መማርዎን ይቀጥሉ

ሎግ ኢን አላደረክም
መማር ለመጀመር፣ እድገትን ለመከታተል፣ ነጥቦችን ለመሰብሰብ እና ወደ ውድድር ለመግባት አሁኑኑ በታ ፕላትፎርም ይመዝገቡ፡ ከተመዘገቡ በኋላ ለሚማሯቸው ርዕሶች የኤሌክትሮኒክስ ሰርተፍኬት ይደርስዎታል።

የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል

ትምህርት የሱና ሶላቶች የሚከለከል ጊዜ

የሱና ሶላትቶች የተከለከሉበት ጊዜ አለ። በዚህ ትምህርት ውስጥ ስለነዚህ ጊዜያት ትማራለህ.

  • የሱና ሶላት የሚከለከልበት ጊዜ ማወቅ።

በፈቃደኝነት የሚሰገዱ ሠላቶች የሚከለከሉበት ወቅት፡

ኢስላም ሠላት በውስጣቸው እንዳይሰገድ ነጥሎ ከጠቀሳቸው ወቅቶች በስተቀር የተቀሩት ወቅቶች በሙሉ አንድ ሰው የውዴታ ሠላቶችን ያለ ገደብ ሊሰግድ ይችላል፡፡ እነኚህ የተከለከሉት ወቅቶች የከሃዲያን ማምለኪያ ሰዓታት ስለሆኑ ያለፈን የግዴታ ሠላት አለያም እንደ ተሒየተል መስጂድ ያሉ ሰበብ ያላቸውን ሠላቶች ካልሆነ በስተቀር የውዴታ ሠላቶችን መስገድ አይቻልም፡፡ ይህ ሠላትን በተመለከተ ያለው ፍርድ ሲሆን አላህን ማወደስና(ዚክር) እና አላህን መለመን(ዱዓእ) ግን በየትኛውም ሰዓት ሊተገበር ይችላል፡፡

የመጀመሪያው ግዜ

የፈጅር ሶላት ከተሰገዳ ጊዜ ጀምሮ ፀሐይ ወጥታ የጦር ዘንግን ያህል ትንሽ ከፍ እስከምትል ድረስ ያለው ወቅት፤ የምድር ወገብ አካባቢ ላሉ አገሮች ከ20 ደቂቃ በኋላ ይህ ወቅት ይደርሳል፡፡

ሁለተኛው ግዜ

ፀሐይ በሰማይ መሐከል ሆና ወደ መጥለቂያዋ እስክትዘነበል ድረስ መስገድ አይቻልም፡፡ ይህ የዙሁር ሰላት ወቅት ከመግባቱ በፊት ያለ ትንሽ ጊዜ ነው፡፡

ሶስተኛ ግዜ

ከዐሥር ሠላት በኋላ ፀሐይ እስከምትጠልቅበት ያለው ጊዜ፡

ትምህርቱን አጠናቅቀሃል


ፈተና ጀምር