መማርዎን ይቀጥሉ

ሎግ ኢን አላደረክም
መማር ለመጀመር፣ እድገትን ለመከታተል፣ ነጥቦችን ለመሰብሰብ እና ወደ ውድድር ለመግባት አሁኑኑ በታ ፕላትፎርም ይመዝገቡ፡ ከተመዘገቡ በኋላ ለሚማሯቸው ርዕሶች የኤሌክትሮኒክስ ሰርተፍኬት ይደርስዎታል።

የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል

ትምህርት የፍጥራ ህጎች

አላህ ሰውን የፈጠረው በደራባቸው ቁጥር የበለጣ የሚያሳምሩት ነገሮችን በገላው ላይ ፈጠረለት። በዚህ ትምህርት ስለ ፍጥረህ ሱና እና ብያኔዎቹን ትማራለህ።

  • የፍጥራ ሱናን ማወቅ። 
  • የፍጥራ ሱናን ብይን ማወቅ።

ተፈጥሯዊ ፈለጎች

ተፈጥሯዊ ፈለግ ማለት አላህ (ሱ.ወ) የሰው ልጅን የፈጠረበት መገለጫዎች ማለት ነው፡፡ አንድ ሙስሊም እነኚህን ነገሮች በመፈፀሙ ሙሉዕ የሚሆንባቸው ናቸው፡፡ ይህን በማድረጉ ያማረ ገጽታና የተዋበ ግርማ ሞገስ ይኖረዋል፡፡ ስለሆነም ኢስላም እነኚህን የውበትና የቁንጅና መሰረት የሆኑ ጉዳዮችን ልዩ ትኩረት በመስጠት አንድ ሙስሊም ውጫዊና ውስጣዊ ማንነቱም ያማረ እንዲያደርግ አዟል፡፡

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹አምስት ነገሮች ተፈጥሯዊ መዋቢያዎች ናቸው፤ መገረዝ፣ በብልት ዙሪያ የሚበቅልን ጸጉር መላጨት፣ ቀድሞ ቀመስን ማሳጠር፣ ጥፍርን መቁረጥ፣ እና በብብት ስር ያለን ጸጉር መንጨት፡፡›› (አል ቡኻሪ 5552/ ሙስሊም 257) ነቢዩ የአላህ ሶላትና ሰላም በእሱ ላይ ይሁን እንድህ አሉ ፡- ‹‹አሥሩ ተፈጥሯዊ መዋቢያዎች ናቸው፡- ቀድሞ ቀመስን መቁረጥ፣ ፂምን ማሳደግ፣ ጥርስን መፋቅ፣ ውሃ በአፍንጫ መሳብ፣ ጥፍር መቁረጥ፣አንጓዎችን ማጠብ፣ ብብት መንቀል፣ የብልት ዙሪያ ጸጉርን መላጨት፣ በመጸዳጃ ውሃን መጠቀም” (ዛጋቢው ኣሉ)፡- አስረኛውንም ረሳሁት፣ አፍን መጉመጥመጥ ካልሆነ በስተቀር (ሙስሊም 261)።

ግርዛት፡

ይህ በብልት ጫፍ ላይ የሚገኝ ቆዳን ማስወገድ ወይም መቁረጥ ነው፡፡ በተለምዶ ይህ ቆዳ እንዲወገድ የሚደረገው በመጀመሪያዎቹ የአራስነት ቀናት ነው፡፡ ግርዛት ለወንዶች ተወዳጅና ከተፈጥሯዊ ፈለጎች መካካል ነው፡፡ ከጤናም አንጻር በርካታ ጥቅሞች አሉት፡፡

ኢስቲሕዳድ፡

ይህ በብልት ዙሪያ ያለን ጸጉር መላጨት ወይም በፈለገው መንገድ ማስወገድ ነው፡፡

ቀድሞ ቀመስን ማሳጠር፡

ቀድሞ ቀመስን ባለበት መተው የተፈቀደ ቢሆንም የተወደደ ግን አይደለም፡፡ ነገር ግን አንድ ሙስሊም ቀድሞ ቀመሱን ከተወው እጅግ በጣም እስኪረዝም ድረስ መተው የለበትም ሊከረክመውና ሊያሳጥረው ይገባል፡፡

ጺምን ማሳደግ፡

ኢስላም ጺም ማሳደግን ያበረታታል፡፡ ጺም የሚባለው በአገጭና በጉንጮች ላይ የሚበቅል ጸጉር ነው፡፡ ጺምን ማሳደግ ማለት ባለበት መተውና አለመላጨት ነው፡፡ ይህ ደግሞ የነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) ፈለግ መከተል ነው፡፡

ጥርስን መፋቅ

ጥርስን ለማጽዳት በአራክ እንጨት ወይም ሌላ ነገር መጠቀም ማለት ነው፤ ይህም ተፈላጊ ነው

ጥፍሮችን መቁረጥ

ሙስሊሙ ለቆሻሻ እንዳይጋለጥ ጥፍሩን በየግዜው ማሳጠር አለበት።

ብብት መንቀል

ሙስሊሙ ምንም አይነት መጥፎ ጠረን እንዳይወጣ የብብት ፀጉርን በመንቀል ወይም በሌላ ማንኛውም ማስወገጃ ማስወገድ አለበት።

የ ጣት መታጠፍያዎችን ማጠብ

አንጓዎች በጣቶቹ ላይ ያሉ መታጠፊያዎች ናቸው እነሱን ማጠብ ተፈላጊ ነው

ዉሃን መጠቀም፤ ኣፍን መጉመጥመጥና በአፍንጫ መሳብ

ውሃን መጠቀም ከመጸዳዳት በኋላ በዉሃ ማፅዳት ማለት ነው፡ ስለእነዚህ ሦስቱ ደግሞ በመጸዳዳት በዉሃ መጠቀምና ውዱእ ትምህርቶች ውስጥ አስቀድመን ተናግረናል።

ትምህርቱን አጠናቅቀሃል


ፈተና ጀምር