መማርዎን ይቀጥሉ

ሎግ ኢን አላደረክም
መማር ለመጀመር፣ እድገትን ለመከታተል፣ ነጥቦችን ለመሰብሰብ እና ወደ ውድድር ለመግባት አሁኑኑ በታ ፕላትፎርም ይመዝገቡ፡ ከተመዘገቡ በኋላ ለሚማሯቸው ርዕሶች የኤሌክትሮኒክስ ሰርተፍኬት ይደርስዎታል።

የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል

ትምህርት የመተጫጨት አደቦች (ስነ-ስርአቶች)

በዚህ ትምህርት ውስጥ ስለ ጋብቻ ጥያቄ ፅንሰ ሃሳብ እና ከእሱ ጋር ተያያዥ የሆኑ ስነ-ስርአቶችን ትማራላችሁ።

1 የጋብቻ ጥያቄ ፅንሰ ሃሳብን ትረዳላችሁ።2 በእስልምና ውስጥ የጋብቻ ጥያቄን ሲያቀርቡ ሊከተሏቸው የሚገቡ ስነ-ስርአቶችን ታውቃላችሁ።3 ጋብቻ ውስጥ እስልምና ያለው ያማረ አቋም ትረዳላችሁ

የጋብቻ ጥያቄ አንድ ሰው በአሏህ ህግ እና በነብዩ ሱና መሰረት አንዲትን ሴት ሊያገባት እንደሚፈልግ ለሴቷ ጠባቂ የቅርብ ዘመድ ማሳወቅ ነው።

ከአሏህ ፀጋዎች ውስጥ አንዱ ደስታን ፣ ጥሩ ምርጫን እና ማረጋገጫን ፣ ሁለቱም ጥንዶች አንዳቸው ካንዳቸው ጋር ተስማምተው እና ተግባብተው ለመተጫጨት የሚረዳቸውን ስነ-ስርአት ማውጣቱ ነው።

ከጋብቻ ጥያቄ ስነ-ስርአቶች መካከል

1 አንድ ሙስሊም ሰው ለጋብቻ የጠየቃትን ሴት ሌላ ሙስሊም ሰው መጠየቅ የለበትም። የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹ቀድሞ የተስማማበትን ሽያጭ ሌላ ሰው (ከፍ ያለ ዋጋ ስላቀረበለት) ሽያጩን አይሰርዝ። በሙስሊም ወንድሙ ቀድማ የታጨችን ሴት እጇን አይጠይቅ (እሷን ለማግባት አይጠይቅ)።የመጀመሪያው ጠያቂ እስካልተዋት ወይም እንዲጠይቃት እስካልፈቀደለት በቀር።›› (ቡኻሪ 5142 ፣ ሙስሊም 1412)

2 እጮኛው እሷን ለማግባት የሚገፋው ነገር በእሷ ውስጥ ይመለከት ዘንድ እሷን ማየት ይችላል። የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹ተመልከቷት፤ በእርግጥ ያነ በሁለታቸው መካከል ውዴታ እንዲፀና ያደርጋልና።›› (ትርሚዚ 1087) ይበልጥ ነገሮችን የተሻለ ያደርጋልና። ከዚህ በተጨማሪ ሴቷ እጮኛዋን የማየት መብት አላት። ከእውቀት ሰዎች ከፊሎቹ ይበልጥ እሱን የመመልከት መብት ያላት እሷ ናት ይላሉ።

ጃቢር ኢብን አብዱሏህ እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹አንዳችሁ አንዲትን ሴት ለጋብቻ በጠየቃችሁ ጊዜ እሷን ለማግባት በእሷ ውስጥ የሚገፋፋውን ነገር ከቻለ ይመልከት አሉ። ጃቢርም እንዲህ አለ፡ ‹‹አንዲትን ሴት ለጋብቻ ጠየኩኝ፤ እሷን ለማግባት የገፋፋኝን ነገር እስካገኝ ድረስ በሚስጥር እመለከት ነበር። ከዚያም አገባኋት።›› (አቡዳውድ 2082)

እጮኛን የመመልከት አደብ

١
1 እጮኛው ሴቷን ሊመለከታት የሚገባው ሊያገባት ከወሰነ ብቻ ነው።
٢
2 እሷን ባለመውደዱ የጋብቻ ጥያቄውን በመሰረዝ እሷን ላለመጉዳት እና ላለማስከፋት የጋብቻ ጥያቄ ከማቅረቡ በፊት ሊያያት ይገባል።
٣
3 በምርጫው እርግጠኛ ይሆን ዘንድ ብዙ ጊዜ ደጋግሞ ማየቱ የተፈቀደ ነው።
٤
የማየት ፍላጎቱ ከተሳካ ከማየት መቆጠብ አለበት ገና አጅነቢ ነችና

3- ከዋና ዋና የማጨት ሥነ-ሥርዓቶች መካከል ወንዱም ሴቱም ምርጫቸውን በሚገባ የሚያደርጉ በመሆናቸው በትክክለኛ መሠረት ላይ ተመስርተው አላህ ፈቅዶ መረጋጋት የሰፈነበት ቤት ይመሠርታሉ።

4 ከጋብቻ ጥያቄ ስነ-ስርአቶች መካከል አንዱ ጥሩ ዘሮቹን ለማብዛት ለምለም (ወላድ) ሴትን ለማግባት መፈለግ ነው። የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹ተወዳጅ እና ለምለም (ወላድ) ሴትን አግቡ፤ ሌሎች ህዝቦችን በእናንተ ቁጥር እበልጣለሁና።››

5 ምክር መፈለግ እና ዱአ ማድረግ ያስፈልጋል። በእርግጥ ሙስሊም ሰው ዱአ ያደርጋል፤ ጌታውን ይማፀናል ፣ አሏህን የሚፈሩ እና ጥሩ ግንዛቤ ያላቸውን ሰዎችም በሁሉም ጉዳዮቹ ያማክራል። ነገርግን ለማግባት መወሰን በሰው ልጅ ህይወት ውስጥ ጠቃሚ ውሳኔ ነው። ሆኖም ምክር ማግኘት እና ዱአ ማድረግ መቅደም አለበት።

6 ሁለቱ ጥንዶች በሁሉም ጉዳዮች ዙሪያ ግልፀኝነት እና ታማኝነት ሊኖራቸው ይገባል። እንከኖቻቸውን መደበቅ ፣ ሆንብሎ መዋሸት አይኖርባቸውም። ምክኒያቱም ወደ ፊት ከተጋቡ በኋላ ትዳራቸው ላይ ተፅኖ ይፈጥራልና ነው።

7 ከጋብቻ ጥያቄው ጋር በተያያዘ ሃይማኖታዊ መስፈርቶችን ከግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርብናል።ይህ የጋብቻ ቃልኪዳን ነው እንጅ ጋብቻው ተፈፀመ ማለት አይደለም። ሆኖም ሁለቱ የወደፊት አጋሮች እጅ ለእጅ መጨባበጥ ፣ ለብቻቸው ተገልለው መቀመጥ ፣ ብፍቅር ቃል መጠራራት እና አንዳቸው ለአንዳቸው ሽቶ መነስነስ እና መጊያጊያጥ የለባቸውም።

ትምህርቱን አጠናቅቀሃል


ፈተና ጀምር