መማርዎን ይቀጥሉ

ሎግ ኢን አላደረክም
መማር ለመጀመር፣ እድገትን ለመከታተል፣ ነጥቦችን ለመሰብሰብ እና ወደ ውድድር ለመግባት አሁኑኑ በታ ፕላትፎርም ይመዝገቡ፡ ከተመዘገቡ በኋላ ለሚማሯቸው ርዕሶች የኤሌክትሮኒክስ ሰርተፍኬት ይደርስዎታል።

የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል

ትምህርት በእህራም ውስጥ የተከለከሉ ነገሮች

ሀጃጁ ወይም ኡምራ አድራጊው ኢህራም ሲገባ ከበርካታ ክልከላዎች መራቅ አለበት። በዚህ ትምህርት ውስጥ የምትማሩት ይህ ነው።

  • ስለ ኢህራም ክልከላዎች ማወቅ።
  • የእነዚህ ክልከላዎች የፈጻማ ሰው ላይ የምበየኑ ድንጋጌዎችን ማወቅ።

በኢህራም ወቅት የሚከለከሉ ነገሮች

ለሐጅ ወይም ለኡምራ ኢህራም ላይ ያለ ሰው ማድረግ የተከለከለው ነገሮች ነው።

የኢህራም ክልከላ በ3 ይከፈላል፡፡

١
ለወንዶች እና ለሴቶች የተከለከለ ክፍል
٢
ለወንዶች ብቻ የተከለከለ ክፍል
٣
በሴቶች ብቻ ሀራም የሆነ ክፍል

ለወንድ እና ለሴት በኢህራም የተከለከሉት ነገሮች

١
ፀጉርን በመለጨትም ይሁን በሌላ መንገድ ማስወገድ ጥፍርን መቁረጥ
٢
ሰዉነቱን ወይም ልብሱን ሽቶ መቀባት።
٣
ከሴት ጋር ግብረስጋ ግንኙነት መፈፀም በስሜት ከሴት ጋር መነካካት፣ መሳሳምና መደባበስ።
٤
የጋብቻ ውል፣ መህራሙ ወንድ ይሁን ሴት
٥
በኢህራም ውስጥ ያለ ሀጃጅ አደን ማድረግ የተከለከለ ነው, ስለዚህ ወፎችን እና የዱር እንስሳትን ማደን አይፈቀድለትም.

ለወንዶች የኢህራም ክልከላዎች

١
የተሰፋ ልብስ መልበስ; እያንዳንዱ አካል ክፍል ዙሪያውን የምሸፍን እንደ ሸሚዝ፣ ቀሚስ፣ ሱሪ፣ ቦላሌ እና የመሳሰሉት።
٢
ጭንቅላትን ብልብስ መሸፈን፡ ነገር ግን የህንጻ ጣሪያዎች፣ ጀልባዎች እና ጃንጥላዎች ጭንቅላቱን ብሸፍኑ ምንም ችግር የለበትም።

ለሴቶች ከተከለከሉት ኢህራም መካከል

١
ኒቃብ እና ፊትን መሸፈኛ፡- መህራም ያልሆኑ ወንዶች በአጠገቧ እስካልተላለፉባት ድረስ ፊቷን እንድትገልጥ ደነገገላት፡ በዚህ ጊዜ ፊቷን መሸፈን ትችላለች እና ይህ ሽፋን ፊቷን ቢነካ አይጎዳትም።
٢
ጓንት መድረግ

ከነዚህ የተከለከሉትን ነገሮች በመዘንጋት፣ ባለማወቅ ወይም በግዴታ የሠራ ሰው በርሱ ላይ ኀጢአት የለበትም። አላህ እንድህ ብሏል (በእናንተም ላይ በተሳታችሁት ነገር ምንም ኀጢአት የለባችሁም፤ ልቦቻችሁም ባሰቡት እንጂ)። (አል-አህዛብ፡ 5) ግን ካስታወሱ ወይም ካወቁ የተከለከሉትን ወዲያውኑ መተው አለበት።

ለተፈቀደለት ችግር የተከለከለን ነገር የሰራ ሰው ቤዛ ይክፈል በእርሱ ላይ ኃጢአት የለበትም።

አላህ እንዲህ ብሏል " ሀድዩም እስፍራው እስከሚደርስ ድረስ ራሶቻችሁን አትላጩ፡፡ ከናንተም ውስጥ በሽተኛ ወይም በራሱ ሁከት ያለበት የኾነ ሰው (ቢላጭ) ከጾም ወይም ከምጽዋት ወይም ከመሥዋዕት ቤዛ አለበት፡፡ ጸጥታም ባገኛችሁ ጊዜ እስከ ሐጅ በዑምራ የተጣቀመ ሰው ከሀድይ የተገራውን (መሠዋት) አለበት፡፡ ያላገኘም ሰው ሶስትን ቀኖች በሐጅ ወራት፤ ሰባትም በተመለሳችሁ ጊዜ መጾም አለበት፡፡ ይህች ሙሉ ዐሥር (ቀናት) ናት፡፡ ይህም (ሕግ) ቤተሰቦቹ ከቅዱሱ መስጊድ አቅራቢያ ላልኾኑ ነው፡፡ አላህንም ፍሩ፤ አላህም ቅጣተ ብርቱ መኾኑን እወቁ፡፡" በቀራ 196

ሆን ብሎ የተከለከለን ነገር ያለችግር የሰራ ሰው ቤዛ መክፈል አለበት ኃጢአተኛም ነው።

ቤዛውን ከግምት ውስጥ በማስገባት የኢህራም ክልከላዎች በአራት ምድቦች ይከፈላሉ።

١
አንደኛ፡ ቤዛ የማያስፈልግ እሱ የጋብቻ ውል ነው።
٢
ሁለተኛ፡ ግመል ቤዛ የምያስከፍል፡ እሱም በሐጅ ወቅት ከመጀመሪያ ፍቺ በፊት የሚደረግ የግብረስጋ ግንኙነት ነው።
٣
ሦስተኛ፡ ቤዛው እሱን ራሱ ወይም ከሱ እኩል የሆነ እንሰሳ የሆነ። እሱ አራዊት ማደን (መግደል) ነው።
٤
አራተኛ፡- በጾም፣ በሶደቃ ወይም እርድ የምከፈል ነው። እሱ (የጉዳት ቤዛ) ሲሆን ይህም ካለፉት ሦስቱ በስተቀር ጭንቅላትን መላጨት እና የተቀሩትን ክልከላዎች ነው።

ትምህርቱን አጠናቅቀሃል


ፈተና ጀምር