መማርዎን ይቀጥሉ

ሎግ ኢን አላደረክም
መማር ለመጀመር፣ እድገትን ለመከታተል፣ ነጥቦችን ለመሰብሰብ እና ወደ ውድድር ለመግባት አሁኑኑ በታ ፕላትፎርም ይመዝገቡ፡ ከተመዘገቡ በኋላ ለሚማሯቸው ርዕሶች የኤሌክትሮኒክስ ሰርተፍኬት ይደርስዎታል።

የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል

ትምህርት ፍች

በዚህ ትምህርት ውስጥ ስለ ፍች ሃሳብ እና ከእሱ ጋር ተያያዥ ስለሆኑ የሸሪዐህ ውሳኔዎች ትማራላችሁ።

1 የፍች ሃሳብን ትረዳላችሁ።2 ከፍች የህግ ውሳኔ ጋር በተያያዘ ስለ እስልምና ውበት ታውቃላችሁ።3 የፍችን ጥቅሞች እና ጉዳቶች ታውቃላችሁ።4 ስለ ፍች አይነቶች ትማራላችሁ።5 የመጠበቂያ ጊዜ (ኢዳ) ሃሳብን ታውቃላችሁ።

የተከበረ ቃልኪዳን

እስልምና የቤተሰብ ህይወትን እና የጋብቻ ግኑኝነትን በቁርጠኝነት መጠበቅ ላይ ትኩረት ሰጥቷል። ቅዱስ ቁርአን ይህንንም የተከበረ ቃልኪዳን ሲል ገልፆታል። ይህ የተከበረ ቃልኪዳን የጋብቻ ውል ነው።

እስልምና የጋብቻ ግኑኝነትን ስለ መጠበቅ ጠቀሜታ አፅንኦት የተሰጠበትማሳያ ውስጥ ባሎች ሚስቶቻቸውን እንዲጠብቁ እና እንዳይፈሯቸው ያዛል። ምንም እንኳ ቢጠሏቸውም እና በእነሱ ውስጥ መጥፎ ነገር ባዩም ማለት ነው። አሏህ እንዲህ አለ፡ "በመልካም ተኗኗሯቸው። ብትጠሏቸውም ታገሱ። አንዳችን ነገር ብትጠሉ አሏህም በእሱ ብዙ ደግ ነገርን ሊያደርግ ይችላልና።" (ሱረቱ ኒሳዕ 19)ከዚህ በተጨማሪ የተከበረው ቃልኪዳን እንዳይሸረሸር እስልምና በሁለቱ ጥንዶች መሃል ጥላቻ መፍጠርን በጥብቅ አስጠንቅቋል። አቡ ኹረይራ (ረ.ዐ) እንሳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡ ‹‹አንዲት ሴተር በባሏ ላይ ያነሳሳ ሰው ከእኛ አይደለም።›› (አቡዳውድ 2175) ማነሳሳት ማለት ማታለል እና ማበላሸት ነው።

የእስልምና እውነታ

እስልምና የጋብቻ ግኑኝነት እንዲቀጥል ቢፈልግም እውነተኛ ሃይማኖት ነውና ከሰዎች ተፈጥሮ ጋር የሚፃረር ነገርን አያዝም ፣ ፍላጎቶቻቸውን አይጨቁንም አያስገድድም። ይልቁንም ሁኔታዎቻቸውን ፣ ስሜቶቻቸውን እና ፍላጎቶቻቸውን ከግምት ውስጥ ያስገባል።የሆነ ጊዜ ፍች አስፈላጊ እና አስገዳጅ እንደሚሆንም ያውቃል። ለዚህም ነው የፍች መፈቀድ ትልቅ ጥበብ ነው የምንለው። ምንም እንኳ ከባድ እና መጥፎ ቢሆንም ማለት ነው።

የፍች ህጋዊነት

የፍች ህጋዊነት በቅዱስ ቁርአን እና በነብዩ ሱና ውስጥ ብዙ ቦታ ላይ ተጠቅሷል። የቁርአን አንቀፆች እና ሐዲሶች ይህ የህግ ውሳኔ እና ሊከተሏቸው የሚገቡ ስነ-ስርአቶችን በተደራጀ መልኩ ያብራራል። ከዚህ በተጨማሪ አንደኛው የቁርአን ምዕራፍ አጦላቅ (ፍች) የሚል ርዕስ ተሰጥቶታል።

በቋንቋ ደረጃ የፍች ትርጉም

የጋብቻ ትስስርን መፍታት ማለት ነው።

በሸሪዐህ የፍች ትርጉም

የጋብቻ ትስስርን ወዲያውኑ ወይም ዘግየት ካሉ በኋላ የተወሰኑ ቃላትን በመጠቀም መፍታት ነው። እነዚህ ቃላቶች ‹‹ፍች›› የሚለው ግልፅ አጠቃቀም እራሱ ወይም ዘይቢያዊ አገላለፅ ‹‹መለያየት›› ፣ ‹‹የተከለከለ›› ፣ ነፃ ብያለሁ›› እና ሌሎችም ናቸው። ከዚህ በተጨማሪ ፅሁፉ ወይም ምልክቶች ልክ እንደ ንግግር ተመሳሳይ ሚናን ይጫወታሉ። ከፍች አገላለፅ ‹‹አፍርሰናል›› እና ‹‹ተለያይተናል›› ማለት ይገኝበታል።

የፍች ጥቅሞች

١
1 በመጀመሪያው ቤተሰብ ውስጥ የሌለውን ነገር በማላቀቅ ሁለት አዲስ ቤተሰቦችን በጠንካራ መሰረት ላይ ለማቆም መንገድ ይጠርጋል። የአሏህ ቸርነት ሰፊ ነው። ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡ "ቢለያዩም አሏህ ሁሉንም በችሮታው ያብቃቃቸዋል። አሏህም ችሮታው ሰፊ ጥበበኛ ነው።" (ሱረቱ ኒሳዕ 130)
٢
2 በጥላቻ እና በቅሬታ የተሞላ ህይወት መቀጠል የሚያስከትለውን ትልቅ ክፋት ይከላከላል። ይህ ትልቅ ክፋት መፈፀምን ሊያስከትል ይችላል። አሏህ ይጠብቀን!
٣
3 ከመጀመሪያው ጋብቻ ትምህርት ይወስዱበታል። ብዙ ነገሮችን መለስ ብሎ ለማሰብ ፣ የእራስን ስህተት ለመለየት ፣ ችግሮችን ለመፍታት እና ሁለተኛው ጋብቻ ስኬታማ ይሆን ዘንድ እራስን ለማሻሻል ይረዳል።
٤
4 ለፍች የሚያበቃው መቃቃር ፣ ጥላቻ ግጭት እና መጥፎ ባህሪ እንዲያበቃ ያደርጋል።
٥
5 ሰላም እና መረጋጋት በሌለበት ቤት ውስጥ መኖር ልጆች ላይ ብዙ ጉዳት ያስከትላል። ሆኖም የቤተሰቡን አባላት ከእንዲህ አይነቱ የስነልቦና ጉዳት እና ከስብዕና ውድቀት ይታደጋል።

ፍች የሚያስከትለው ጉዳት

١
1 ቤተሰብን ይበትናል፤ በመዋደድ እና በመተዛዘን መሰረት ላይ መቆም የነበረበት ጎጆ ይፈርሳል።
٢
2 ከፍች በኋላ ወላጆቹ በተገቢው መንገድ መልካም ምግባር የማይፈፅሙ ከሆነ ፣ አንዳቸው በአንዳቸው ላይ ጠላት ሆነው ልጆቹ ለእኔ ይገባኛል የሚል አተካራ ውስጥ ቢገቡ ወይም ልጆቹን እንደ ግፊት መፍጠሪያ ዘዴ የሚጠቀሙባቸው ከሆነ ልጆቹ ለስነልቦና እና ለባህሪ ችግር ይጋለጣሉ። የዚህ ውጤትም እስከ ህይወታቸው ፍፃሜ ድረስ አብሯቸው ይኖራል።
٣
3 በባል እና በሚስት መካከል ያለ ጥላቻ እና መቃቃር ወደ ቤተሰባቸው ሊለጠጥ የሚችል ከሆነ ሰፊ ጥላቻ እና መቃቃርን ያስከትላል። ነገርግን ይህ እስልምና ከሚፈልገው በተቃራኒ ነው። እስልምና የሚፈልገው ማህበረሰቡ አንድ እዲሆን እና እንዲዋሃድ ነው።

የፍች አይነቶች

١
1 ሊመለስ የሚችል ፍች
٢
2 ቀላል በታኝ ፍች
٣
3 ከባድ በታኝ ፍች

ሊመለስ የሚችል ፍች

ባል በሚስቱ ላይ አንዴ እና ሁለቴ ፈትቸሻለሁ ብሎ በመናገሩ ምክኒያት የሚከሰት ፍች ነው። ባል ሚስቱ በመጠበቂያዋ ጊዜ ውስጥ እስከሆነች ድረስ ሃሳብ አስተያየቷን ሳይጠይቅ እና ሌላ የጋብቻ ውል ሳይፈፅም መልሶ ሊወስዳት ይችላል።

ቀላል ብተና ፍች

ይህ አይነቱ ፍች የሚከሰተው ባል አንድ ወይም ሁለት ጊዜ ፈትቸሻለሁ ብሎ የመጠበቂያዋ ጊዜ (ኢዳዋ) ካለፈ ነው። በእንዲህ አይነቱ ጉዳይ ባል ሚስቱን በቀላሉ መልሶ ይዞ ሊሄድ አይችልም። የግድ አዲስ የጋብቻ ውል ከእሷ ጋር መፈፀም አለበት።

ትልቅ የማይሻር ፍች

ይህ ሶስተኛው የፍች አይነት ነው። ባል ከሚስቱ ጋር አብረው መኖር የሚችሉት አዲስ የጋብቻ ውል በመፈፀም ወይም ሌላ ባል ካገባች በኋላ ቢፈታት ወይም ቢሞት እንደገና ጥሎሽ ሰጥቶ ብቻ ነው።

ሊመለስ የሚችል ፍች ፣ ቀላል ፍች እና ትልቅ ፍች ጋር የተያያዙ አህካሞች (የህግ ውሳኔዎች) ጥበብ የእስልምና ህግ ድንጋጌ ውበት ያሳያል። ሆኖም ፍች የመንገዱ ማብቂያ አይደለም። ሊመለስ በሚችል ፍች አጢነው እና የሚያስከትለውን ውጤት ተረጋግተው አስበውእና ችግሩን አስወግደው የመመለስ እድል አላቸው። ልክ እንደዚሁ ሴቷ ከሁለተኛ ባሏ በትልቅ ፍች ከተፈታች በኋላ ሁለቱ ወገኖች አብረው ለመኖር ካሰቡ እና ከወሰኑ ያጥሩ ምርጫ ነው። ብዙ ጊዜ ይህ አይነቱ ልምድ ትዳርን በጠንካራ መሰረት ላይ ለማቆም ምክኒያት ነው።

የመጠበቂያ ጊዜ (ኢዳ)

ሁለት ጥንዶች በፍች ወይም በሞት ምክኒያት ከተለያዩ በኋላ ሴቲቷ ነፍሰጡር አለመሆኗን ለማረጋገጥ የምትጠቀምበት እና በዚህ ጊዜ የማታገባበት ወቅት ነው።

ሴቷ መጠበቂያ ጊዜዋን የባሏ ቤት ውስጥ ሆና የማሳለፍ መብት አላት።እሱም ወጭዎቿንሁሉ የመሸፈን ሃላፊነት አለበት። ከዚህ በተጨማሪ በመጠበቂያ ጊዜዋ ላይ ሆና እያለ ባሏ ቢሞት ንብረቱን የመውረስ መብት አላት። በመጠበቂያ ጊዜዋ ከወንድ ጋር መተጫጨት ለእሷ የተከለከለ ነው።

ከመጠበቂያ ጊዜ ህጋዊነት ጀርባ ያለው ጥበብ

١
1 ለአሏህ አገልጋይ የመሆን ማሳያ ነው። ምክኒቱም ሙስሊም ወንድ እና ሙስሊም ሴት ጉዳያቸውን ለአሏህ የሚሰጡ ናቸው። አንድን ነገር በወሰነ ጊዜ ለመታዘዝ እና ባርነታቸውን ለማሳየት ይቻኮላሉ።
٢
2 የሴቷ ማህፀን ፅንስ የሌለው እና እርግዝና ላለመኖሩ ማረጋገጫ ነው።
٣
3 ባል የተፈታች ሚስቱን ለመመለስ ሰፊ ጊዜ እንድሰጠው ነው።
٤
4 ለሟች ባል የማዘኛ ጊዜን ይሰጣል።

ትምህርቱን አጠናቅቀሃል


ፈተና ጀምር