የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት በመልክተኞች ማመን
በመልዕክተኞች ማመን ትርጉም
መልዕክታቸው በትክክልና በቀጥታ ከአላህ ዘንድ ነው የተላለፈው ብሎ ማመን፡፡የመልዕክተኞች ሁሉ ጥሪ፣ አላህን ያለአጋር በብቸኝነት ወደ ማምለክ ነው፡፡ አላህ(ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «በየ ሕዝቡም ሁሉ ውስጥ አላህን ተገዙ ጣዖትንም ራቁ በማለት መልዕክተኛን በእርግጥ ልከናል::»(አል ነህል 36)
መልዕክተኞች ሁሉም እውነተኞችና እውነተኝነታቸው በአላህ የተረጋገጠ ነው፡፡ አላህን በእጅጉ የሚፈሩና ታማኞች ናቸው፡፡ ወደ ትክክለኛው ጎዳና የተመሩና የሚመሩ ናቸው፡፡ አላህ(ሱ.ወ) እነርሱን የላከበትን ነገር በሙሉ አድርሰዋል፡፡ ከርሱ ምንም የደበቁትም ሆነ የቀየሩት ነገር የለም፡፡ ከራሳቸው ዘንድ አንዲትም ፊደል በውስጡ አልጨመሩም አልቀነሱምም፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «እነዚያ የአላህን መልእክቶች የሚያደርሱና የሚፈሩት ከአላህም ሌላ ማንንም የማይፈሩ መርማርነት በአላህ በቃ።፡» (አህዛብ 39)
ለሰው ልጆች ሕግጋትን የሚያብራራላቸውና ወደ ትክክለኛው ጎዳና የሚመራቸው ከጌታ የሆነ መልዕክተኛ ሊኖራቸው የግድ ይላል፡፡ መለኮታዊ መልዕክት የዓለም እስትንፋስና የሕይወት ብርሃን ነው፡፡ መንፈስ፣ ሕይወትና ብርሃን የሌለው ዓለም እንዴት ዓይነት ሕልውና ሊኖረው ይችላል?
አላህ (ሱ.ወ) መልክቱን ሩሕ ሲል የሰየመው ለዚህ ነው ፡፡ ሩሕ ከሌለ ሕይወት የለም፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «እንደዚሁም ወደ አንተ ከትዕዛዛችን ሲኾን መንፈስን (ቁርኣንን) አወረድን፡፡ መጽሐፉም እምነቱም ምን እንደሆነ የምታውቅ አልነበርክም፡፡ ግን (መንፈሱን) ከባሮቻችን የምንሻውን ሰው በርሱ የምንመራበት ብርሃን አደረግነው፡፡ አንተም ወደ ቀጥተኛው መንገድ በርግጥ ትመራለህ፡፡» (አል ሹራ 52) ይኸውም የሰው ልጅ አዕምሮ በጥቅሉ ጠቃሚና ጎጂ ነገሮችን መለየት የሚችል ቢሆንም፣ በመልዕክተኞች አማካይነት ካልሆነ በስተቀር በረቀቀ መልኩ መጥፎውንና መልካሙን የሚለይበት መንገድ አይኖረውም፡፡
በሁለቱም ዓለም ደስታም ሆነ ስኬት ሊገኝ የሚችልበት መንገድ በመልዕክተኞች እጅ የሚገኘው ብቻ ነው፡፡ ክፉና ደጉንም በረቀቀ መልኩ የሚለየው መንገድ የነርሱ መንገድ ብቻ ነው፡፡ ለዚህ፣ መልዕክተኞች ካስተላለፉት መልዕክት ጀርባውን የሰጠ ሰው ለመልዕክቱ ተቃራኒ በሆነበትና ጀርባውን በሰጠበት ልክ አለመረጋጋት፣ ጭንቀትና መረበሽ ያገኘዋል፡፡አላህ ሱ/ወ/ እንድህ ብሏል «ሁላችሁም ኾናችሁ ከርሷ ውረዱ፡፡ ከኔም የኾነ መመሪያ ቢመጣላችሁ ወዲያውኑ መመሪያዬን የተከተለ ሰው በነሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ እነሱም አያዝኑም» አልናቸው፡፡ እነዚያም (በመልክተኞቻችን) የካዱ በአንቀጾቻችንም ያስተባበሉ እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው፡፡ እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡
በመልዕክተኞች ማመን ከኢማን ማዕዘናት መካከል አንዱ ነው፡፡
በመልዕክተኞች ማመን ከስድስቱ የኢማን ማዕዘናት መካከል አንዱ ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «መልዕክተኛው ከጌታው ወደ እርሱ በተወረደው አመነ፡፡ ምእመናንም (እንደዚሁ)፤ ሁሉም በአላህ፤ በመላዕክቱም፤ በመጽሐõፍቱም፣ ከመልዕክተኞቹ በአንድም መካከል አንለያይም (የሚሉ ሲሆኑ ) አመኑ፡፡» (አልበቀራ 285) አንቀጹ፣ በመልዕክተኞች መካከል ምንም ሳይለያዩ በሁሉም ማመን ግዴታ እንደሆነ ያስረዳል፡፡ አይሁዶችና ክርስቲያኖች እንዳደረጉት በከፊሎቹ አምነን በከፊሎቹ አንክድም፡፡
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) የኢማን ማዕዘናትን አስመልክተው እንዲህ ብለዋል፡- «በአላህ በመላ በአላህ፣ በመጻሕፍቱ፣ በመልክተኞቹ፣ በመጨረሻው ቀንና በክፉም በደጉም በአላህ ውሳኔ ልታምን ነው፡፡» (ሙስሊም 8)
የመልዕክተኞች ምልክቶችና ታዓምራታቸው
አላህ (ሱ.ወ) መልዕክተኞቹን በማስረጃና ተያያዥነት ባላቸው የተለያዩ ነገሮች እውነተኝነታቸውንና ነብይነታቸውን በማረጋገጥ ረድቷቸዋል፡፡ ከዚህም መካከል በሰው ልጅ ችሎታ የማይከሰቱ በሆኑ ታዓምራትና ግልጽ በሆኑ ምልክቶች ያደረገላቸው እገዛ ወይም ድጋፍ አንዱ ነው፡፡ ይህም የሆነው እውነተኝነታቸውን ለማጽደቅና ነብይነታቸውን ለማጽናት ነው፡፡ታዓምራት የሚባለው ተለምዶን ጥሰው የሚከሰቱ ነገሮችን ነው፡፡ ይኸውም አላህ (ሱ.ወ) በነብያቱና በመልእክተኞቹ አማካይነት ይፋ የሚያደርገው ሲሆን ሰዎች መሰሉን ሊያመጡ ወይም ሊያስከስቱ የማይችሉት እንደሆነ በመፎካከር መልክ የሚከሰት ነው፡፡
ከነብያት ተዓምራት መካከል፡
በመልዕክተኞች ማመን ምንን ያካትታል?
መልዕክታቸው በትክክልና በቀጥታ ከአላህ ዘንድ ነው የተላለፈው ብሎ ማመን፡፡ የመልዕክተኞች ሁሉ ጥሪ፣ አላህን ያለአጋር በብቸኝነት ወደ ማምለክ ነው፡፡
አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «በየ ሕዝቡም ሁሉ ውስጥ አላህን ተገዙ ጣዖትንም ራቁ በማለት መልዕክተኛን በእርግጥ ልከናል::» (አል ነህል 36)
በርግጥ የየነብያቱ ደንብና ስርዓት ንዑስ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ሊለያይ ይችላል፡፡ ከነኚያ ከተላኩባቸው ሕዝቦች አንጻር የተፈቀዱና የተከለከሉ ነገሮች ሊለያዩ ይችላሉ፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «ከናንተ ለሁሉም ህሕግና መንገድን አደረግን፡፡» (አልማኢዳ 48)
በነብያትና በመልክተኞች በሙሉ ማመን፡፡ አላህ በስማቸው የነገረንን ከነስማቸው እናምንባቸዋለን፡፡ ለምሳሌ ሙሐመድ፣ ኢብራሒም፣ ሙሳ፣ ዒሳ፣ ኑሕ (ዐለይሂሙ ሰላም) …. ከነሱ መካከል ስማቸውን የማናውቃቸውን ደግሞ በጥቁሉ እናምንባቸዋለን፡፡ ከነሱ መካከል አንዱን የካደ ሁሉንም ክዷል፡፡
በቁርኣንና በሐዲስ የተጠቀሱ የመልዕክተኞችን ገድልና ተዓምራት እውነት ነው ብሎ መቀበል፡፡ ለምሳሌ ለነብዩላህ ሙሳ (ዐ.ሰ) ባሕሩ የተሰነጠቀላቸው መሆኑን ማመን፡፡
4 ወደ እኛ የተላኩትን መልዕክተኛ ህግና ስርዓት መተግበር፡፡ እሳቸውም ከሁሉም በላጩና መቋጫ የሆኑት ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ናቸው፡፡
የመልዕክተኞች መገለጫ
1 መልዕክተኞች የሰው ዘር ናቸው፡፡
በነሱና በሌላው ሰው መሐከል ያለው ልዩነት፣ አላህ (ሱ.ወ) በመለኮታዊ ራዕይና መልዕክት የመረጣቸው መሆኑ ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «ከአንተም በፊት ወደ እነሱ የምናወርድላቸው የኾኑ ሰዎችን እንጂ ሌላን አልላክንም፡፡» (አል አንቢያእ 7) የጌትነትም ሆነ የአምላክነት ደረጃ የላቸውም፡፡ ነገር ግን በውጫዊ ተክለ ሰውነታቸው ምንም እንከን የሌላቸው፣ የሙሉዕነትን ደረጃ የደረሱ ሲሆን በስ- ነምግባራቸውም በሙሉዕነት የመጨረሻውን ጣራ የነኩ ናቸው፡፡ በተጨማሪም በጎሳቸውም የተከበረ ጎሳ አባል ናቸው፡፡ እንዲሁም ብሩህ አዕምሮና ማራኪ ልሳን የተቸሩ ናቸው፡፡ ይህም የመልዕክቱን ውጣ ውረድ በአግባቡ እንዲሸከሙ አድርጓቸዋል፡፡ የነብይነትን ፈተናም በብቃት እንዲወጡ አግዟቸዋል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) መልዕክተኞችን ከሰው ዘር ያደረገበት ምክንያቱ የሰዎች ተምሳሌቶች ከራሳቸው እንዲሆን ነው፡፡ በመሆኑም መልዕክተኞችን መከተልና እነርሱን በተምሳሌትነት መያዝ በሰዎች ሊከናወን የሚችልና በችሎታቸው ስር ያለ ጉዳይ ነው፡፡
2 አላህ (ሱ.ወ) መልዕክቱን በማስተላለፉ ለይቷቸዋል፡፡
ከሌላው ሰው ነጥሎ እነርሱን መለኮታዊ ራዕዩን እንዲረከቡ መርጧቸዋል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «እኔ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ማለት ወደ እኔ የሚወረድልኝ ቢጢያችሁ ሰው ብቻ ነኝ፡፡» (አል ካሕፍ 110) የነብይነት ማዕረግም ሆነ መለኮታዊ መልዕክት፣ በመንፈሳዊ ምጥቀት ወይም በጮሌነት ወይም በአዕምሮ ብስለት የሚያገኝ ነገር አይደለም፡፡ እሱ የአላህ መምረጥና ማጨት ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) ከሰዎች መካከል መልዕክተኞችን መርጦ አጭቷቸዋል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «አላህ መልክቱን የሚያደርግበትን ስፍራ ዐዋቂ ነው፡፡» (አል አንዓም 124)
3 እነርሱ ከስህተትና ከመርሳት የተጠበቁ ናቸው፡፡
እነርሱ ከአላህ በሚያስተላልፉት መልዕክት ከስህተትና ከመርሳት የተጠበቁ ናቸው፡፡ ከአላህ በሚያስተላልፉት መልዕክት አይሳሳቱም፡፡ አላህ ወደ እርነሱ የላከውንም በማስፈፀም አይሳሳቱም፡፡
4 እውነተኝነት፡
መልዕክተኞች በንግግራቸውም በተግባራቸውም እውነተኞች ናቸው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «ይህ አዛኙ ጌታ የቀጠረን፣ መልዕክተኛቹም እውነትን የነገሩን ነው፡፡» (ያሲን 52)
5 ትዕግስት፡
መል°ክተኞች ወደ አላህ ሃይማኖት አብሳሪና አስጠንቃቂ በመሆን በርግጥ ተጣርተዋል፡፡ በዚህም የተለያዩ ስቃዮችና መከራዎች ደርሰውባቸዋል፡፡ ሁሉንም የሚደርስባቸውን መከራና ስቃይ የአላህን ቃል የበላይ በማድረግ ጉዞ ላይ በትዕግስት ተሸክመው አልፈዋል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «ከመልዕክተኞችም የቆራጥነት ባለቤት የነበሩት እንደታገሱ ሁሉ ታገስ፡፡» (አል አሕቃፍ 35)
በመልዕክተኞች ማመን ከባድ ጥቅም አለው ከነዚህም መካከል
አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «ከኔም የኾነ መሪ ቢመጣላችሁ መሪየን የተከተለ አይሳሳትም አይቸገረምም፡፡ ከግሳጼዬም የዞረ ሰው ለርሱ ጠባብ ኑሮ አልለው፡፡» (ጧሃ 123-124)