የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት ዝምድናን መቀጠል
ለዘመዶቻችን ካለን ነገር ማካፈል ፣ ለእነሱ ደግ መሆን ፣ መተዛዘንን ፣ መጠያየቅን ፣ ደህንነታቸውን ማረጋገጥን እና የሚጠቃቀሙበትን ነገር ለእነሱ መስጠትን አቅፎ ይይዛል።
ቅዱስ ቁርአን እና ሱና ዝምድና መቀጠልን ያስተምራል፤ እሱን ማቋረጥንም ይከለክላል። አሏህ ከሃዲያንን ሲገልፅ እንዲህ አለ፡ ‹‹እነዚያ የአሏህን ቃል ኪዳን ከአጠበቀባቸው በኋላ የሚያፈርሱ እንዲቀጠልም በሱ ያዘዘውን ነገር የሚቆርጡ በምድር ላይ የሚያበላሹ እነዚያ እነሱ ከሳሪዎቹ ናቸው።›› (ሱረቱል በቀራ 27) አሏህ እንዲህ አለ፡ ‹‹ብትሸሹም በምድር ላይ ማበላሸትን ፣ ዝምድናችሁን መቁረጥን ከጀላችሁን?) (ሱረቱ ሙሐመድ 22)
በሌላ በኩል ደግሞ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹በአሏህና በመጨረሻው ቀን ያመነ ዝምድናን ይቀጥል።›› (ቡኻሪ 6138) እንዲህም አሉ፡ ‹‹አሏህ ፍጡራኑን ፈጠረ፤ ከፍጥረቱ በጨረሰም ጊዜ ፅንሱም አለ፡ ‹‹አሏህ ሆይ! ከዚህ ቦታ እኔን ከሚጎዱ ሁሉ ያንተን ከለላ እሻለሁ።አሏህ አለ፡ ‹‹አዎ! ከአንተ ጋር መልካም ግኑኝነት የሚያደርግን በማድረጌ አትደሰትምን?›› እሱም (ፅንሱ)፡ አዎን! ጌታየ ሆይ! ይላል። አሏህም፡ ያ ለአንተ ነው አለ። የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ሲሉ (ከቁርአን ) አክለው ተናገሩ፡ ‹‹ብትሸሹ በምድር ላይ ማበላሸትን ፣ ዝምድናችሁን መቁረጥን ከጀላችሁን?›› (ሱረቱ ሙሐመድ 22) (ቡኻሪ 5987 ፣ ሙስሊም 2554)
እንደየ ቅርበቱ እና እንደ ሰውየው ዝምድና ሸሪአ ዝምድናን መቀጠልን ያዛል።
ዝምድናን መቀጠሉ ግዴታ የሆነ
ይህም ልክ እንደ ወላጆች ፣ ወንድ ልጆች ፣ ሴት ልጆች ፣ ወንድሞች ፣ እህቶች ፣ አክስት ፣ አጎት ፣ ያሉ መህረም ጋር ዝምድናን መቀጠል ነው።
ዝምድናን መቀጠሉ የተወደደ የሆነ
ይህም ልክ እንደ አጎት ልጅ ፣ የአክስት ልጅ ያሉ መህረም ያልሆኑ ሰዎች ጋር ዝምድናን መቀጠል ነው።
ዝምድናን እንዴት መቀጠል ይቻላል
ዝምድናን መቀጠል አንድ ሰው በቻለው አቅም መልካም ነገርን መስጠትን እና መጥፎ ነገርን ከዛ ሰው ማስወገድን ይይዛል። ሰላምታ ፣ መልካም ቃል ፣ በገንዘብ ድሆችን ማገዝ ፣ መጥፎ ነገርን ማሰወገድ ፣ ጥሩ ፊት ማሳየት ፣ ዱአ ማድረግ ወ.ዘ.ተ ሊሆን ይችላል።
ዝምድናን የመቀጠል ምሳሌ
ዝምድናን የመቀጠል ትሩፋቶች (ጥቅሞች)
1 ለመዋደድ እና በቤተሰብ መካከል ዝምድናን ለመቀጠል ሰበብ ነው።
የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹ስለ ዘራችሁ ተማሩ፤ ዝምድናን ለመቀጠል ያቀላልና። በእርግጥ ዝምድናን መቀጠል በዘመዶች መካከል ውዴታን ይጨምራል ፣ ሃብትን ያሰፋል ፣ እድሜንም ይጨምራል።›› (ትርሚዚ 1979)
2 ሪዝቅን ያሰፋል ፣ እድሜን ይጨምራል
የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹ሪዝቁ እንዲሰፋ እና እድሜው እንዲረዝም የሚፈልግ ሰው ዝምድናን ይቀጥል።›› (ቡኻሪ 2067 ፣ ሙስሊም 2557)
3 ዝምድናን የሚቀጥሉ ሰዎችን አሏህ እነሱን ይቀጥላቸዋል
የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹አሏህ ፍጡራኑን ፈጠረ፤ ከፍጥረቱ በጨረሰም ጊዜ ፅንሱም አለ፡ ‹‹አሏህ ሆይ! ከዚህ ቦታ እኔን ከሚጎዱ ሁሉ የአንተን ከለላ እሻለሁ። አሏህ አለ፡ ‹‹አዎ! ከአንተ ጋር መልካም ግኑኝነት የሚያደርግን በማድረጌ አትደሰትምን? እሱም (ፅንሱ)፡ አዎን! ጌታየ ሆይ! ይላል። አሏህም፡ ያ ለአንተ ነው አለ። የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ከቁርአን አክለው ተናገሩ፡ "ብትሸሹ በምድር ላይ ማበላሸትን ፣ ዝምድናችሁን መቁረጥን ከጀላችሁን?" (ሱረቱ ሙሐመድ 22) (ቡኸሪ 5987 ፣ ሙስሊም 2554)
4 ጀነት ለመግባት ሰበብ ነው
አንድ ሰው ጀነት የሚያስገባው ስራ ምን እንደሆነ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጠይቋቸው ሲመልሱ እንዲህ አሉ፡ ‹‹አሏህ ብቻ ተገዙ፤ ለእሱም አንድንም ባላንጣ አታብጁ፤ ሶላት ስገዱ ፣ ዘካ ክፈሉ ፣ ዝምድናን ቀጥሉ።›› (ቡኻሪ 1396 ፣ ሙስሊም 13)