የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት ከወረርሽኝ ጋር የተያያዙ ህጎች
ክትባት በሽታው ከመከሰቱ በፊት በሽታን ቀድሞ ለመከላከል የሚረዳ በመሆኑ እና በአሏህ ላይ ከመመካት ጋር የማይፃረር በመሆኑ የተፈቀደ ነው። ምክኒያቱም ትክክለኛ በሆነ ሐዲስ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡ ‹‹ሰባት የአጅዋ ተምሮችን ጧት ላይ የበላ ሰው፤ ያን ቀን መረዝም ሆነ ድግምት አይጎዳውም ብለዋል።›› (ቡኻሪ 5445 ፣ ሙስሊም 2047) ይህ መከራ ከመከሰቱ በፊት አስቀድሞ መከላከልን የተመለከተ ነው።
ታማሚ ሰው ከጤነኛ ሰው ጋር እንዳይደባለቅ ሸሪአው ያዛል። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡ ‹‹የታመመ ሰው ወደ ጤነኛ ሰው መቅረብ የለበትም›› ብለዋል። (ቡኻሪ 5771 ፣ ሙስሊም 2221)
ስለዚህ በተላላፊ በሽታ ወደ ተለከፈ ሰው ከመሄድ ይቆጠባል። ነገርግን የበሽታውን ስርጭት መከላከል የሚያስችል ዘዴ በመጠቀም ቤተሰቦቹን እና ያለበትን ሁኔታ መጠየቅ ፣ በቻለው አቅም ለህክምና የሚሆን ገንዘብ መርዳት ይችላል።
ወረርሽኝ ወዳለበት ሐገር መግባት ወይም መውጣት አይፈቀድም። ይህ አብዱረህማን ኢብን አውፍ (ረ.ዐ) ባስተላለፈው የሐዲስ ማስረጃ ይደገፋል። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹በአንድ ቦታ ውስጥ እንደተከሰተ ከሰማችሁ እትቅረቡት። በዚያ አካባቢ እያላችሁ ከተከሰተ ከእሱ ለማምለጥ ብላችሁ አትውጡ።›› (ቡኻሪ 5729 ፣ ሙስሊም 2219) የብዙሃኑ ሊቃውንት ስምምነት በዚህ ላይ የፀና ነው። እንዲዚህ አይነት ወረርሽኝ ወደ ተከሰተበት ሐገር መሄድ ወይም ከበሽታው ለማምለጥ ሲባል ወጥቶ መሄድ አይፈቀድም።
የጀመአ (የህብረት) ሶላት በወንዶች ላይ ግዴታ ነው። ነገርግን አሳማኝ እና በቂ ምክኒያት ካለ የህብረት ስግደቱን ማስቀረት እንደሚቻል ሊቃውንት ይናገራሉ። ይህ አኢሻ (ረ.ዐ) ባስተላለፈችው የሐዲስ ማስረጃ ይደገፋል። ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) በአንድ ወቅት ታመው ከምዕመናን ጋር መስገድ ባልቻሉ ጊዜ እንዲህ አሉ፡ ‹‹ሰዎቹን በሶላትአቡበክር እንዲመራ ንገሩት።›› (ቡኻሪ 664 ፣ ሙስሊም 418) ይህ የሚያመለክተው አንድ ሙስሊም ሰው ታሞ ወይም (መከራ) ችግር ደርሶበት ከሆነ ይቅር እንደሚባልለት ማሳያ ነው። ሆኖም ህብረቱ ወደ መስጊድ ከመሄድ መቅረት እና በራሱ ቤት ውስጥ መስገድ የተፈቀደ ነው።
አንድ ሙስሊም የጀመአ ሶላቱን ለመተው በቂ ሰበብ ኖሮት የፈርድ እና የሱና ሶላቶች ቤቱ ውስጥ ለመስገድ የሆነ ቦታን እንደ መስጅድ መጠቀም የተወደደ ነው። ይህ ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የሆነ መመሪያ ነው። ኢትባን ቢን ማሊክ (ረ.ዐ) ባስተላለፈው ሐዲስ እና ሙስሊም በዘገበው ሐዲስ ውስጥ ለነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እይታው እንደከዳው (እንደደከመ) ፣ ዶፍ እንደወረደ በእሱና በሰዎች መካከል ሸለቆ እንደሆነበት፤ በዚህም ምክኒያት ወደ መስጅድ መሄድ እንደማይችል ነገራቸው። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ ቤቱ መጥተው እንዲጎበኙት እና በውስጧም እንዲሰግዱ ጠቃቸው። የነብዩን(ሰ.ዐ.ወ) የስግደት ቦታ እንደ መስገጃ ቦታ አድርጎ ለመያዝ። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መጡና በእሷም ውስጥ ሁለት ረከአ ሰገዱ።
ልክ እንደዚሁ መይሙና (ረ.ዐ) ቤቷ ውስጥ መስገጃ ቦታ ነበራት። አማር ኢበኑ ያሲርም ቤቱ ውስጥ የመስገጃ ቦታ ነበረው። ይህን ችግር ልንጠቀምበት እና ቤቶቻችን ውስጥ የሆነን ቦታ ለመስገጃነት ማበጀት አለብን።
መስጅድ ውስጥ መስገድ ባልተቻለ ጊዜ የጀመአ (የህብረት) ሶላት መስገድ የሚጀምረው ቤት ውስጥ ነው። የጀመአን ምንዳ በዚህ ማሳካት ይቻላል።............................
ምዕመናን ቤታቸው ውስጥ በህብረት የሚሰግዱ ከሆነ የቤቱ ባለቤት ስግደቱን የመምራት መብት አለው። ሶላቱን የማይመራ ሰው ከሆነ የአሏህን መጽሐፍ ያነበበ ሰው ይመራል። ሁላቸውም እኩል ከሆኑ የሶላትን ህገ ደንብ በደንብ የሚያውቅ ሰው ያሳግዳል። አሁንም እኩል ከሆኑ ከእነሱ መካከል ታላቁ ያሰግዳል።
አንድ ሙስሊም ሰው ቤቱ ውስጥ የሚሰግድ ከሆነ እና የሚከተለው ሰው አንድ ወንድ ከሆነ ተከታዩ በቀኝ ጎኑ በኩል ሆኖ ይሰግዳል። የሚከተሉት ብዙ ከሆኑ ግን ከኢማሙ ኋላ ሆነው ይሰግዳሉ። ተከትላው የምትሰግደው ሴት ከሆነች የምትሰግደው ከኋላው ሁና ነው።
እነዚህ መከራ እና ችግሮች ቤተሰባችነን ሶላት እንዴት አንደሚሰገድ ፣ ቅድመ ሁኔታዎቹ ፣ የንፅህና ደንቦች እና በእሱ ውስጥ ምንምን አስፈላጊ እንደሆነ ለማስተማር ትልቅ እድል ነው። በዚህም ላይ እንመካከራለን።
የጀመአ ሶላት ለሴቶች የተላለፈው ሸሪአዊ ብያኔ በቤቶቻቸው ውስጥ እንዲሰግዱ ነው። ይህ በኡሙ ወረቃ ፣ በአኢሻ እና ኡሙ ሰላማ(ረ.ዐ) ባስተላለፉት ዘገባ መሰረት የተረጋገጠ ነው። ጀመአቸውም ሞገስ ያለው እና ሽልማታቸው ከአሏህ ነው። ኢማማቸው ከረድፉ መሃል ትቆማለች።
በተለይ በወረርሽኝ በሽታ የተለከፈ ሰው በሰዎቹ ስብስብ (በጀመአው) መገኘት የተከለከለ ነው። ምክኒያቱም ይህ በሰዎች ላይ ጉዳት ስለሚያስከትል ነው። ሃያሉ አሏህ እንዲህ ይላል፡ "እነዚያ ምዕመናን እና ምዕመናትን ባልሰሩት ነገር የሚያሰቃዩ ዕብለትን እና ግልፅ ሃጢያትን በእርግጥ ተሸከሙ።" (ሱረቱ አህዛብ 58)
ከተደነገጉ ህግጋቶች መካከል አለመጉዳት እና አፀፋን አለመመለስ ነው። ይህ በሽታ ያለበት ሰው ከጤነኛ ሰዎች ጋር መቀላቀል አይፈቀድለትም። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹የታመመ ሰው ከጤነኛ ሰው ጋር አይቀላቀል።›› (ቡኻሪ 5771 ፣ ሙስሊም 2221)
በሶላት ወቅት አፍን በማክስ መሸፈኑ ለሰጋጁ የተጠላ ነው። ይህን ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከልክለዋልና። ነገርግን በምክኒያት ባስፈለገ ጊዜ ወይም የተላላፊ ወረርሽኝ መስፋፋት በፈራ ጊዜ እንዲህ አይነቱን ማክስ መልበስ ይችላል።
የህብረት ሶላቱን የሚረብሽ ክስተት በሚኖርበት ሁኔታ በጁምአ ቀን ላይ ያሉ ህግጋቶች የተጠበቁ ናቸው። ሆኖም በፈጅር ሶላት ውስጥ ሱረቱ ሰጅዳ እና ሱረቱ ኢንሳን ማንበብ ፣ ዱአ ይበልጥ ምላሽ በሚያገኝበት የአሱር የመጨረሻዋ ሰአት ላይ ዱአ ማድረግ ፣ በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ሰለዋት ማውረድ የተወደደ እና የተደነገገ ደንብ ነው። ሱረቱል ካህፍን ማንበብ እንደመርህ የነዚህ ህገ ደንቦች ህጋዊነት ማሳያ ነው። እናም እነዚህ በሶላቱ ላይ ብቻ የተመሰረቱ አይደሉም።
በእጅ መጨባበጥ ሱና ነው። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹ሁለት ሙስሊሞች ተገናኝተው እጅ ለእጅ የሚጨባበጡ የሉም ከመለያየታቸው በፊት የተማሩ ቢሆን እንጅ።›› (አቡዳውድ 5212) አንድ ሙስሊም ሰው በእጅ በመጨባበጡ በሽታው ይተላለፍብኛል ብሎ ከፈራ በቃል ሰላምታን መለዋወጥ በቂው ነው። በአሏህ ፍቃድ ያሰበው ምንዳ ይፃፍለታል።