መማርዎን ይቀጥሉ

ሎግ ኢን አላደረክም
መማር ለመጀመር፣ እድገትን ለመከታተል፣ ነጥቦችን ለመሰብሰብ እና ወደ ውድድር ለመግባት አሁኑኑ በታ ፕላትፎርም ይመዝገቡ፡ ከተመዘገቡ በኋላ ለሚማሯቸው ርዕሶች የኤሌክትሮኒክስ ሰርተፍኬት ይደርስዎታል።

የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል

ትምህርት የሱራ አል ፋቲሃ ትርጉም

ሱረቱል ፋቲሀን መቅራት ከሶላት ዋና ዋና ምሰሶዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን ከሱ ውጪ ሶላት ትክክል አይሆንም በዚህ ትምህርት የዚህን ታላቅ ሱራ አንቀጾች ትርጉም ትማራለህ።

  • የፋቲሃ ሱራ አንቀጾችን ትርጉም ማወቅ

የፋቲሓ ምዕራፍ ትርጉም

ሱረቱል ፋቲሀን መቅራት ከሶላት ዋና ዋና ምሰሶዎች አንዱ ሲሆን ሶላት በርሷ እንጂ ሙሉ አትሆንም.

አላህን በባሕሪያቱ፤በተግባራቱ፣ በግልጽና ስውር ፀጋዎቹ በሙሉ ከውዴታና ከማላቅ በመነጨ መልኩ አመሰግነዋለሁ ማለት ነው፡፡ ጌታ(ረብ)፡ የሁሉ ፈጣሪ፤ ባለቤት፤ አስተናባሪና ባለ ጸጋ የሆነ ጌታ ማለት ነው፡፡ ዓለማት፡ የሚባለው ደግሞ ማንኛውም ከአላህ ባሻገር ያለ፣ የሰው፣ የጅን፣ የመላእክት፣ የእንሰሳትና የተቀሩት ፍጡራንን የሚገልጽ ቃል ነው፡፡

እነኚህ ከአላህ የተዋቡ ስሞች መካከል ሁለት ስሞቹ ናቸው፡፡ ‹‹ርኅሩኅ›› ማለት ሁሉን ነገር የሚያዳርስ የሆነ ርኅራኄ ባለቤት ማለት ነው፡፡ ‹‹አዛኝ›› የሚለው ቃል ደግሞ ምእመናን ባሮቹን ብቻ የሚደርስ በሆነ የርኅራኄ ባህሪ የሚገለፅ ማለት ነው፡፡

የፍርዱና የግምገማው ቀን ባለቤትና አስተናባሪ ማለት ነው፡፡ ይህ አንቀጽ የመጨረሻውን ቀን ያስታውሳል፤ በመልካም ስራ ላይም ያበረታታል፡፡

ጌታችን ሆይ! እኛ አምልኮን ላንተ ብቻ እንሰጣለን፤ በየትኛውም የአምልኮ ዓይነት ካንተ ጋር ሌላን አካል አናጋራም፤ በማንኛውም ጉዳያችን ላይ ካንተ ብቻ እርዳታና እገዛን እንፈልጋለን፤ እያንዳንዱ ጉዳያችን በአንተ እጅ ነው፤ ከርሱ የቅንጣት ታክልም ሌላ አካል ባለቤትነት የለውም፡፡ ማለት ነው፡፡

ቀጥተኛውን መንገድ አመላክተን፤ አቅጣጨን፤ ግጠመን፤ ካንተ እስከምንገናኝ ድረስ በርሱ ላይም አጽናን ማለት ነው፡፡ ቀጥተኛው መንገድ ኢስላም ነው፡፡ እርሱም ግልጽ፣ ወደ አላህ ውዴታና ወደ ጀነት የሚያደርስ ወይም የሚወስድ መንገድ ነው፡፡ እርሱ ያ የነብያትና የመልዕክተኞች መደምደሚያ የሆኑት ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የጠቆሙት መንገድ ነው፡፡ በርሱ ላይ በመጽናት እንጂ ለሰው ልጅ ስኬትና ደስታ ሊገኝ አይችልም፡፡

የእነዚያን ቀጥተኛውን መመሪያ ያደልካቸውንና በሱም ላይ ያጸናሃቸውን ሰዎች፣ ማለትም የነብያትንና የፃድቃንን መንገድ ምራን ማለት ነው፡፡ እነሱ በርግጥ እውነትን አውቀው የተከተሉ ናቸው፡፡አንተ ከተቆጣህባቸውና ከተናደድክባቸው ሰዎች መንገድ አርቀን፤ ሰውረን፤ ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም እነርሱ ሐቅን አውቀው አልተገበሩትም፡፡ ከተሳሳቱት ሰዎችም መንገድ ሰውረን፤ አርቀን፤ ማለት ደግሞ፣ ካለማወቃቸው የተነሳ ወደ እውነት ያልተመሩ ሰዎችን፡፡

የ ፋቲሃ ም እራፍ ንባብ አዳምጥ

ትምህርቱን አጠናቅቀሃል


ፈተና ጀምር