ቅዱስ ቁርአን
ሃያሉ አሏህ ቁርአንን የገለጠው ከፍጡራኖቹ ሁሉ በላጭ እና የነብያት መደምደሚያ ለሆኑት ለነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ነው። ለሰው ልጆች ሁሉ መመሪያ እና ሰዎችን ከጨለማ አውጥቶ ወደ ብርሃን የሚያሻግር ነው። ሃያሉ አሏህ እንዲህ ይላል፡ "በእርግጥ ከአሏህ ዘንድ ብርሃን እና ገላጭ መጽሐፍ መጣላቸው። አሏህ ውዴታውን የተከተሉትን ሰዎች የሰላምን መንገዶች በእሱ ይመራቸዋል። በፈቃዱም ከጨለማ ወደ ብርሃን ያመጣቸዋል። ወደ ቀጥተኛውም መንገድ ይመራቸዋል።" (ሱረቱል ማኢዳ 15-16)