መማርዎን ይቀጥሉ

ሎግ ኢን አላደረክም
መማር ለመጀመር፣ እድገትን ለመከታተል፣ ነጥቦችን ለመሰብሰብ እና ወደ ውድድር ለመግባት አሁኑኑ በታ ፕላትፎርም ይመዝገቡ፡ ከተመዘገቡ በኋላ ለሚማሯቸው ርዕሶች የኤሌክትሮኒክስ ሰርተፍኬት ይደርስዎታል።

የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል

ትምህርት የሶላት ምሰሶዎች፣ ግዴታዎች፣ አጥፊዎች እና የማይወደዱ ነገሮች

ሶላት ምሰሶዎች እና ግዴታዎች አሉት፤ የሚያበላሹት ነገሮችም አሉ. በዚህ ትምህርት ውስጥ ስለ ሶላት ምሰሶዎች፣ ግዴታዎች፣ አጥፊዎች እና የማይወደዱ ነገሮች ይማራሉ።

  • የሶላትን ምሰሶዎች ማወቅ።የ
  • የሶላት ግዴታዎችን ማወቅ።
  • ሶላትን የሚያበላሹትን ነገሮች ማወቅ።
  • የመርሳትን ሱጁድን ማወቅ።
  • በሶላት ውስጥ የተጠሉትን ነገሮች ማወቅ።

የሠላት ማዕዘናት

የሠላት ማዕዘናት የሚባሉት የሠላት ዋና ዋና ክፍሎች ሲሆኑ ታውቆም ሆነ በመርሳት ከተተዉ ሠላት የሚበላሽባቸው ነገሮች ናቸው፡፡

የሠላት ማዕዘናት

١
ተክቢረቱል ኢሕራም (የመግቢያ ተክቢራ ወይም‹‹አላሁ አክበር‹‹)
٢
መቆም ለሚችል ሰው መቆም •
٣
ፋቲሐን ማንበብ፤
٤
ሩኩዕ፤
٥
ከሩኩዕ ቀና ማለት፤
٦
ሱጁድ፤
٧
በሁለትሱጁዶች መሐከል መቀመጥ፤
٨
የመጨረሻውተሸሁድ፤ ለመጨረሻው ተሸሁድ መቀመጥ፤
٩
መረጋጋት ወይም ጡመእኒና
١٠
ማሰላመት
١١
በመእዘናት መሃከል ቅደም ተከተል መጠበቅ።

የሰላት ግዴታዎች

የሰላት ግዴታዎች ማለት በሰላት ውስጥ ግዴታ የሆኑ አካላት ማለት ሲሆን እነዚህ ግዴታዎች ሆን ተብሎ ከተተው ሰላቱ ይበላሻል። ነገር ግን አንድ ሰው ረስቶ ወይም ዘንግቶ ከተዋቸው የጐደለውን ለመሙላት የመርሳት ሱጁድ የመውረድ ግዴታ አለበት።

የሰላት ግዴታዎች

١
ከተክቢረተል ኢሕራም ውጭ ያሉት ሁሉም ተክቢራዎች፤
٢
ሩኩዕ ላይ እያሉ አንድ ጊዜ ‹‹ሱብሐነረቢየል ዐዚም›› ማለት፤
٣
ብቻውን ለሚሰግድና ኢማም ሆኖ ለሚያሰግድ ‹‹ሰሚዐላሁ ሊመን ሐሚደሁ›› ማለት፤
٤
ለሁሉም ሰጋጅ ‹‹ረበና ወለከልሐምዱ›› ማለት፤
٥
ሱጁድ ውስጥ አንድ ጊዜ ‹‹ሱብሐነ ረቢየል አዕላ›› ማለት፤
٦
በሁለቱ ሱጁዶች መሐከል ሲቀመጡ አንድ ጊዜ ‹‹ረቢግፊርሊ›› ማለት፤
٧
የመጀመሪያው ተሸሁድ

እነኚህ ግዴታዎች በመርሳት ምክንያት ከተተዉ ግዴታነታቸው ይቀራል፡፡ እነርሱም የእርሳና ሱጁድ ወይም ሱጁደ ሰህው በማድረግ ይጠገናሉ፡፡

የሠላት ሱናዎች

የሠላት ሱናዎች፡ ማንኛውም የሠላት ማዕዘን ወይም ግዴታ ውስጥ የማይመደብ የሶላት ስራ ንግግርም ሆነ ተግባር የሠላት ውስጥ ሱና ይባላል፡፡ ሠላትን የሚያስውብና የሚያሟላ ነው፡፡ በመሆኑም እርሱን በዘውታሪነት መፈፀም ተገቢ ነው፡፡ ነገር ግን እርሱን በመተዉ ሠላት አይበላሽም፡፡

ሱጁደ ሰህው (የማእሳት ሱጁድ)

ሱጁደ ሰህው፣ ሁለት ሱጁድ ሲሆን በሠላት ውስጥ ለሚከሰቱ ጉድለቶችና ክፍተቶች ማካካሻና መጠገኛነት የተደነገገ ነው፡፡

ሱጁደ ሰህው ማድረግ የሚፈቀደው መቼ ነው?

١
አንድ ሰጋጅ በመርሳትና በስህተት ምክንያት በሠላቱ ውስጥ ተጨማሪ ሩኩዕን ወይም ሱጁዱን ወይም መቆም ወይም መቀመጥን ከጨመረ ሰጅደተ ሰህው ይሰግዳል፡፡
٢
ከሠላት ማዕዘናት መካከል አንዱን ማዕዘን ካጎደላ፣ ያንን ያጎደለውን ማዕዘን ያሟላና በሠላቱ ማብቂያ ላይ ሰጅደተ ሰህው ይሰግዳል፡፡
٣
እንደ ተሸሁደል አወል (የመጀመሪያው አታሂያት) ዓይነት ያሉ የሠላት ግዴታዎች መካከል አንዱን ረስቶ ከተወ ሰጅደተ ሰህው ይሰግዳል፡፡
٤
የሰገዳቸውን የረከዓት ቁጥር ከተጠራጠረ፣ መጀመሪያ እርግጠኛ የሆነውን፣ አነስተኛውን ቁጥር ይይዝና ካሟላ በኋላ ሰጅደተ ሰህው ይሰግዳል፡፡

የመርሳት ሱጁድ ዓይነት

ሱጁድ የማድረጊያው ሁላት ጊዜ አለው ከሁለቱ በፈለገው ያደርጋል።

١
ከመጨረሻው ተሸሁድ በኋላ ይሰግዳትና ከዚያም ያሰላምታል፡፡
٢
ሠላቱን በሰላምታ ካሰናበተ በኋላ ሁለት ሱጁዶችን ስግዶ፣ ለሁለተኛ ጊዜ በሰላምታ ያሰናብታል፡፡

ሠላትን የሚያበላሹ ነገሮች

እነዚህ ነገሮች ሶላትን ውድቅ የሚያደርጉ እና መደገም ግዴታ የምያስደርጉ ነገሮች ናቸው።

ሶላት የሚያበላሹ ነገሮች

١
1 ሠላት፣ አንድ ሰጋጅ መተግበር የሚችለው ሆኖ፣ ሲታወቀውም ይሁን በስህተት ማዕዘንን ወይም የሠላት መስፈርትን ከተወ ሠላቱ ትበላሻለች፡፡
٢
ሲታወቀው ከሠላት ግዴታዎች መካከል አንዱን ግዴታ ከተወ ትበላሻለች፡፡
٣
ሲታወቀው ከተናገረ ትበላሻለች፡፡
٤
ሠላት ድምጽ ባለው ሳቅ፣ በማሽካከት ትበላሻለች፡፡
٥
5 በማያስገድዱ ሁኔታዎች ውስጥ በሚደረጉ ተከታታይና በርካት በሆኑ እንቅስቃሴዎች ትበላሻለች፡፡

በሠላት ውስጥ የተጠሉ ነገሮች፡፡

እነኚህ ነገሮች፣ የሠላትን ምንዳ የሚቀንሱ፣ ለሠላት መተናነስን የሚያጠፉ፣ እና የሠላትን ግርማ ሞገስ የሚሰልቡ ናቸው፡፡

በሰላት ውስጥ መዞር

በሰላት ውስጥ መዞር የተጠላ ተግባር ነው ምክንያቱም ነቢዩ(ሰ∙ዐ∙ወ) በሰላት ውስጥ መዞርን (እየዞረ መመልከትን) አስመልክቶ ጥያቄ ሲቀርብላቸው ‹‹እርሱ ሰርቆት ነው (ሸይጧ የአላህ ባሪያ ከሰላቱ ይሰርቀዋል›› ብለዋል።(ቡኻሪ፡ 718)

በእጆች፣ በፊት፣ መጫወት

በሠላት ውስጥ በእጆች፣ በፊት፣ ጣቶችን በማጣመርና በማንጫጫት መጫወት ይጠላል፡፡

አንድ ሰው፣በልቡ በሌላ ነገር ተጠምዶ ወደ ሶላት ማግባት

አንድ ሰው፣ ልቡ በሽንት ሐሳብና በምግብ ክጃሎት ሐሳብ ልቡ ተጠምዶ ወደ ሠላት መግባቱ ይጠላል፡፡ ነገሩ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዳሉት ነው፡፡ ‹‹ምግብ ቀርቦ፣ ሁለቱ ቀሻሾች እየገፈተሩትም ሠላት የለም›› (ሙስሊም 560)

ትምህርቱን አጠናቅቀሃል


ፈተና ጀምር