የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት የጋብቻ ስነ-ስርአት
ከጋብቻ ጋር የተያያዙየህግ ድንጋጌዎች አንዳንዶቹ ከጋብቻው ውል በፊት የሚቀድሙ ፣ አንዳንዶቹ በውሉ ጊዜ እና አንዳንዶቹ ደግሞ ከውሉ በኋላ የሚፈፀሙ ናቸው። ባለ ትዳሮች ሊከተሉት ሚገባ የጋብቻ ስነ-ስርአትን የሚፈፅሙ ናቸው። ባለትዳሮች ሊከተሉት የሚገባ የጋብቻ ስነ-ስረአትን እስልምና አስገኝቷል። ይህ ሊሆን የሚገባው ከአሏህ ሽልማትን ለመቀበል በመፈለግ እና የትዳር ግኙኝነትን ለመጠበቅ እና ለማጠናከር ተስፋ በማድረግ ነው።
1 ኒያ (ማሰብ)
1 ኒያ (ማሰብ) በእስልምና ውስጥ ትልቅ ቦታ አለው። ተከታዩ ሐዲስ ለዚህ ትልቅ ማስረጃ ነው። ‹‹የስራዎች ሽልማት መሰረቱ ማሰብ ነው።›› ሁሉም ሰው ባሰበው ነገር ላይ ሽልማቱን ያገኛል።›› (ቡኻሪ 1 ፣ ሙስሊም 1907) ሆኖም ጥንዶቹ በጋብቻ ውስጥ መልካምን ነገር አስበው መግባት አለባቸው። ከአሏህ ብዙ ትሩፋት እና ሽልማት ለማግኘት በመፈለግ ብዙ ቢያስቡ (ኒያ) ቢያደርጉ በላጭ ነው። አንድ ሰው በጋብቻ ውስጥ ሊኖር ከሚችለው በጎ ሃሳቦች (ኒያዎች) መካከል ጋብቻ የሚያበረታቱ ትዕዛዛትን ለመፈፀም ፣ አሏህን ብቻ የሚገዙ ዘሮችን ለማብዛት ፣ እራስን በጋብቻ ለመሰብሰብ እና ከፈተና ለመጠበቅ ወ.ዘ.ተ የሚሉት ናቸው።
2 በጋብቻ ሌሊት ሱናውን መከተል
የጋብቻ ድግስ የተረጋገጠ ሱና ነው። ምክኒያቱም አብዱ ረህማን ኢብን አውፍ (ረ.ዐ) ባገባ ጊዜ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለውታልና፡ ‹‹አንዲት በግ እንኳ ብትሆን ደግስ።›› (ቡኻሪ 2048 ፣ ሙስሊም 1427)
በድግስ ጊዜ መታሰብ ያለበት ነገር
4 በሰርግ ሰአት የሴቶች መዝፈን
ጥሩ እና የተፈቀዱ ቃላትን በመጠቀም ከወንዶች እይታ እርቀው ድቤ እየደቡ መጫወት ለሴቶች የተፈቀደ ነው። ሌላ የሙዚቃ መሳሪያ መጠቀም ግን የለባቸውም። በዚህ የደስታ ጊዜ መጫወት እና መደሰት በእስልምና የተፈቀደ ነው።
5 በደግነት መኗኗር
ከተረጋገጡ የጋብቻ ስነ-ስርአቶች ውስጥ አንዱ ተፈላልጎና ተዋዶ ህይወትን በተገቢው መንገድ አብሮ መኖር ነው። ሆኖም በአሏህ ፈቃድ ውዴታቸው የደስታን ህይወት እንዲኖሩ ያስችላቸዋል። አሏህ እንዲህ አለ፡ ‹‹በደግነት ተኗኗሯቸው።›› (ሱረቱ ኒሳዕ 19)