መማርዎን ይቀጥሉ

ሎግ ኢን አላደረክም
መማር ለመጀመር፣ እድገትን ለመከታተል፣ ነጥቦችን ለመሰብሰብ እና ወደ ውድድር ለመግባት አሁኑኑ በታ ፕላትፎርም ይመዝገቡ፡ ከተመዘገቡ በኋላ ለሚማሯቸው ርዕሶች የኤሌክትሮኒክስ ሰርተፍኬት ይደርስዎታል።

የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል

ትምህርት የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንደ ባል

በዚህ ትምህርት ውስጥ የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) በቤታቸው ውስጥ የነበራቸውን ህይወት እና ከሚስቶቻቸው ጋር የነበራቸውን መስተጋብር ትማራላችሁ።

1 ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በቤት ውስጥ ስለ ነበራቸው ባህሪ ትማራላችሁ።2 ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከቤተሰባቸው አባሎች ጋር በሚኖራቸው መስተጋብር ይላበሷቸው ስለነበሩ ድንቅ ግብረገቦች ትማራላችሁ።3 ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከሚስቶቻቸው ጋር የነበራቸውን መስተጋብር እንደ ምሳሌ ትከተላላችሁ።

ከአሏህ ጥበቦች ውስጥ አንዱ መልዕክተኞቹን የሰው ልጅ ማድረጉ ነው። ይህም ሰዎች ምሳሌ አድርገው ላለመከተላቸው ሰበብ (ምክኒያት) እንዳያቀርቡ ያደርጋቸዋል። እንዲሁም ስነ-ምግባራቸውን እንዲላበሱ እና ልክ እንደነሱ እንዲሰሩ ይረዳቸዋል። የሙስሊም ሰው ደስታ በዚህ አለም እና በመጭው አለም ህይወት ያለው ቁርአንን ፣ ሱናን እና የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መንገድ በመከተል ነው። ለዚህም ነው ሙስሊሞች የነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) የህይወት ታሪክ እና ሱናቸውን ማወቅ ያለባቸው።በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ምሳሌ አድርጎ መያዝ ያስፈልጋል።

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በቤታቸው ውስጥ የነበራቸው ህይወት እና ከሚስቶቻቸው ጋር የነበራቸው መስተጋብር ለሰው ልጆች ሁሉ ትልቅ ምሳሌ ነው። ቤተሰቦቹ በዚህ አለም ውስጥ ጥሩ ህይወት እንዲኖሩ እና በመጭው አለም ደግሞ ጀነትን እንዲገቡ የሚፈልጉ ባሎች ሁሉ የእሳቸውን ፈለግ መከተል አለባቸው። አሏህ እንዲህ አለ፡ "በእርግጥ አሏህን እና የመጨረሻውን ቀን ለሚከጅል ሰው ፣ አሏህን ብዙ ለሚያወሳ ሰው በአሏህ መልዕክተኛ ላይ (ሊከተሉት የሚገባ) ምርጥ ምሳሌ አለላችሁ።" (ሱረቱል አህዛብ 21)

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከሚስቶቻቸው ጋር የነበራቸው ግብረገብ

አኢሻ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈችው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹ከእናንተ መካከል በላጩ ለቤተሰቦቹ ጥሩው ነው። እኔ ደግሞ ለቤተሰቦቼ ጥሩው ነኝ።›› (ትርሚዚ 3895) ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የኡመታቸው ወንዶች ለሴቶቻቸው መልካም እንዲሆኑ እና መልካም ነገር እንዲያደርጉ አዘዋል። ይህን የሚያደረጉትንም አሞካሽተዋል።

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሚስቶቻቸውን ለማዝናናት እና ፍላጎቶቻቸውን ለሟሟላት የሰጡት ትኩረት

አኢሻ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈችው እንዲህ አለች፡ አቢሲኒያኖች (ኢትዮጲያኖች) መስጅድ ውስጥ ሲጫወቱ እነሱኑ እየተመለከትኩ ሳለ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በሳቸው ሪዷ (የላይኛውን የሰውነት ክፍል ሚሸፍን እንደኮት ያለ ልብስ) አለበሱኝ። እኔም እስከምፈልገው ድረስ ማየቴን ቀጠልኩ። ከዚህ ክስተት አንዲት ሴት ባሏ ሊያዝናናት እናሊንከባከባት የሚገባው በዚህ መንገድ እንደሆነ ትረዳላችሁ።›› (ቡኻሪ 5236 ፣ ሙስሊም 892) ይህንኑ የመልዕክተኛውን (ሰ.ዐ.ወ) ምሳሌነት መከተል ያስፈልጋል። ባል ሁሌም አስተዋይ ፣ የሚስቱን ፍላጎት ማክበር ፣ መንፈሳዊ እና ቁሳዊ ፍላጎቶቿን ማሟላት አለበት።

የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) አንድ ሰው ከሚስቱ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ከተፈቀዱ ጨዋታዎች መካከል እንደሆነ ቆጥረውታል። የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹የአደም ልጅ ጥፋት ሁሉ ተቀባይነት የለውም፤ ሶስት ነገሮች ካልሆኑ በቀር። ቀስት ውርወራ ፣ ፈረስ ግልቢያ እና ከሚስቱ ጋር መጫወት ናቸው። እነዚህ ጥፋቶች ተቀባይነት ያላቸው ናቸው።›› (አህመድ 17337)

በሌላ በኩል አኢሻ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈችው በአንድ ጉዞ ላይ ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጋር ሆኜ እያለ ከእሳቸው ጋር ውድድር ገጠምን። በእግሮቼ አፈትልኬ ቀድሚያቸው ሮጥኩ። እንደገና ደንደን ባልኩ ጊዜ ከእሳቸው ጋር ተፎካከርን። እናም ቀደመውኝ እሮጡ። እሳቸውም፡ ይህ ነው ውድድር አሉ።›› (አቡዳውድ 2578) ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከሚስቶቻቸው ጋር ይጫወቱ እና ይቀላለዱ ነበር። የትዳር ህይወት አሰልች እና ደባሪ መሆን የለበትም።

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የቤተሰብ ችግሮችን የሚፈቱበት ጥበብ

በአባላቶቹ መካከል ከሚነሳ ችግር ነፃ የሆነ ቤት የለም። እነዚህን ችግሮች እንዴት እንደምንጋፈጥ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ምርጥ ምሳሌን ትተውልናል። አነስ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከአንዷ ሚስታቸው ቤት ውስጥ ሆነው በነበረ ጊዜ ከምዕመናን እናት አንዷ በሳህን አድርጋ ምግብ ላከችላቸው። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከቤቷ የነበሩባት ሚስታቸው የአገልጋዩን እጅ ስትመታው ሳህኑ ወድቆ ተሰበረ። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የሳህኑን ስብርባሪ ሰበሰቡ። ሳህኑ ላይ የነበረውም ምግብ እሱ ላይ ሰበሰቡትና ‹‹እናትህ (ሚስቴ) ቀናች›› አሉ። ከዚያም ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከቤቷ የነበሩባት ሚስታቸው ደህና ሳህን እስክትሰጣቸው ድረስ አገልጋዩን አቆዩት። እናም ሳህኗ ለተሰበረባት ሚስታቸው ደህና ሳህን ሰጧት። የተሰበረውንም ሳህን የተሰበረበት ቤት ውስጥ (እንዲቀር) አደረጉ።›› (ቡኻሪ 5225)

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከሚስቶቻቸው ወይም ከቤተሰብ አባላቸው በተፈጥሯዊ ስሜት ምክኒያት የተለያዩ ክስተቶች ሲገጥማቸው አይበሳጩም ነበር። ለሁሉም ክስተቶች ምልሽ የሚሰጡት በሳል በሆነ እና ጥበብ በተሞላበት አግባብ ነው። ክስተቱ ወይም አለመግባባቱ ጭቅጭቅ እና ጠብ ከታከለበት ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ገነሩን ገታ ፣ ውጥረቱን ረገብ ያደርጉና ለሁሉም ፍትሃዊ ነገር ያደርጉ ነበር።

ከዚህ በተጨማሪ የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሚስቶቻቸው በተቆጡ ጊዜ እና ይህንኑ ባዩ ጊዜ ለዚህ ምላሽ የሚሰጡት በደግነት እና በእዝነታቸው ነው። አኢሻ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈችው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹በእርግጠኝነት በእኔ በምትደሰች እና በምትቆጭ ጊዜ አውቃለሁ። እሷም እንዴት ነው ምታውቁት? ስትል ጠየቀቻቸው። እሳቸውም አሉ፡ ‹‹በእኔ በተደሰትሽ ጊዜ ‹‹አይደለም! በሙሐመድ ጌታ ይሁንብኝ›› ትያለሽ። በእኔ በተቆጣሽ ጊዜ ደግሞ ‹‹አይደለም! በኢብራሂም ጌታ ይሁንብኝ›› ትያለሽ አሏት። ከዚያም አዎ! የአሏህ መልዕክተኛ ሆይ! በአሏህ ይሁንብኝ ምንም ነገር አልተውም ያንቱን ስም ቢሆን እንጅ።›› (ቡኻሪ 5228 ፣ ሙስሊም 2439)

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከሚስቶቻቸው ጋር የነበራቸው በጎ ህይወት

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በቤታቸው ጉዳይ ውስጥ የሚስቶቻቸውን ሸህም ለማቅለል ሚስቶቻቸውን ያግዙ ነበር። ከእሳቸው ግብረገብ አንዱ እሳቸውን የሚያገለግሉ እና በግል ያሳሰባቸውን ጉዳይ እራሳቸው ይፈፅሙ ነበር።

በአንድ ወቅት ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ቤት ውስጥ ምን እንደሚሰሩ አኢሻ (ረ.ዐ) ተጠይቃ ስትመልስ እንዲህ አለች፡ ‹‹ቤተሰባቸውን ያገለግላሉ። የሶላት ሰአት በደረሰ ጊዜም ለመስገድ ይሄዳሉ።›› (ቡኻሪ 676) በሌላ ሐዲስ ደግሞ እንዲህ ብላለች፡ ‹‹የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ነጠላ ጫማቸውን ይጠግናሉ ፣ ልብሳቸውን ይጥፋሉ እናም ልክ እንደናንተው ቤት ውስጥ ስራ ይሰራሉ።›› (አህመድ 25341)

ለሚስቶች የፍቅር መግለጫ መንገዶች

١
ለሚስቶች የፍቅር መግለጫ መንገዶች
٢
2 በእጅህ ምግብ መጉረስ
٣
እንደምትወዳት ንገራት
٤
ስታወራ በጥሞና አድምጣት

በፍቅር መግለጫ ቃላት ጥራት

በሐዲስ ውስጥ እንደተዘገበው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ለአኢሻ (ረ.ዐ) እንዲህ አሏት፡ ‹‹አኢሻ ሆይ! ይህ ሰላምታ የሚሰጥሽ ጅብሪል ነው።›› (ቡኻሪ 3768) ‹‹አል-ሁሚራ›› ብለውም ይጠሯት ነበር። ሮዛማ ወይም አመራዊ ቆዳ ያላት ማለት ነው።

ባል ሚስቱን በእጁ መመገብ

ከሰአድ ኢብን አቢወቃስ (ረ.ዐ) እንደተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹የምትለግሱት ማንኛውም ነገር ምፅት ነው። ከሚስታችሁ አፍ ላይ የምታደርጉት ቁራሽ ምግብ እንኳ ቢሆን።›› (ቡኻሪ 2742)

ባል ለሚስቱ ውዴታውን መግለፅ

አምር ቢን አል-አስ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የዛተ ሲላሳ ወታደሮችን እንድመራ ሰየሙኝ። ወደ እሳቸው መጣሁና ‹‹በጣም አብልጠሁ የምተርወዱት ሰው ማነው?›› አልኳቸው እሳቸውም፡ የእሷን አባት አሉኝ። ከዚያስ አልኳቸው። እሳቸውም፡ ኡመር ኢብን ኸጧብ አሉ። ከዚያም ሌላ ሰው ጠሩ።›› (ቡኻሪ 3662 ፣ ሙስሊም 2384)

በሚያወሩ ጊዜ በጥሞና ማዳመጥ

ይህን ከሚያመላክቱ ነገሮች መካከል የኡሙ ዘር (ረ.ዐ) ረዥም ሐዲስ ነው። በዚህ ሐዲስ ውስጥ አስራ አንድ ሴቶች ወደ አኢሻ መጥተው እሷ ዘንድ በመቀመጥ እያንዳንዳቸው ከባላቸው ጋር ያላቸውን ሁኔታ አጫወቷት። አኢሻ የሚሆነውን ነገር ነግራቸው አስክታበቃ ድረስ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዝም ብለው አዳመጡ።

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ለምስቶቻቸው ራሳቸውን ያስውቡና ያስጌጡ ነበር

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ ቤታቸው ሲገቡ በምን እንደሚጀምሩ አኢሻ (ረ.ዐ) ተጠይቃ ስትመልስ፡ ‹‹ሲዋክ በመጠቀም›› አለች። (ሙስሊም 253) ከዚህ በተጨማሪ እንዲህ ብላለች፡ ‹‹የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ውብ መአዛ ያለውን ሽቶ እቀባቸዋለሁ፤ የማዕዛውን ምልክት ግንባራቸው እና ፂማቸው ላይ እስካይ ድረስ።›› (ቡኻሪ 5923)

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ለሚስቶቻቸው ያላቸው ታማኝነት

ይህን ታማኝነት የሚያሳየን ግልፅ ያለ ምስል ከኸድጃ (ረ.ዐ) ሞት በኋላ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ነበረው ተፅዕኖ ነው። የመካ ሰዎች እስረኞቻቸውን ለማስፈታት የማስለቀቂያ ገንዘብ በላኩ ጊዜ ዘይነብ አቡል አስን ባገባች ጊዜ ኸድጃ (ረ.ዐ) የሰጠቻትን ሀብል ጨምራ ገንዘቡን ላከች። የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ሃብሉን ባዩ ጊዜ ፍቅሯ ተሰማቸውና እንዲህ አሉ፡ እስረኛዋን ፍታላት፤ ለእሷ የሚገባውንም መልስላት፤ ያ ጥሩ ይሆናልና።›› (አቡዳውድ 2692) ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ለኸድጃ የነበራቸው ፍቅር ጥልቅ በመሆኑ አኢሻ (ረ.ዐ) እሷን ምንም እንኳ ባታውቃትም እንድትቀናባት አድርጓል። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዘወትር ስሟን ያነሱ ነበር። በግ አርደው በመከፋፈል ለኸድጃ (ረ.ዐ) ጓደኞች ይልኩ ነበር። አንዳንዴ ‹‹ኸድጃን የምትንከባከባት ከኸድጃ በቀር ምድር ላይ ሴት የለለ በሚመስል ሁኔታ ነው›› ባልኳቸው ጊዜ እሳቸውም፡ ‹‹ኸድጃ እንዲህ እንዲህ ያለች እና ልጅ የወለድኩባት ናት›› ይሉ ነበር።›› (ቡኻሪ 3818 ፣ ሙስሊም 2435)

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በሚስቶቻቸው መካከል የነበራቸው የፍትሃዊነት መገለጫ

١
1 ከእነሱ ጋር የሚያሳልፉት ጊዜ ፍትሃዊ ነው። ሌሊቱን በመካከላቸው እኩል ጊዜ የሳልፋሉ። በመካከላቸውም ልዩነትን ሳያደርጉ ለእያንዳንዳቸው የሚገባቸውን ጊዜ ይሰጣሉ። የሆነ ነገር ሲፈጠር እና በጣም አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ደግሞ ቅድሚያ ፈቃደኝነታቸውን ይጠይቁ ነበር። አኢሻ (ረ.ዐ) እንዲህ እንዳለች ተዘግቧል። ‹‹የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ህመም በጠና ጊዜ ሚስቶቻቸው እኔ ቤት ውስጥ ሆነው እንዲገለገሉ ፈቃዳቸውን ጠየቋቸው። እናም ተስማሙ።›› (ቡኻሪ 198 ፣ ሙስሊም 418)
٢
2 በጉዟቸው አብሮ የሚሄድን በመምረጥ እንዲሁ ፍትሃዊ ነበሩ። በሚስቶቻቸው መካከል እጣ ይጥሉ ነበር። እጣው የወጣላት እሳቸው ጋር አብራ ትሄዳለች።
٣
3 አግብታ የተፈታችን ሴት ባገቡ ጊዜ ቤቷ ውስጥ ሶስት ቀናትን ይቆዩ ነበር። ከዚያም ከቀሪ ሚስቶቻቸው ጋር እኩል የሆነ ሌሊትን ያሳልፋሉ።
٤
4 ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በሚስቶቻቸው መካከል በሁሉም የወጭ እና የገንዘብ ጉዳዮች ዙሪ ፍትሃዊ ነበሩ።

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሚስቶቻቸውን ያበረታቱና ያማክሩ ነበር

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከሚስታቸው ኡሙ ሰላማ (ረ.ዐ) ጋር በሁደይቢያ ጦርነት ቀን ያደረጉት ምክክር የዚህ ምሳሌ ግልፅ ማሳያ ነው። ሙስሊሞች መስዋዕት እንዲያደርጉ እና እራሳቸውን እንዲላጩ በጠየቋው ጊዜ አንዳቸውም አልተነሱም ነበር። ከዚያም ወደ ኡሙ ሰላማ ቤት ገቡና ከህዝቦቹ የገጠማቸውን ነገሯት። ኡሙ ሰላማ እንዲህ አለች፡ የአሏህ ነብይ ሆይ! ይህን እንዲያደርጉ ትፈልጋለሁ? ለማንም ሰው አንዲት ቃል ሳይናገሩ ወጥተው ሄዱና መስዋዕቱን ይረዱ፤ ከዚያም ፀጉር የሚያስተካክልሁን ጠርተው ራስሁን ተላጩ አለቻቸው። አንድ ቃል ሳተነፍሱ ወጥተው ሄዱና መስዋዕታቸውን አረዱ፤ ፀጉራቸውንም ተላጩ። ሰዎችም ይህን ባዩ ጊዜ መስዋዕታቸውን አረዱ። እረስ በእርሳቸውም እራሳቸውን ተላጫጩ።›› (ቡኻሪ 2731)

ትምህርቱን አጠናቅቀሃል


ፈተና ጀምር