የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት የሮመዳን ጾም
አላህ (ሱ.ወ) ሙስሊሞች በአመት አንድ ወርን እንዲጾሙ ግዳጅ አድርጎ ደንግጓል፡፡ እሱም የተባረከውን የረመዳንን ወር ነው፡፡ አራተኛ የኢስላም ማዕዘንና ታላቅ መሰረት አድርጎታል፡፡ አላህ (ሱ.ወ)፡- ‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ ጾም በነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት (ሕዝቦች) ላይ እንደተፃፈ በናንተም ላይ ተፃፈ (ተደነገገ) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡›› ይላል፡፡ (አል በቀራ 183)
ጾም በኢስላም ያለው ትርጉም፡ ጎሕ ከቀደደበት ሰዓት ጀምሮ፣ ፀሐይ እስክትጠልቅ (የመግሪብ ሠላት አዛን የሚባልበት ወቅት) ድረስ ከምግብ፣ ከመጠጥ፣ ከግብረ ስጋ ግንኙነትና ከሌሎችም ጾምን ከሚያበላሹ ነገሮች እራስን በመቆጠብና በማገድ አላህን መገዛት ነው፡፡
የረመዳን ወር በላጭነት
አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡፡-‹‹(እንድትጾሙ የተፃፈባችሁ) ያ በርሱ ውስጥ ለሰዎች መሪ፣ ከቅን መንገድና (ውነትን ከውሸት) ከሚለዩም ገላጮች (አንቀጾች) ሲሆን ቁርኣን የተወረደበት የረመዳን ወር ነው፡፡ ከናንተም ወሩን ያገኘ ሰው ይጹመው፡፡›› (አልበቀራ 185)
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ረመዳን ሲገባ የጀነት በሮች ይከፈታሉ፤ የጀሀነም በሮች ይዘጋሉ፤ ሰይጣናት ይታሰራሉ፡፡›› (አል ቡኻሪ 3103/ ሙስሊም 1079) አላህ (ሱ.ወ) መልካምን በመሥራትና ከመጥፎ በመራቅ ባሮቹ ወደርሱ የሚመለሱበትን ሁኔታ አመቻችቷል፡፡
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹በእምነትና አላህ ዘንድ ያለውን ምንዳ በማሰብ የረመዳንን ወር የጾመ፣ ቀደም ሲል የሠራው ወንጀል ይማርለታል፡፡›› (አል ቡኻሪ 1910 /ሙስሊም 760) ‹‹በእምነትና አላህ ዘንድ ያለውን ምንዳ በማሰብ በረመዳን ወር (ተራዊሕና ተሃጁድን በመስገድ) የቆመ ሰው ቀደም ሲል የሰራው ወንጀል ይማርለታል፡፡›› (አል ቡኻሪ 1905/ ሙስሊም 759)
ይህች ሌሊት አላህ (ሱ.ወ) በመጽሐፉ፣ በዚች በርሷ ውስጥ የሚሠራ መልካም ሥራ፣ ለረዥም ዓመታት ከሚሠራ መልካም ሥራ እንደሚሻልና እንደሚበልጥ የተናገረላት ነች፡፡ አላህ (ሱ.ወ):- ‹‹መወሰኛይቱ ሌሊት ከሺህ ወር በላጭ ናት፡፡›› ብሏል (አል ቀድር 3) እናም ይህችን ሌሊት በእምነትና አላህ ዘንድ ያለውን ምንዳ በማሰብ በመስገድ ቆሞ ያሳለፈ ሰው ቀደም ሲል የሰራው ወንጀል ይማርለታል፡፡ እርሷ በረመዳን ወር በመጨረሻዎቹ አስርት ሌሊቶች ውስጥ የምትገኝ ነች፡፡ ይህችን ሌሊት፣ ማንም ሰው በእርግጠኝነት በዚህ ዕለት ትሆናለች ብሎ መወሰንና መናገር አይችልም፡፡
የጾም ትሩፋት
1 ወንጀሉ ይማርለታል
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ጾመኛ ሁለት ደስታዎች አሉት፡፡ በሚያፈጥርበት ጊዜ የሚደሰተውና ከጌታው ጋር ሲገናኝ የሚደሰተው ደስታ ነው፡፡›› (አል ቡኻሪ 1805 /ሙስሊም 1151)
3 በጀነት ውስጥ ከጾመኞች በስተቀር ማንም የማይገባበት የሆነ ረያን የሚባል በር አለ፡፡
4 አላህ (ሱ.ወ) የጾምን ምንዳ ወደራሱ አስጠግቶታል፡፡
የጾም ሚስጥር
ጾም፣አንድ ባሪያ የሚወዳቸውን ነገሮች ወይም ፍላጎቶቹን በመተው፣ ስሜቱን በመጫን፣ አላህን የሚገዛበት አምልኮ በመሆኑ፣
አንድ ጾመኛ ሐላል ነገሮችን በመከልከል የአላህን ትዕዛዝ ማክበር ከቻለ፣ የወንጀልና የሀጢኣት ስሜቱን በመለጎሙና አላህ ከገደበው ወሰን በመጠበቁ፣የበለጣ ይመቸዋል
ጾም፣ የተራቡና የተቸገሩ ሰዎችን ሕይወት የሚካፈሉበትና ዓመቱን ሙሉ በችግርና በሰቆቃ የሚያሳልፉትን ድሆች ሁኔታ የሚያስታውሱበት የአምልኮ ዘርፍ ነው፡፡ ትክክለኛ የአላህ ባሪያ፣ ድሃ ወንድሞቹ ምን ያህል በረሃብና በጥማት እንደሚቸገሩ ያስታውሳል፤ በመሆኑም ለነርሱ የእርዳታ እጁን በመዘርጋት የሚቻለውን ሁሉ ያደርጋል፡፡