መማርዎን ይቀጥሉ

ሎግ ኢን አላደረክም
መማር ለመጀመር፣ እድገትን ለመከታተል፣ ነጥቦችን ለመሰብሰብ እና ወደ ውድድር ለመግባት አሁኑኑ በታ ፕላትፎርም ይመዝገቡ፡ ከተመዘገቡ በኋላ ለሚማሯቸው ርዕሶች የኤሌክትሮኒክስ ሰርተፍኬት ይደርስዎታል።

የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል

ትምህርት ትልቁ ርክሰት እና መታጠብ

እራስን ከትልቅ ርክሰት ለማንጻት እስልምና ትጥበትን ደንግጓል። በዚህ ትምህርት ስለ ትጥበት ምክንያቶች እና እራስዎን በትጥበት እንዴት ከትልቁ ርክሰት ማፅዳት እንደሚችሉ ይማራሉ

  • የመታጠብ አስገዳጆችን ማወቅ።
  • ከትልቁ ርክሰት እንዴት ማፅዳት እንደሚቻል ማወቅ።

ትጥበትን ግድ የሚያደርጉ ነገሮች

ትጥበትን ግድ የሚያደርጉ ነገሮች። እነኚህ ነገሮች በአንድ ሙስሊም ካሉበት ሠላትን ከመስገድና ጠዋፍ ከማድረግ በፊት ገላውን መታጠብ ግዴታ የሚያድርጉ ነገሮች ናቸው፡፡ ይህ ሰው ከመታጠቡ በፊት ትልቁ ሐደስ አለበት ይባላል፡፡

1 የፍቶት ፈሳሽ ማውጣት

የፍቶት ፈሳሽ (የዘር ፍሬ - መኒይ)፣ በንቃትም ሆነ በእንቅልፍ ውስጥ፣ በእርካታ መልክ እየተገፋተረ መውጣት፡፡ የፍቶት ፈሰሽ (መኒይ) የሚባለው በጣም በስሜት ውስጥ ሲገባና እርካታ ሲሰማ ከብልት የሚወጣ ነጭና ትኩስ ፈሳሽ ነው፡፡

2 የግብረ ስጋ ግንኙነት

የግብረ ስጋ ግንኙነት፡ ይህ ማለት የፍቶት ፈሰሽ (መኒይ) ባይፈስም፣ የወንድ ብልት በሴቷ ብልት ውስጥ ማስገባት ነው፡፡ የወንዱ ብልት ጫፍ ሴቷ ብልት ውስጥ መግባቱ ብቻ ትጥበትን ግዴታ ያስደርጋል፡፡

3 የወር አበባና የወሊድ ደም መፍሰስ

የወር አበባ ደም የሚባለው፣ በየወሩ ሴቶች የሚፈሳቸው ተፈጥሯዊ ደም ነው፡፡ እንደ ሴቶቹ ተፈጥሯዊ ልዩነት ሰባት ቀናት ወይም ከዚያ በታች ወይም ከዚያ በላይ ይፈሳል፡፡ የወሊድ ደም ደግሞ በመውለዳቸው ምክንያት ከሴቶች የሚወጣ ደም ሲሆን ለተወሰነ ቀናት ይቆያል፡፡

የወር አበባና የወሊድ ሴቶች ጾምና ሶላት

የወር አበባና የወሊድ ደም ላይ ያሉ ሴቶች፣ ደሙ በሚፈስባቸው ቀናት የጾምና የሠላት ግዴታ ይነሳላቸዋል፡፡ ከደሙ ሲጸዱ፣ ጾሙን ይከፍላሉ ሠላቱን ግን አይከፍሉም፡፡

በወር አባበ ወሊድ ደም ላይ ያለችን ሴት ግብረስጋ ግንኙነት መድረግ።

በነኚህ ቀናት ውስጥ ባሎቻቸው ሊገናኟቸው አይፈቀድላቸውም፡፡ ከግንኙነት መለስ ባለ ነገር ግን መደሰት ይችላሉ፡፡ ሴቶቹ ደሙ ከቆመላቸው በኋላ ገላቸውን መታጠባቸው የግድ ይሆናል፡፡ አላህ (ሱ.ወ)፡- «ሴቶችንም በወር አበባ ጊዜ ራቋቸው፡፡ንጹህ እስከሚኾኑም ድረስ አትቅረቧቸው፡፡ ንጹህ በኾኑም ጊዜ አላህ ካዘዛችሁ ስፍራ ተገናኟቸው፡፡» ይላል፡፡ (አል በቀራ 222) «ንጹህ በኾኑም ጊዜ » ማለት ገላቸውን በታጠቡ ጊዜ ማለት ነው፡፡

አንድ ሙስሊም ከጀናባ ወይም ከትልቁ ሐደስ የሚጠራው እንዴት ነው?

አንድ ሙስሊም መጽዳትን በልቡ አስቦ ገላውን በሙሉ በውሃ ከታጠበ፣ ከትልቁ ሐደስ ይጸዳል፡፡

የነቢዩ ሰ/ዐ/ወ/ ትጥበት

ይህ ትጥበት የተሟላ የሚኾነው ግን፣ ከተጸዳዳ በኋላ የሚያደርገውን ዓይነት ኢስቲንጃ አድርጎ፣ውዱእን አስከትሎ፣ከዚያም ሰውነቱን በጠቅላላ በውሃ አዳርሶ ሲታጠብ ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ትጥበት ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የአስተጣጠብ ፈለግ ጋር ስለሚገጣጠም ከምንዳ አንፃር ከፍተኛው ነው፡፡

ትጥበት ውዱእን ይሸፍናል?

አንድ ሙስሊም ከጀናባ ሲታጠብ ትጥበቱ ከውዱእ ያብቃቃዋል፡፡ ከትጥበቱ በተጨማሪ ውዱእ ማድረግን አይገደድም፡፡ በላጩ ግን፣ በነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ) የአስተጣጠብ ፈለግ መሰረት ወዱእንም ያካተተ ትጥበት መታጠብ ነው፡፡

ትምህርቱን አጠናቅቀሃል


ፈተና ጀምር