የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት የሙስሊም ቤተሰብ ደረጃ በእስልምና
አንድ ማህበረሰብ የጋራ እሴት ያላቸውን ግለሰቦች አካቶ የያዘ ነው። ከእነዚህ እሴቶች መካከል መነሻቸው ፣ ቋንቋ ፣ ታሪክ ፣ ሃይማኖት ፣ ወግ እና ስርአታቸው ይገኙበታል። እነዚህ ግለሰቦች የመጡት ከባል እና ከሚስት ጎጆ ነው። ከዚያም አዲስ ቤተሰብ የሚመሰርቱ ወንድ እና ሴት ልጆችን ያፈራሉ። ማህበረሰቡ የሚኖረው እና ቀጣይነት እንዲኖረው የሚያደርገው በዚህ መንገድ ነው።
ጥሩ የጋብቻ ህይወት ለሐገር መሰረት ነው።ሆኖምዋናው መርሆ ለቤተሰብ ትኩረት መስጠት አስፈላጊ ነው የሚለው ነው።
ምንም እንኳ የሰው ልጅ በተፈጥሮው ማህበራዊ ፍጡር ቢሆንም በማህበረሰቡ ውስጥ በመኖር ካልሆነ በቀር ምቾት አይሰጥም። አባላቶቹ ብዙ ትስስር እና ግኑኝነት ያሉት ነው። ነገርግን የተወሰኑ ፍላጎቶቹን እና ስሜቶቹን የቤተሰቡ አባላት ለሆኑት ለተወሰኑት ግለሰቦች ማዋል አለበት። ቤተሰብ በእስልምና ውስጥ አንድን ወንድ እና አንድ ሴት በህጋዊ ጋብቻ ተጣምረው ልጆችን የሚያፈሩበት የማህበራዊ ህይወት አንዱ አካል ነው።
እስልምና ለዚህ ተቋም ትኩርት ይሰጣል። ሰዎች እንዲያገቡ ጥሪ ከማድረግ ጀምሮ ፣ የልጆች መብቶች በመጠበቅ እና በቤተሰቡ አባላት መካከል ሊኖር ስለሚገባው ትስስር በመቆጣጠር እና አፅንኦት በመስጠት ያበቃል። ይህ የቤተሰብ አወቃቀር ሃያሉ አሏህ እንደሚፈልገው የሆነ እፁብ ድንቅ የሰብአዊነት ገፅታ ነው።
ቤተሰብ በእስልምና ውስጥ ያለው ደረጃ
አሏህ በወንድ እና በሴት ውስጥ አንዳቸው በአንዳቸው ላይ መፈላለግን እና መዘንበልን አድርጓል። ሆኖም በትዳር (በጋብቻ) ይህ መፈላለግ እና መዘንበል የሚፈፀምበት ፣ የሰው ልጅ ዘሩን የሚተካበት እና የሰው ዘር የሚቀጥልበት ህጋዊ መንገድ አድርጎታል። እስልምና በቅዱስ ቁርአን እና በነብዩ ሱና ውስጥ ጋብቻን ያበረታታል።
የሙስሊም ቤተሰብ የሚመሰረተው በሁለት ምሰሶዎች ላይ ነው
የስነ-ልቦና ድጋፍ
አሏህ በንግግሩ እንዳለው የልቦና መረጋጋትን ፣ ሰላምን ፣ መዋደድን እና መተዛዘንን አጠቃሎ ይይዛል።"ለእናንተም ከነፍሶቻችሁ ሚስቶችን ወደ እነሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ ፣ በመካከላችሁ ፍቅርን እና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው። በዚህ ውስጥ ለሚያስተውሉ ህዝቦች ተአምራቶች አሉ።" (ሱረቱ ሩም 21)
ቁሳዊ ድጋፍ
የጋብቻ ውሉ ቅድመ ሁኔታዎች መፈፀማቸውን ማረጋገጥ አለበት። ይህም ባለትዳሮቹ እያንዳንዳቸው ሃላፊነታቸውን እና ግዴታቸውን መፈፀማቸውን ማረጋገጥ ይዛል። ከእነዚህ ሃላፊነቶች እና ግዴታዎች ውስጥ ፍቅር ፣ እንክብካቤ ፣ ተቆራጭ ገንዘብ ፣ የቤት ውስጥ ጉዳዮችን እና ወጭዎችን መሸፈን እና የልጆችን ፍላጎት ማሟላት ወ.ዘ.ተ ናቸው።
ከዚህ በተጨማሪ ይህ ተቋም እንዳይፈርስ እና ቤተሰቡ እንዳይበተን የትዳር አጋሮቹ እንዲንከባከቡት እና ጠብቀው እንዲያቆዩት እስልምና ያበረታታል። በሁለቱ ጥንዶች መካከል መፋቀር ባይኖር እንኳ ትዳሩ እንዲቀጥል እስልምና ጥሪ የሚያደርገው ለዚሁ ነው። አሏህ እንዲህ አለ።"በመልካም ተኗኗሯቸው። ብትጠሏቸውም (ታገሱ)። አንዳችን ነገር ብትጠሉ አሏህም በእሱ ብዙ ደግ ነገርን ሊያደርግ ይችላልና።" (ሱረቱ ኒሳዕ 19)