የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት የወረርሽኝ ትምህርት በስብከት ውስጥ
ወረርሽኝ ሙስሊም የሆኑ እና ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎችን የሚገጥማቸው የአሏህ ውሳኔ ነው። ነገርግን ሙስሊሞችን የሚገጥማቸው ችግር ከሌሎቹ ጋር አንድ አይነት አይደለም። ምክኒያቱም ጌታው ስላዘዘው ከበሽታው ጋር እየታገለ ይታገሳል ፣ ከመከሰቱ በፊት የተፈቀዱ ሰበቦችን በመጠቀም ይከላከላል ፣ ከደረሰበት ደግሞ ታግሶ ያገግማልና ነው።
በማይክሮስኮፕ ብቻ የሚታይ ደካማ ፍጡር በሆነው የኮሮና ቫይረስ ምክኒያት ወረርሽ ተስፋፍቶ አለምን በሙሉ አምሷል። በነፍሶች ላይ ፍርሃት እና ሽብርን አድርሷል። ይህ የአሏህን ሃያልነት እና የሰው ልጆች የደረሱበት ስልጣኔ ላይ ቢደርሱ ፣ የብዙ ቴክኖሎጅ ባለቤት ቢሆኑም ደካማ ፍጡር የመሆናቸው ትልቅ ማሳያ ነው። ሃያሉ አሏህ በሰማያትም ሆነ በምድር ላይ ሁሉን ማድረግ የሚችል አምላክ ነው።
ቀዷ እና ቀደር (የአሏህ ውሳኔ) እውነት ነው!
በዚህ ፍጥረተ አለም ውስጥ ያለው ክስተት ሁሉ የአሏህ ውሳኔ እና ከመፍጠሩ በፊት በመጽሐፉ ተፅፎ ያለ መሆኑን ሙስሊሞች ያምናሉ። ይህ እምነታቸው በፈሩ እና በተጠራጠሩ ጊዜ እንደገና ያረጋግጣሉ እምነታቸውንም ያጠነክራሉ። የአሏህን ውሳኔ በተከፈተች ልብ ይቀበላሉ።
ግሳፄ እና አሳቢነት
መከራ እና ውጣውረዶች ለሙስሊሞች
እነዚህ መከራዎች በተከሰቱ ጊዜ ከሚደረጉ የአምልኮ ተግባራት ውስጥ ለአሏህ መተናነስ ፣ እጅ መስጠት እና ዱአ አብዝቶ ማድረግ ነው። እርዳታን መፈለግ እና ከችግሩ ፋታ ለማግኘት መለመን የሚገባው ሃያሉ አሏህ ብቻ ነው። ሃያሉ አሏህ እንዲህ ብሏል፡ "ታዲያ ቅጣታችን በመጣባቸው ጊዜ (አሏህን በመገዛት) አይዋደቁም ኖሯል ግን ልቦቻቸው ደረቁ። ይሰሩት የነበሩትንም ነገር ሰይጣን ለእነሱ አሳመረላቸው።" (ሱረቱል አል አንዓም 43) ቅን የሆነ ዱአ የሰማይን በር ይከፍታል ፣ ግርዶውን ይገልጣል ፣ ርቀትን ይሸፍናል ፣ ከአዛኙ አሏህ ጋር ያቃርባል። "ባሮቼ ስለ እኔ በጠየቁህ ጊዜ እኔ ቅርብ ነኝ በላቸው። የለማኝን ፀሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ።" (ሱረቱል በቀራ 186) ወሃብ ኢብን ሙናቢህ እንዲህ አለ፡ ‹‹መከራ የሚደርሰው ዱአን ሊያወጣ ነው።››
ትልቁ እብሪት ከእነዚህ በሽታዎች እና መከራዎች ደህና ነን ብለን ማመናችን እና የምናስበውም ስለመኖር (ስለ ህይወት) ብቻ መሆኑ ነው። መከራ እና ችግር በሃጢያቶቻችን መካከል ያሉ ናቸው። ይህ በብዙ የቁርአን አንቀፅ ተረጋግጧል። ሃያሉ አሏህ እንዲህ ይላል፡ "በእርግጥ ያገኛችሁ መከራ ባገኛችሁ ጊዜ ‹‹ይህ ከየት ነው›› አላችሁ። እሱ ከነፍሶቻችሁ ነው።" (ሱረቱል ኣለ ኢምራን 165) አሏህ እንዲህ አለ፡ "ከመከራም ያገኛችሁ ነገር እጆቻችሁ በሰሩት ሃጢያት ምክኒያት ነው። ከብዙውም ይቅር ይላል።" (ሱረቱ አሹራ 30)
አሏህ ለባሮቹ ቸር ነው
በአሏህ ላይ መመካት መከራ እና ችግርን ለመጋፈጥ ከሚረዱ ትልቅ መንገዶች ውስጥ አንዱ ነው። ሆኖም መከራው ማለፉ የማይቀር መሆኑን እርግጠኛ ሁኑ። በዙሪያችሁ ላሉ ሰዎች ተስፋ ስጡ ፣ ጭንቀት ፣ ፍርሃትን እና ተስፋ ማጣትን አስወግዱ፤ ያለበለዚያ መከራው ይብዳል እንጅ አይቀልምና። "ከችግር ጋር ምቾት አለ። በእርግጥ ከችግር ጋር ምቾት አለ።" (ሱረቱ ኢንሽራህ 5-6)
ህጋዊ እና ሚናው የጎላ ቁሳዊ ሰበቦችን ተጠቅሞ ክፋትን መመከት እና ማባረር አሏህ በዚህ ፍጥረተ አለም ውስጥ ካደረጋቸው ህግጋት አንዱ ነው። መልዕክተኞች እና ደጋግ የአሏህ ባሮች ይህን ተቀብለዋል። ይህ ሙሉ በሙሉ በአሏህ ላይ የመመካት እና ያዘዘውን ነገር የመታዘዝ አንዱ አካል ነው።
በአይን ሊታይ የማይችል ፍጡር የአለምን ህዝብ በተድላ ፣ በደስታ ፣ በደህንነት ፣ መረጋጋት እና መተዳደሪያ ገቢ ረብሻቸዋል። ምዕመናን ተዋቸውና እንደው ጤናማ አዕምሮ ያለው ሰው የተረጋጋና ቤቱ አድርጎ መያዝ ፣ በእሱ ላይ መፋለም እና በፍርስራሹ መወዳደርን ይከጅላሉን?
ያለ ጥርጥር ይህ ቫይረስ አሏህ ባሮቹን የሚያስፈራራበት እና የሚያስጠነቅቅበት ፣ ከራሳቸው ጋር እንዲመክሩ እንዲያስቡበት ፣ የፍርሃትን እስራት እንዲያድሱ ከሚገፋፋቸው የአሏህ ምልክቶች ውስጥ ነው። ሃያሉ አሏህ እንዲህ ይላል፡ "ተአምራቶችንም ለማስፈራራት እንጅ አንልክም።" (ሱረቱ ኢስራዕ 59)
የአሏህ ምልክቶችን መፍራት እንዲያንሰራራ ማድረግ
በዚህ አለም ውስጥ የሙስሊሞች ገንዘባቸው ጊዜያቸው ነው። ከገንዘብ እና ከማንኛውም የዋጋ ተመን ሁሉ ይበልጣል። ኢብን አባስ (ረ.ዐ) ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ይዞ እንዳወራው እንዲህ አለ፡ ‹‹ብዙ ሰዎች የሚያጧቸው ሁለት በረካዎች አሉ፡ ጤና እና ትርፍ ጊዜ ናቸው። (ቡኻሪ 6412)