ወረርሽ እና በሽታ
ወረርሽኝ ሙስሊም የሆነን ሰውም ሆነ ሙስሊም ያልሆነን ሰው የሚያጋጥም የአሏህ ውሳኔ ነው። ነገርግን ሙስሊም ሰው የደረሰበትን ጉዳት የሚሳልፍበት መንገድ ከሌሎች ሰዎች የተለየ ያደርገዋል። ምክኒያቱም በሽታውን ሃያሉ አሏህ እንዳዘዘው በትዕግስት ያሳልፈዋልና። በሽታው ከመከሰቱ በፊት ተገቢ እና የተፈቀዱ ሰበቦችን ተጠቅሞ ለመከላከል ይሞክራል ፣ በሽታው ከያዘው ደግሞ ታግሶ ይታከማል።