የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት ህጋዊ ክትባት
በሽታው እና በወረርሽኙ ሰዎች በሽብር ሲናጡ፤ ሙስሊም ሰው ቁሳዊ ሰበቦችን እያደረገ መከላከያ ይሆነው ዘንድ ሸሪኣዊ ክትባትን ይከተባል።
በመከራ እና በችግር ጊዜ አማኝ ሰው እራሱን ለመጠበቅ የሚያደርገው የመጀመሪያው ፣ በጣም አስፈላጊው እና ትልቁ ነገር ወደ ሃያሉ አሏህ መጠጋት እና ከዚህ ክፉ ነገር እንዲጠብቀው መፈለግ ነው። ዩሱፍ(ዐ.ሰ) በአል-ዚዝ ሚስት በተፈተነ ጊዜ "በአሏህ እጠበቃለሁ አለ።" (ሱረቱ ዩሱፍ 23) መርየም (ዐ.ሰ) ጅብሪል ወደ እሷ በተገለጠ ጊዜ "እኔ ከአንተ በአረህማን እጠበቃለሁ።" (ሱረቱ መርየም 18)
አሏህ መከራውን እንዲያነሳው እና የተጨነቁ ጭንቀታቸው እንዲቀልላቸው ወደ አሏህ ፀሎት ማድረግ እና ወደ እሱ መዋደቅ ያስፈልጋል። ሆኖም ዱአ የሙስሊሞች ምሽግ እና ጥሩ ማሳሪያ ነው። በአሏህ ውሳኔ መከራ በደረሰ ጊዜ ምንም የሚያቆመው የለም፤ ዱአ ቢሆን እንጅ። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹ቀዷን (የአሏህ ውሳኔ) የሚያስቀር ነገር የለም ዱአ ቢሆን እንጅ።›› (ትርሚዚ 2139)
ከእሱ ፈውስ ፈልጉ፤ ለሁሉም አካለዊና የሞራል በሽታዎች መድሃኒት ነውና። "ከቁርአንም ለምዕመናን መድሃኒት እና እዝነት የሆነን እናወርዳለን።" (ሱረቱ ኢስራዕ 82) በኢማን ፣ በታማኝነት እና በእርግጠኝነት የመዳን ሰበቡ ይጨምራል። ሃያሉ አሏህ እንዲህ ይላል፡ "እሱ ለእነዚያ ላመኑት መመሪያ እና መፈወሻ ነው።" (ሱረቱ ፉሲለት 44)
ሙሉ ቁርአን ፈውስ (መድሃኒት) ነው። ነገርግን አንዳንድ ሱራዎች እና አንቀፆች ልዩ ጥቅሞች አላቸው። ለምሳሌ ሱረቱል ፋቲሃ ፣ አል-ሙአዊዛት እና አያተል ኩርሲ ይጠቀሳሉ። ኢብነል ቀይም (ረሂመሁሏህ) እንዲህ አለ፡ ‹‹አንድ ሰው እራሱን በአል-ፋቲሃ ጥሩ አድርጎ ካከመ በመዳኑ ላይ አስደናቂ ተፅዕኖ ይኖረዋል። ከእነሱም በፍጥነት ያገግማል (ይድናል)።››
በተለይ ደግሞ የሱብሂ ሶላትን፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ ‹‹የፈጅር ሶላትን የሰገደ ሰው በአሏህ ጥበቃ ስር ነው።›› (ሙስሊም 657)
ለሙስሊም ሰው ጠቃሚ ከሆኑ ምሽጎች ውስጥ አንዱ ዱአ ነው። የታመሙ እና መከራ የደረሰባቸውን ሰዎች ባየ ጊዜ በሐዲስ እንደተገለፀው ዱአ ያደርጋል። ‹‹መከራ የደረሰበት ሰው ባየ ጊዜ ‹‹ምስጋና ለአሏህ፡ ከደረሰብህ ነገር ላዳነኝ እና ከፈጠራቸው ነገር ሁሉ በላይ ለመረጠኝ›› ያለ ሰው መከራው አይደርስበትም።›› (ትርሚዚ 3432)
ሃያሉ አሏህን ብዙ ማውሳት (ማወደስ) በዚህ አለም ህይወት ብዙ ጥቅሞች እና በመጭው አለም ህይወት ደግሞ ትልቅ ሽልማት አለው። የጧት እና እና የማታ አዝካሮች (ውዳሴዎች) አንድ ሙስሊም ሰው አብዝቶ ሊያደርጋቸው ከሚገቡ በጣም ጠቃሚ ከሆኑ ነገሮች ውስጥ አንዱ ነው። ከጥቅሞቹ መካከል፡ ደረትን ያሰፋል ፣ ልብን ያረጋጋል ፣ ወደ ሃያሉ አሏህ ያቃርባል ፣ በከፍተኛ ስብስብ ውስጥ ሆኖ ያስታውሰዋል።
ከዱአዎች ፣ ከዚክሮች (ውዳሴዎች) እና ህጋዊ ክትባቶች መካከል
ከመተኛትዎ በፊት አያተል ኩርሲን ማንበብ
በሐዲስ ውስጥ አንድ ሰው ለአቡ ኹረይራ (ረ.ዐ) እንዲህ አለው፡ ‹‹ወደ መኝታችሁ በሄዳችሁ ጊዜ አያተል ኩርሲን (2፡255) አንብቡ፤ ከአሏህ የሆነ ጠባቂ ይጠብቃችኋልና። እስከ ጧትም ድረስ ሰይጣን አይቀርባችሁም።›› ይህን አስመልክቶ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹ውሸታም ቢሆንም እውነትን ነግሯችኋል። እሱ እራሱ ሰይጣን ነው።›› (ቡኻሪ 3275)
ከሱረቱ በቀራ የመጨረሻዎቹን ሁለቱን አንቀፆች አንብቡ
አቡ መስኡድ (ረ.ዐ) ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ይዞ እንዳወራው እንዲህ አለ፡ ‹‹ማታ ላይ ከሱረቱል በቀራ የመጨረሻዎቹን ሁለት አንቀፆች ያነበበ ሰው ያ ለእሱ በቂው ነው።›› (ቡኻሪ 5008 ፣ ሙስሊም 808)
ተስቢህ (ማጥራት) እና እስቲግፋር (ንሰሃ) ማብዛት
ባሪያው አሏህን በማጥራት (በተስቢህ) እና በስቲግፋር (መሃርታውን) በመጠየቅ ከበረታ አሏህ ከመከራ እና ከችግር ይጠብቀዋል። ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡ "አሏህም አንተ በመካከላቸው እያለህ የሚጠቅማቸው አይደለም። እነሱ ምህረትን የሚለምኑ ሲሆኑ አሏህ የሚቀጣቸውም አይደለም።" (ሱረቱል አንፈል 33)