የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት ሙስሊም ሰው ወረርሽኝ ስጋፈጥ
እጣፋንታ (ቀደር) አንዱ የኢማን መሰሶ በመሆኑ የሚከሰተው ነገር ጥሩም ይሁን መጥፎ በእሱ እናምናለን። በሰዎች ላይ የሚደርስ እንደ ወረርሽኝ ፣ በሽታ ፣ ተፈጠሯዊ አደጋ እና መጥፎ እድሎች ወ.ዘ.ተ የሚከሰቱት በአሏህ ፈቃድ እና ውሳኔ ነው። የአሏህን ፍርድ ወይም ውሳኔ መቀበል እንጅ መቆጣት ፣ መበሳጨት ፣ ማማረር ወይም መሸበር አያስፈልግም። ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡ "ከመከራም ማንንም አይነካም በአሏህ ፈቃድ ቢሆን እንጅ። በአሏህም ለሚያምን ሰው ልቡን ይመራለታል። አሏህ ነገሩን ሁሉ አዋቂ ነው።" (ሱረቱ ተጋቡን 14)
ሙስሊም ሰው በሽታ በአሏህ ትዕዛዝ እና ውሳኔ እንጅ በአቅሙ ድንበር አያልፍም ብሎ ያምናል። ነገርግን የጤና እና የመከላከያ ቁሳዊ ሰበቦችን መጠቀም ከበሽታ አምጭ መንስኤዎች እና ወረርሽኝ በተከሰተባቸው ቦታ እንድንርቅ እና ቅድመ መከላከል ከታማሚዎች ጋር በሚኖር መስተጋብር ጥንቃቄ እንድናደርግ ታዘናል። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹ተላላፊ በሽታ የለም ፣ መጥፎ ምልክት የለም ፣ ሐምም የለም ፣ በሰፈር ወር መጥፎ እጣ የለም በአሏህ ፈቃድ ቢሆን እንጅ። አንድ ሰው ከአንበሳ እንደሚሸሸው ሁሉ ከቁምጥናም መሸሽ አለበት አሉ።›› (ቡኻሪ 5707)
የወረርሽኝ በሽታ ከሃያሉ አሏህ የሆነ ለካፊሮች እና ለሙናፊቆች አስቸኳይ ቅጣት ሲሆን ለአማኞች ደግሞ እዝነት ፣ ደረጃቸውን ከፍ የሚያደርጉበት እና ሃጢያቶቻቸውን የሚያብስበት ነው። ስለ ወረርሽኝ አኢሻ(ረ.ዐ) በጠየቀቻቸው ጊዜ ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹አሏህ በሻው ሰው ላይ ያወረደው ቅጣት ነው። አሏህ ወረርሽኝ በሁሉም ላይ የሚያወርድ ሲሆን ለአማኞች የእዝነት ምንጭ አድርጎታል። ሆኖም የአሏህን ምንዳ ፈልጎ ፣ ከአሏህ ውሳኔ ውጭ ምንም ነገር እንደማይሆን አውቆ በትዕግስት በሐገሩ ውስጥ ቆየ ሰው የሰማዕትነት ያህል ምንዳ (ሽልማት) ያገኛል።›› (ቡኻሪ 3474)
በእንደዚህ አይነት ሁኔታዎች ውስጥ ሁሉም ሙስሊም ሰው በአስተዳደር ሃላፊነት ላይ ላሉ ባለስልጣናት ምክር ምላሽ መስጠት አለበት። ከግል ጥቅሙ ይልቅ የህዝቡን ጥቅም በማስቀደም ሃላፊነቱን መወጣት አለበት። መረጋጋትን እና ህይወት ወደ ተለመደው ሁኔታ እንዲመለስ በሚደረገው ጥረት መተባበር አለበት። ሃያሉ አሏህ እንዲህ ይላል፡ "በበጎ ነገር እና አሏህን በመፍራት ተረዳዱ። በሃጢያት እና ወሰን በማለፍ አትረዳዱ።" (ሱረቱል ማኢዳ 2)
ወረርሽኝ በተከሰተ ጊዜ እርም የተደረጉ ነገሮች
አልቧልታ ወሬን ማሰራጨት የተከለከለ ውሸት ሲሆን ጥረርጥር የለውም። በሰዎች መካከል ሽብር ለመፍጠር ምክኒያት ነው። ማስረጃ የሌለው መረጃን ላለማስተላለፍ መጠንቀቅ ጠቃሚ ነው። ሃያሉ አሏህ የሙናፊቆችን ባህሪ በመጥቀስ እንዲህ ይላል፡ "ከፀጥታ ወይም ከፍርሃት አንዳች ወሬ እሱን ያጋንናሉ። ወደ መልዕክተኛው እና ከእነሱ ወደ ትዕዛዙ ባለቤቶች ወደ አዋቂዎች በመለሱት ኖሮ እነዚያ ከእነሱ ነገሩን የሚያውጣጡት ባወቁ ነበር።" (ሱረቱ ኒሳዕ 83)
በተለይ ችግር በተከሰተ ጊዜ ሸቀጦችን በበላይነት መቆጣጠር ፣ ማጭበርበር ፣ ከሚገባው በላይ ዋጋ መጨመር እና የሰዎችን ንብረት መመዝበር እስልምና ይከለክላል። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹በሙስሊሞች ላይ (ዋጋን ጨምሮ) በሃይል ለማስከፈል የሆነን ነገር በበላይነት የተቆጣጠረ ሰው፤ እሱ ሃጢያተኛ ነው።›› (መሰነድ 8617)
በማኝኛውም አይነት ሃሳብ ቢሆን ሆንብሎ ወረርሽኝን ከበሽተኛ ሰው ወደ ጤነኛ ሰው ማዛመት የተከለከለ ተግባር ነው። ከትልልቆቹ ሃጢያቶች የሚቆጠር ክፉ ስራ ነው። እንዲህ ያደረገ ሰው በዚህ አለም ቅጣት ያስፈልገዋል። ቅጣቱ እንደ ድርጊቱ ክብደት እንዲሁም በግለሰቦች እና በማህበረሰቡ ላይ እንዳደረሰው ጉዳት ይወሰናል።
ሆንብሎ ወረርሽኝን ወደ ሌላ ሰው ያስተላለፈ ቅጣቱ
4 በሽታን መስደብ
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ትኩሳትን መስደብ ከልክለዋል። ጃቢር ኢብን አብዱሏህ (ረ.ዐ) እንዳለው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ለኡሙ አሳኢብ እንዲህ ብለዋል፡ ‹‹ትኩሳትን እንዳትሰድቡ፤ የእሳት ምድጃ ብረትን እንደሚያጠራው ሁሉ የአደምን ልጅ ሃጢያት ያስወግዳልና።›› (ሙስሊም 2575)