የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት የመንገደኛና የህመምተኛ ሶላት
አንድ ሙስሊም አእምሮው ጤናማ እስከሆነ ድረስ በማንኛውም ሁኔታ ሶላት ግዴታው ነው። ነገር ግን እስልምና በሽታንና ጉዞን ጨምሮ የሰዎችን የተለያዩ ሁኔታዎችና ችግሮችን ግምት ውስጥ ያስገባል።
መንገደኛ ከቦታ ቦታ በሚዘዋወርበት ወይም ከአራት ቀን ላነሰ ወቅት ጊዚያዊ ቆይታ በሚያደርግበት ስፍራ ሆኖ ባለ አራት ረከዓ ሰላቶቹን ሁለት ረከዓ አድርጎ መስገድ ይወደድለታል፡፡ዙህር ዐሱርና ዒሻን የአገሬ ነዋሪ የሆነ ኢማምን ተከትሎ ካልሰገደ በስተቀር በአራት አራት ረከዓ ምትክ ሁለት ሁለት አድርጎ ይሰግዳል፡፡ እንዲያ ከሆነ ግን ኢማሙን ሊከተልና እንደሱ አራት ረከዓ ሊሰግድ ይገባል፡፡
ከፈጅር ሱና በስተቀር የተቀሩትን ተቀጥላ ሱና ሰላቶችን ቢተው ወይም ባይሰግድ ይችላል፡፡ የዊትርን ሶላት እና የሌሊት ሶላትን እንዲጠብቅ ተደነገገበት።
ዙህርና ዐስሩን በአንድነት መግሪብና ዒሻን በአንድነት አቆራኝቶ መስገድ ይችላል፡፡ በተለይ በሚዘዋወርበትና በሚሳፈርበት ወቅትና ሁናቴ ላይ ከሆነ የአላህን ህግ ገራገርነት እዝነትና ማጨናነቅ የሌለው መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡
መቆም የማይችል ወይም መቆም የሚያስቸግረው ወይም ለመቆም የሚያስችለው ፈውሱ የሚዘገይበት የሆነ ህመምተኛ ቆሞ መስገድ ይሻርለታል፡፡ እርሱ የሚሰግደው ቁጭ ብሎ ነው፡፡ቁጭ ማለትም ካልቻለ በጎኑ እንደተጋደመ ይሰግዳል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡ ቁመህ ስገድ፡፡ ካልቻልክ ቁጭ ብለህ ስገድ፡፡ ካልቻልክ በጎንህ ተጋድመህ ስገድ አል ቡኻሪ 1066