን ሃያሉ አሏህ እንዳዘዘው በትዕግስት ያሳልፈዋልና። በሽታው ከመከሰቱ በፊት ተገቢ እና የተፈቀዱ ሰበቦችን ተጠቅሞ ለመከላከል ይሞክራል ፣ በሽታው ከያዘው ደግሞ ታግሶ ይታከማል።