የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት በሁለቱ ፆታዎች መካከል የግንኙነት ገደብ
የእስልምና ህግ በወንዶች እና በሴቶች መካከል ያለውን ቅርርብ ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች የሰዎች ጉዳዮች ላይ ትኩረት ይሰጣል። አሏህ ወንዶችን እና ሴቶችን የፈጠረው እርስ በእርሳቸው እንዲፈላለጉ እና እንዲሳሳቡ አድርጎ ነው። የዚህ ስበት እና መፈላለግ ውጤት ህጋዊ የሚሆነው በጋብቻ ብቻ ነው። የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹ከእኔ በኋላ ለወንዶች ከሴቶች የበለጠ የከፋ ፈተናን አልተውኩም።›› (ቡኻሪ 5096 ፣ ሙስሊም 2741)
በወንድ እና በሴት መካከል ባለው ቅርርብ በጣም የከፋው እና አደገኛው ነገር ዝሙት ላይ መውደቅ ነው። ሸሪአ ይህን ስርአት ማጣት እና ግብረገብነት የጎደለው ተግባር መከላከል ብቻ ሳይሆን ወደ እሱ መቅረብንም በጥብቅ ከልክሏል። ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡ "ዝሙትን አትቅረቡ። እሱ በእርግጥ መጥፎ ስራ ነውና። መንገድነቱም ከፋ!" (ሱረቱ ኢስራዕ 32) ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አለ፡ ‹‹የአይን ዝሙት (የተከለከለን ነገር) ማየቱ ነው። የምላስ ዝሙት ማውራቱ ነው። እንዲሁም የውስጥ ፍላጎት እና ምኞቶች ናቸው። ሀፍረተ ገላዎች ይህን ሁሉ ይመሰክራሉ ወይም ይክዳሉ።›› (ቡኻሪ 6243 ፣ ሙስሊም 2657)
ማንኛውንም ስህተት እና ጥመት ለማስቀረት ሲባል እና መጥፎ ውጤት ከማስከተሉ በፊት በሴቶች እና በወንዶች ቅርርብ ላይ አስፈላጊ ሸሪአዊ ቁጥጥሮችን እና ገደቦችን አስቀምጧል። ለምሳሌ መግዛት ፣ መሸጥ እና ሌሎች የተፈቀዱ ግብይቶች እንዲሁም የግድ አስፈላጊ በሚሆን ጊዜ ሴት ዶክተሮች በማይኖሩበት ጊዜ አንዲትን ሴት ማከም ወ.ዘ.ተ ናቸው። ከእነዚህ ቁጥጥሮች እና ገደቦች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡-
እይታን መስበር
መነካካትን ወይም በእጅ መጨባበጥን ማስወገድ
ሴት ጋር ብቻውን ተገልሎ መቀመጥ
ሙስሊም ሴቶች ከወንዶች ጋር የግድ መቀራረብ በሚያስፈልግበት ጊዜ ሊከተሏቸው እና ሊጠብቋቸው የሚገቡ ደንቦች እና ድንበሮች አሉ።
ሙስሊም ሴት በመጀመሪያ የአሏህን ትዕዛዝ በማክበር እና ከዚያም ወንዶች እንዲያከብሯት እና በንግግራቸው ፣ በድርጊታቸው እና በእይታቸው እንዳይጎዷት ህጋዊ የሸሪአ የአለባበስ ስርአትን መከተል አለባት። አሏህ እንዲህ አለ፡"ለምዕመናትም ንገራቸው! አይኖቻቸውን ይከልክሉ። ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ። ጌጣቸውንም ከእሷ ግልፅ ከሆነው በስተቀር አይግለጡ። ጉፍታዎቻቸውንም በአንገታቸው ላይ ያጣፉ።" (ሱረቱ ኑር 31) አሏህ እንዲህም ብሏል፡ "አንተ ነብይ ሆይ! ለሚስቶችህ ፣ ለሴት ልጆችህም ፣ ለምዕናን ሚስቶችም መከናነቢያቸውን በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው። ይህ እንዲታወቁ እና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመሆን በጣም የቀረበ ነው። አሏህ መሃሪ አዛኝ ነው።" (ሱረቱ አህዛብ 59)