የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት የወላጆች መብት
እስልምና ለወላጆች ትልቅ ክብር አጎናፅፏቸዋል። ክብራቸው በእስልምና ውስጥ በጣም ትልቅ ከሆነው የአሏህ አሃዳዊነት ጉዳይ ጋር አስተሳስሮታል።"ጌታችሁ እሱን እንጅ ሌላን አትገዙ። ለወላጆቻችሁም መልካምን ስሩ ሲል አዘዘ።" (ሱረቱል ኢስራዕ 23) ሃያሉ አሏህ ወላጆችን የወንድ እና የሴት ልጆች መኖር ሰበብ አድርጓቸዋል። ልጆች ያደረጉ ቢያደርጉ የወላጆቻቸውን ሃቅ መመለስ አይችሉም። ለልጆቻቸው ምቾት እና እንክብካቤ ሲሉ ያጋጠማቸው ፈተና ፣ ድካም እና መዛል ፣ ጉዳት ፣ እረፍት እና እንቅልፍ ማጣት እና እንግልት ሊክሱ አይችሉም።
ከአሏህ ፍትሃዊነት መገለጫዎች ውስጥ አንዱ ወላጆች ለልጆቻቸው ባደረጉላቸው ምስጉን ተግባራት እና እንክብካቤ በልጆቻቸው ላይ መብቶች ያላቸው መሆኑን መደንገጉ ነው። አሏህ እንዲህ አለ፡ "ሰውንም ለወላጆቹ መልካም አድራጎትን እንዲያደርግ አዘዝነው።" (ሱረቱል አንከቡት 8) እንዲህም አለ፡ "በቅርቢቱ አለም በመልካም ስራ ተወዳጃቸው።" (ሱረቱ ሉቅማን 15) በሌላ በኩል ደግሞ ከሶሃቦች አንዱ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ሲሉ ጠየቃቸው፡ የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ሆይ! በጣም ላገለግለው የሚገባ ማነው? እሳቸውም፡ እናትህ አሉ። እሱም፡ ከዚያስ አላቸው። እሳቸውም እናትህ አሉት። ከዚያስ ማነው አላቸው። እሳቸውም እናትህ አሉ። እሱም ከዚያስ ማነው? አላቸው። እሳቸውም ከዚያ አባትህ አሉት።›› (ቡኻሪ 5971 ፣ ሙስሊም 2548)
ለወላጆች በጎ መዋል ቱሩፋት
ወላጆችን ማክበር ግዴታ ነው። እነሱን ማክበር ሽልማቱ ትልቅ ነው። እርዚቅ (ሲሳይ) ወይም በረካ ለማግኘት ሰበብ ነው። በዚህ አለም ህይወት መልካምነት ሲሆን በመጭው አለም ህይወት ደግሞ ጀነት ለመግባት ሰበብ ነው። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹ባፍንጫው አቧራ ውስጥ ይደፋ ፣ ባፍንጫው አቧራ ውስጥ ይደፋ ፣ ባፍንጫው አቧራ ውስጥ ይደፋ አሉ። የአሏህ መልዕክተኛ ሆይ! እሱ ማን ነው? ተብለው ተጠየቁ። እሳቸውም፡ በእርጅና እድሜ አንዳቸውን ወይም ሁለቱንም ወላጆቹን አግኝቶ ጀነት ያልገባ ሰው ነው አሉ።›› (ሙስሊም 2551)
ለወላጆቹ ደግ መሆን አሏህ በጣም የሚወደው ተግባር ነው። አብዱሏህ ቢን መስኡድ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በጣም የሚወደደው ተግባር ምንድነው? ብሎ ጠየቃቸው። እሳቸውም፡ በወቅቱ መስገድ ነው አሉ። እሱም ከዚያስ ምንድነው? አላቸው። እሳቸውም ወላጆችን ማክበር ነው አሉ። እሱም ከዚያስ? ምንድነው አላቸው። እሳቸውም ጅሃድ ፊ ሰቢሊላህ (በአሏህ መንገድ መታገል) ነው አሉት።›› (ቡኻሪ 527 ፣ ሙስሊም 85)
ወላጆችን ማክበር ከተጨማሪ ጅሃድ የበለጠ ነው። አንድ ሰው ወደ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መጣና ኡጃሂዱ (ልታገል ፣ ጅሃድ ላድርግ) አላቸው። እሳቸውም፡ ‹‹ወላጆች አሉህን?›› አሉት።እሱም አዎ አለ። እሳቸውም፡ ‹‹ለእነሱ ጥቅም ታገል›› አሉት።›› (ቡኻሪ 5972 ፣ ሙስሊም 2549)
ወላጆችን ማስከፋት
ወላጆችን አለማክበር ከትልልቅ ወንጀሎች ውስጥ አንዱ እና ከእነሱ ውስጥ ትልቁም ነው። በሐዲስ ውስጥ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡ ‹‹ከትልልቅ ወንጀሎች ሁሉትልቁ በአሏህ ላይ ማጋራት እና ወላጆችን አለማክበር ነው።›› (ቡኻሪ 6919 ፣ ሙስሊም 87)