መማርዎን ይቀጥሉ

ሎግ ኢን አላደረክም
መማር ለመጀመር፣ እድገትን ለመከታተል፣ ነጥቦችን ለመሰብሰብ እና ወደ ውድድር ለመግባት አሁኑኑ በታ ፕላትፎርም ይመዝገቡ፡ ከተመዘገቡ በኋላ ለሚማሯቸው ርዕሶች የኤሌክትሮኒክስ ሰርተፍኬት ይደርስዎታል።

የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል

ትምህርት መጥፎ እና የተከለከሉ የገንዘብ ግብይቶች

በዚህ ትምህርት ውስጥ ስለ ተጭበረበሩ ትርፎች ሃሳብ ፣ መንስኤያቸው እና የሚያደርሱት ጉዳት እንዲሁም ስለ ተከለከለ የገንዘብ ግብይቶች ሃሳብ ትማራላችሁ።

የተጭበረበረ ትርፍን እና የሚያደርሳቸውን ጉዳት ትለያላችሁ።ስለ ተከለከሉ የገንዘብ ግብይቶች ትማራላችሁ።

ከትርፎች መካከል ደስ የሚል ፣ ጥሩ እና የተፈቀደ አለ። እንዲሁም የተጠላ ፣ መጥፎ እና የጠከለከለ አለ። አሏህ እንዲህ ይላል፡ "እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ካፈራችሁትና ከዚያ ከምድር ካወጣንላችሁ ከመልካሙ ለግሱ። መጥፎውንም ለመስጠት አታስቡ።" (ሱረቱል በቀራ 267)

በአቡ ኹረይራ (ሰ.ዐ.ወ) ሐዲስ ውስጥ ደግሞ ነብዩ እንዲህ ብለዋል፡ ‹‹በእርግጥ ሰዎች ገንዘቡን ከየት እንዳገኙት እና በተፈቀደ መንገድ ያግኙት ወይም ባልተፈቀደ መንገድ ያግኙት የማያስጨንቃቸው የሆነ ጊዜ ይመጣል።›› (ቡኻሪ 2083)

መጥፎ ገቢ

የሰዎችን ገንዘብ ያለ አግባብ መብላት ወይም በሸሪአ ህግ በተከለከለው መልኩ ገቢ ማግኘት ነው።

መጥፎ ገቢ የሚገኝባቸው መንገዶች

١
የሰዎችን ገንዘብ ያለ ፍትህ ያለ አግባብ በመብላት ነው። ይህም ያለ አግባብ የሰዎችን ገንዘብ በመንጠቅ ፣ በማጭበርበር ፣ በማታለል ፣ ያለ አግባብ ስልጣንን በመጠቀም ያለ ባለቤቱ ፈቃድ እና ስምምነት መውሰድን ሁሉ ያጠቃልላል።
٢
በሸሪአ በተከለከለው የግብይት መንገድ በአራጣ ፣ በቁማር እና የተከለከሉ ነገሮችን በመሸጥ ለምሳሌ ወይን ፣ የአሳማ ስጋ ፣ የሙዚቃ መሳሪያ እና ሌሎችም ገቢ ማግኛ መንገዶች ይይዛል።

መጥፎ ገቢ ለማግኘት የምያነሳሱ ምክኒያቶች

١
አሏህን ያለ መፍራት እና ይሉኝታ ያለመኖር፡ ከአንድ ሰው ቀልብ ላይ የአሏህ ፍራቻ እና ይሉኝታ ከጠፋ ገቢው ከተፈቀደ ወይም ካልተፈቀደ ነገር ይሁን አይሁን ለእሱ አያሳስበውም።
٢
ቶሎ ገቢ ለማግኘት መጓጓት፡ አንዳንድ ሰዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ በጣም በርከት ያለ ገንዘብ ለማግኘት የሚቋምጡ እና የሚቸኩሉ ትዕግስት የሌላቸው ናቸው። ይህም የተከለከለን ነገር እንዲበሉ ያስገድዳቸዋል።
٣
ስግብግብነት እና እርካታ አለመኖር፡ አንዳንድ ሰዎች አሏህ የሰጣቸው ህጋዊ ገቢያቸው ብዙ ቢሆንም እርካታ ግን የላቸውም። ምንም እንኳ አሏህ የከለከለው ቢሆንም ከዚህም ብዙ ይፈልጋሉ።

መጥፎ ገቢ የሚያስከትለው ጉዳት

١
የሃያሉ አሏህ ቁጣን ያመጣል ፣ የጅሃነም እሳት ውስጥ ያስገባል። አቡ ኡማማ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹የአንድ ሙስሊም ሰው መብት ምሎ የወሰደ ሰው አሏህ የጀሃነም እሳትን በእሱ ላይ ግዴታ አድርጎታል። ጀነትም ለእሱ እርም የተደረገች (የተከለከለች) ናት። አንድ ሰው ‹ቀለል ያለ ነገር እንኳ ቢሆን? ሲል ጠየቃቸው። እሳቸውም ‹‹የአረክ ዛፍ ጭራሮ (ቅርንጫፍ) ቢሆን እንኳ አሉ።›› (ሙስሊም 137)
٢
የልብ መጥቆር ፣ አሏህን ለመታዘዝ መገጣጠሚያ አካላቶቹ መስነፍ ፣ ከሪዝቅ እና ከህይወቱ በረካ መነሳት ያስከትላል።
٣
ዱአዎች ተቀባይነት ያጣሉ። አቡ ኹረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ‹‹አንድ እንዳሻው የሚጓዝ ፣ ፀጉሩ የተንጨባረረ እና በአቧራ የተሸፈነ ሰውን ጠቀሱና እጁን ወደ ሰማዩ ከፍ አድርጎ አንስቶ ዱአ አደረገ። ‹‹ጌታየ ሆይ! ጌታየ ሆይ! አለ። ምግቡ ሃራም (ያልተፈቀደ) ፣ መጠጡ ሃራም ፣ ልብሶቹ ሃራም ፣ መጠቃቀሚያዎቹ ሃራም ሆኖ ሳለ እና እንዴት ዱአው ተቀባይት ያለው ይሆንለታል? አሉ።›› (ሙስሊም 1015)
٤
በሰዎች መካከል ጠብ እና ጥላቻን ይፈጥራል እና በማህበረሰቡ ውስጥ መበታተንን ያስከትላል፡ ይህ ሰዎችን ገንዘብ ያለ አግባብ እና ያለ ፍትህ በመብላት እና በማውጣት የሚከሰት ነው። አሏህ እንዲህ አለ፡ "ሰይጣን የሚፈልገው በአስካሪ መጠጥ እና በቁማር በመካከላችሁ ጠብ እና ጥላቻን ሊያደርግ ፣ አሏህን ከማውሳት እና ከስግደት ሊያግዳችሁ ብቻ ነው።" (ሱረቱል ማኢዳ 91)

የተከለከሉ የገንዘብ ግብይት አይነቶች

١
የታወቁ የአይነት ክልከላዎች
٢
በህደት ባህሪያቸው የተከለከሉ

በአይነት የተከለከሉ ነገሮች

የተከለከሉ ሸቀጦች ለምሳሌ ሙቶ የተገኘ የእንስሳ ስጋ ፣ ደም ፣ የአሳማ ስጋ ፣ ቆሻሻ እና የረከሰ ነገር ሁሉ ናቸው። እነዚህ ነፍስ በተፈጥሮ የምትጠላቸው ነገሮች ናቸው። አሏህ እንዲህ አለ፡ "ሙሐመድ ሆይ! ንገራቸው፡ ወደ እኔ በተወረደው ውስጥ በክት ወይም ፈሳሽ ደም ወይም የአሳማ ስጋ እሱ እርኩስ ነውና ወይም በአመፅ ከአሏህ ስም ውጭ ሌላ በእሱ ላይ የተወሳበት ካልሆነ በስተቀር በሚመገበው ተመጋቢ ላይ እርም የሆነን ነገር አላገኘም። አመፀኛ እና ወሰን ያለፈ ሳይሆንም የተገደደ ሰው (ከተወሱት) ቢበላ ሃጢያት የለበትም። ጌታህ አዛኝ መሃሪ ነውና።"

በህደት ባህሪያቸው የተከለከሉ

የሸሪአን ህግ የሚጥሱ ማንኛውም የግብይት አይነቶች ናቸው። ለምሳሌ አራጣ ፣ ቁማር ፣ ማጭበርበር ፣ ደብቆ ማከማቸት ፣ ማታለል ወ.ዘ.ተ ናቸው። እንዲሁም በሰራተኞች ላይ ኢፍትሃዊ መሆንን እና ያለ አግባብ የሌሎች ሰዎችን ገንዘብ መብላትን ያጠቃልላል። እንዲህ አይነቱን ባህሪ ደግሞ ነፍስ ትመኘዋለች። በእንዲህ አይነቱ ባህሪ የተሳተፉ በቅጣት ማስተካከል የሚያስፈልገው ለእዚህ ነው። አሏህ እንዲህ አለ፡ "እነዚያ የየቲሞችን ገንዘብ በመበደል የሚበሉ በሆዳቸው ውስጥ የሚበሉት እሳት ብቻ ነው። እሳትንም በእርግጥ ይበላሉ።" (ነሳኢ 10) ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡ "(278) እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አሏህን ፍሩ። ከአራጣም የቀረውን ተው። አማኞች እንደሆናችሁ ተጠንቀቁ። (279) የታዘዛችሁትን ባትሰሩም ከአሏህ እና ከመልዕክተኛው በሆነች ጦር መወጋታችሁን እወቁ።" (ሱረቱል በቀራ 278-279)

ትምህርቱን አጠናቅቀሃል


ፈተና ጀምር