የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት ሽያጭ
የሽያጭ ትርጉም
በቋንቋ ደረጃ ሽያጭ ማለት አንድን ነገር በሌላ መለወጥ ነው። በህግ ደረጃ ደግሞ አንድ ሸቀጥ ከሌላ ሰው መገብየት ወደ ሶስተኛ ወገን መስተላለፍ ነው።
የሽያጭ ሁክም
ሽያች በቁርአን ፣ በሱና እና በኡለማኦች ስምምንት መሰረት የማይሻር ውል ነው። አሏህ እንዲህ አለ፡ "አሏህ ንግድን ፈቅዷል።" (ሱረቱል በቀራ 275)
የሽያጭ ጥበብ
1 የሰው ልጆች ሌሎች ሰዎች ያለ ክፍያ የማይሰጧቸው የሆኑ እንደ ምግብ ፣ መጠጥ ፣ ልብስ ፣ መጠለያ ቤት እና ሌሎች ሸቀጦችን ይፈልጋሉ። ሆኖም ሁለቱ ወገኖች ፍላጎቶቻቸውን የሚያሟሉት በሽያጭ ነው። ሻጩ የእቃውን የዋጋ ተመን ያገኛል። ገዡ ደግሞ የፈለገውን ሸቀጥ ያገኛል።
2 ሰዎች ህይወታቸው በተሻለ መንገድ እንዲመሩ ይረዳቸዋል። ምክኒያቱም የሰው ልጆች ፍላጎቶቻቸውን የሚያሟሉበት ምናልባት በሽያጭ ብቻ ነውና።
3 ሌብነትን ፣ ማጭበርብርን ፣ ስልጣንን ተገን አድርጎ ገንዘብብ መመዝበርን እና ሌሎች መሰል ተግባራትን ይከላከላል። ምክኒያቱም የሰው ልጆች በግዥ ፍላጎቶቻቸውን የሚያሟሉበት እድል አለና ነው።