የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት የነብዩ ሙሐመድ ሰ/ዐ/ወ/ ባህሪያት
የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ባህሪያት
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የውብ ባህሪያት እና የታላቅ ምግባር ባለቤት ናቸው። እሳቸው እጅግ በጣም ጥሩ ባህሪያት ፣ ጥሩ ስነምግባር እና ታላቅ ስብዕና ያላቸው ናቸው። በመልካም ባህሪያቸው እና በታላቅ ምግባራቸው የሚያስተነትን ሰው የሰው ልጆች ከሚያውቋቸው ሁሉ የበለጠ ታላቅ ሰው ናቸው።
ከአሏህ አገልጋዮች ሁሉ በላጩ እናአሏህ ዘንድ ከሁሉም በላይ ተወዳጁ ኸሊሉሏህ (የአሏህ ወዳጅ) እና የምርጦች ምርጥ እሳቸው ናቸው። አሏህ ለፍጡራኑ ሁሉ ነበቭይ እና መልዕክተኛው እንደሆኑ እና ሰዎችን ወደ መልካም ነገር እንዲያመላክቱ እና ወደ መመሪው ጥሪ እንዲያደርጉ መርጧቸዋል።
ከምርጥ እና ከጥንታዊ የሰው ዘር መርጧቸዋል። በባህሪያቸው እና በምግባራቸውለሰው ልጆች ሁሉ ፍፁም ባሪ ምሳሌ አድርጓቸዋል። በውብ ገፅታቸው ፣ በሚያምር መልካቸው እና ፍክት ባለው ፈጊታቸው ይለያሉም። ከሶሃቦች (ከሃዋሪያዎቻቸው) መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል።
የአሏህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) አካላዊ አቋም ገለፃ
አነስ ቢን ማሊክ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሲገልፅ እንዲህ አለ፡ ‹‹ልከኛ ቁመት ነበራቸው፤ አይረዝሙ አያጥሩ።›› (ቡኻሪ 3547)
2 የተከበረው ፊታቸው መገለጫ
እሳቸው ከሰዎች ሁሉ የበለጠ ውብ ፊት ነበራቸው። ፊታቸው ክብ ሆኖ በመጠኑ ረዘም ያለ ፣ በጣም የሚያምር ብሩህ እና አንፀባራቂ ነበር። ፊታቸው ጨረቃዋ ሙሉ ሆና እነደምታበራበት ሌሊት ያንፀባርቅ ነበር። ላያቸው ሰው ፊታቸው ለወዳጅነት ይጋብዛል። በተደሰቱ ጊዜ ደግሞ የፊታቸው ሚስጥር ተገልጦ ሲያንፀባርቅ የግንባራቸው መስመር ይሰበሰብ ነበር። እንዲሁም ጆሯቸው ፍፁም ያምር ነበር።
የፊታቸው ገፅታ
ፂማቸው ጥቅጥቅ ያለ ወፍራም ፣ ጥቁር እና ፊታቸውን ያካበበ ነው። በአገጫቸው እና በታችኛው ከንፈራቸው መካከል ያለው ፂም ጎላ እና ከፍ ያለ ነው። ከታችኛው ከንፈራቸው ስር ያለው ፀጉር የፂማቸው አካል መስሎ ይተኛ ነበር።
3-የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የቆዳ ቀለም
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ምርጥ የቆዳ ቀለም ነበራቸው። ነጣ ያለ ሆኖ ከቀይነተር ጋር የተቀላቀለ የደምግባት ነበራቸው። ነጣ ያለ እና ክብ ውብ ፊት ነበራቸው። ጁበይር ቢን ሙቂም እንዳስተላለፈው አሊ ቢን አቢጧሊብ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሲገልፃቸው እንዲህ አለ፡ ‹‹ትልቅ ራስ ፣ ነጣ ያለ ደም ግባት (መልክ) ፣ ትልቅ ፂም ነበራቸው።›› (ሙሰነድ አህመድ 944)
4-የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ፀጉር
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ብዙ ፀጉር ነበራቸው። ፀጉራቸውን አሳጥረው በቆረጡት ጊዜ እስከ ጆሯቸው መካከል ይደርስ ነበር። ረዝም ሲሆን ደግሞ እስከትከሻቸው ይደርስ ነበር። ፀጉራቸው ቀጥ ያለ ወይም የተጠቀለለ አልነበረም። ይልቁንም መካከለኛ ገፅታ ነበረው።አንዳንዴ በገርንባራቸው ዝንፍል ይላል። ሌላ ጊዜ ደግሞ ከግንባራቸው ላይ ምንመ ፀጉር ሳይተው ፀጉራቸውን ከራሳቸው መሃል ላይ ለሁለት ከፍለውት (ገምሰውት) ይዘናጠፍ ነበር።
ቀታዳ እንዳስተላለፈው አነስ ኢብን ማሊክ ስለ አሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ፀጉር እንዴት እንደሆነ ተጠይቆ ሲመልስ እንዲህ አለ፡ ‹‹የአሏህ መልዕክተኛ ፀጉር ብዙም ቀጥ ያለ ብዙም የተጠቀለለ አልነበረም። እስከ ትከሻቸው እና እስከ ጆሯቸው የታችኛው ክፍል ድረስ ይንጠለጠል ነበር።›› (ቡኻሪ 5905 ፣ ሙስሊም 2338)
ራሳቸው እና ፂማቸው ላይ ያለው ሽበት ፀጉር ሃያ አምስት እንኳ አይደርስም። አብዘሃኛውም የነበረው ፂማቸው ላይ ነው። ሆኖም ነጭ ፀጉር የነበረው በአገጫቸው እና በታችኛው ከንፈራቸው መካከል ነው። እራሳቸው ላይ ያለው ነጭ ፀጉር ደግሞ ፀጉራጨውን በሚገምሱበት ቦታ ላይ ነበር።
እናም ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ያለምንም ቅንጦት እና መሞላቀቅ ፀጉራቸውን ያፀዱ ፣ ያበጥሩ እና አሳምረው ይንከባከቡት ነበር። ለፀጉራቸው እንክብካቤ ሲያደርጉ ሁሌም በቀኝ በኩል ይጀምሩ ነበር።
5 የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ትከሻ ፣ ክንድ እና እጅ ገለፃ
አነስ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ፡ ‹‹ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እጅ በላይ የሚለሰልስ ሐር ወይም አጥላስ (ከፋይ ልብስ) ነክቸ አላውቅም።›› (ቡኻሪ 3561 ፣ ሙስሊም 2330)
የነብይነት ማብቂያ ምልክት
በግራ ትከሻቸው በኩል የነብይነት ማብቂያ ምልክት አለ። ይህም ከአካላቸው ጋር የሚመሳሰል ከፍ ያለ እነደ የእርግብ እንቁላል ያህል መጠን ያለው ስጋ ነው። ዙሪያውን በፀጉር የተሸፈነ ሲሆን ሁለት ምልክቶች አሉት።
ጃቢር ኢብን ሳሙራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ፡ ‹‹የእርግብ እንቁላል የሚያክል ማተም ከጀርባቸው ላይ አይቻለሁ።›› (ሙስሊም 2344)
7 የደረታቸው እና የሆዳቸው ገለፃ
8 የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ባት እና እግር
ላበታቸው ከሚስክ በላይ ውዳል (ይሸታል-ለጥሩ ሽታ)። የሆነ ሰው ከእሳቸው ጋር እጅ ለእጅ ቢጨባበጥ ቀኑን ሙሉ ጠረናቸውን ይሸታል። ብዙ ጊዜም ሽቶን ይጠቀማሉ።
አነስ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ፡ ‹‹ሚስክ ወይም አንበር ፈፅሞ አሽትቼ አላውቅም፤ የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ደስ የሚል መአዛ (ሽታ) የሚበልጥ ቢሆን እንጅ።›› (ሙስሊም 2330)
የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ታላቅ ግብረገብ (ስነ-ምግባር) የሚገልፅ ሁሉን አቀፍ ቃል
ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡ "በእርግጥ አንተ በታላቅ ምግባር ላይ ነህ።" (ሱረቱል ቀለም 4) ጅብሪል ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ እሳቸው በመጣ ጊዜ ክፉኛ በፍርሃት ተውጠው የሙዕሚኖች (የአማኞች) እናት ለሆነችው ኸድጃ (ረ.ዐ) እንዲህ አሏት፡ ‹‹ለነፍሴ እፈራለሁ›› አሏት እሷም ለእሳቸው ‹‹አብሽር! በአሏህ ይሁንብኝ! አሏህ ፈፅሞ አያሳፍርህም። በአሏህ ይሁብኝ ዝምድናን ትቀጥላለህ ፣ አውነትን ትናገራለህ ፣ ድሆችን እና ረዳት የሌላቸውንም ትረዳለህ ፣ እንግዶችን በእንግድነት ታስተናግዳለህ ፣ መከራ የደረሰባቸውን ታፅናናለህ አለች።›› (ቡኻሪ 4953 ፣ ሙስሊም 160)
1 የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ታማኝነት
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በታማኝነታቸው ይታወቃሉ፤ ነብይ ሁነው ከመላካቸው በፊት ህዝቦቻቸው ‹‹አል-አሚን›› ታማኙ ብለው ይጠሯቸው ነበር። ምንም እንኳ ነብይ ሁነው ከተላኩ በኋላ ጠላት አድርገው ቢይዟቸውም እንኳ አደራቸውን (አማናቸውን) እሳቸው ዘንድ ያስቀምጡ ነበር።
2 አዛኝ እና ርህሩህነታቸው
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ለህዝቦቻቸው አዛኝ እና ርህሩህ ነበሩ። ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡ "በእርግጥ! ችግራችሁ በእሱ ላይ የሚያሳዝነው ፣ በእናንተ (እምነት) ላይ የሚጓጓ ፣ ለምዕመናን አዛኝ ርህሩህ እና ከእናንተው የሆነ መልዕክተኛ መጣላችሁ።" (ሱረቱ ተውባ 128) ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡ ‹‹ከአሏህ በሆነ ችሮታ ለዘብክላቸው። አመለ መጥፎ ልበ ደረቅ ብትሆን ኖሮ ከዙሪያህ በተበታተኑ ነበር።" (ሱረቱል ኢምራን 159)
3 ይቅር ባይነታቸው እና መሃሪነታቸው
የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ መካ ድል አድርገው በገቡ ጊዜ የመካ ባላበቶች እና መሪዎቻቸው ከፊታቸው እጅ ሰጥተው ቆሙ። ምንም እንኳ በጠላትነታቸው ቢዘልቁም እና እሳቸውን እና ሶሃቦቻቸውን ለብዙ አመታት ቢያሰቃያቸውም ‹‹ዛሬ አልወቅሳችሁም፤ ነፃ ናችሁና ሂዱ›› አሏቸው። ይህን እሳቸው እንጅ ሌላ ማን ይላል።
4 ሰዎችን ለመምራት የነበራቸው ጉጉት
ሰዎችን በመምራት ላይ ቅን ነበሩ። ለእነሱ በማዘን ነፍሳቸውን (እራሳቸውን) እስኪያጡ ድረስ ማለት ነው። ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡ "ምናልባት! በኮቲዎቻቸው ላይ (ከአንተ መዞራቸውን አይተህ) በሃዘን እራስህን እንዳታጣ። ምክኒያቱም በዚህ ሐዲስ (ቁርአን) አያምኑምና።" (ሱረቱል ካህፍ 6)
5 ጥንካሬያቸው እና ጀግንነታቸው
አሊ (ረ.ዐ) የነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) ጀግንነት ሲገልፅ የጀግኖች ሁሉ ጀግና ነበሩ ብሏል። ‹‹ፍልሚያው (ጦርነቱ) በተጧጧፈ ጊዜ እና ሁለቱም በፍልሚያው ሲፋጩ ከአሏህ መልዕክተኛ ኋላ መሆንን እና መጠለል እንፈልጋለን፤ ለጠላትም ከእሳቸው የበለጠ የቀረበ አልነበረም።›› (አህመድ 1347)