የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት የጁምዐህ ሶላት
አላህ (ሱ.ወ) በጁምዓ ዕለት፣ በዙህር ሠላት ወቅት እጅግ በጣም የላቀ የኢስላም መገለጫና ከግዴታዎቹ ሁሉ የጠበቀ ሠላትን ደንግጓል፡፡ ይህ ሙስሊሞች በሳምንት አንዴ የሚሰባሰቡበት ዕለት ነው፡፡በዚሁ ዕለት የጁምዐው ኢማም የሚያቀርብላቸውን ምክርና ተግሳጽ ያዳምጣሉ ከዚያም የጁምዐን ሠላት ይሰግዳሉ፡፡
የጁምዓ ዕለት ትሩፋት
የጁምዓ ዕለት ከሳምንቱ ቀናቶች ትልቁና የላቀ ክብር ያለው ዕለት ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) ከቀናቶች መካከል መርጦታል፡፡ ከተቀሩት ወቅቶች በበርካታ ልዩ ነገሮች አብልጦታል፡፡ ከነኚህም መካከል፡-
አላህ (ሱ.ወ)፡ ይህን ሕዝብ ከሌሎች ሕዝቦች ነጥሎ በዚህ ዕለት አልቆታል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡ - ‹‹አላህ (ሱ.ወ) ከኛ በፊት ያሉትን የጁምዓን ዕለት አስቷቸዋል፡፡ ለአይሁዶች የቅዳሜን ዕለት፣ ለክርስቲያኖችም የእሁድን ዕለት አደረገላቸው፡፡ አላህ እኛን አመጣንና ለጁምዓ ዕለትም መራን፡፡›› ብለዋል፡፡ (ሙስሊም 856)
አደም የተፈጠረው በዚሁ ዕለት ነው፡፡ የምፅዓት ዕለትም የምትከሰተው በጁምዓ ዕለት ነው፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡- #ፀሐይ ከምትወጣባቸው ቀናቶች በላጩ የጁምዐ ቀን ነው፡፡ኣደም የተፈጠረው በሱ ውስጥ ነው፡፡ ጀነት እንዲገባ የተደረገውም በሱ ውስጥ ነው፡፡ ከሷም እንዲወጣ የተደረገው በዚሁ ዕለት ውስጥ ነው፡፡ ሰዓቲቱም በጁምዓ ዕለት እንጂ አትከሰትም፡፡; ብለዋል፡፡ (ሙስሊም 854)
ጁምዓ ግዴታ የሚሆነው በማን ላይ ነው?
ከጀሙዓ ሠላት በፊት ገላን መታጠብ፤ኹጥባ ከመጀመሩ ቀደም ብሎ በጊዜ ወደ መስጂድ መምጣትና ጥሩ ልብስ መልበስ የተወደደ ነው፡፡
ሙስሊሞች ጁምዓ በሚሰገድበት ትልቅ መስጂድ ወይም መስጂድ ጃሚዕ ውስጥ ይሰባሰቡና፣ ኢማሙ በመድረክ ላይ በመውጣት ፊቱን ወደ ሰጋጆቹ በማዞር በሁለት ክፍል የተከፈለ ኹጥባ/ ዲስኩር ያደርግላቸዋል፡፡ በሁለቱ ኹጥባዎች መሐከል፣ ለመለያ ያክል ትንሽ ጊዜ በመቀመጥ እረፍት ያደርጋል፡፡ በኹጥባው ውስጥ፣ አላህን እንዲፈሩ ያስታውሳል፡፡ የቁርኣን አንቀጾችን እያጣቀሰ የተለያዩ ምክሮችና ተግሳጾችን ያስተላልፋል፡፡
ሰጋጆቹ ኹጥባውን በጥሞና ማዳመጥ አለባቸው፡፡ መነጋገር ወይም ከኹጥባው ተጠቃሚ እንዳይሆኑ በሚያደርጉ ነገሮች እራስን ማጥመድ ክልክል ነው፡፡ መስገጃ መነካካት ወይም አሸዋና አፈር እያነሱ መበተን እንኳን ክልክል ነው፡፡
የጁምዓ ሠላት ያመለጠው ሰው
የጁምዓ ሠላት የተደነገገው የተወሰነ ያክል ሰው ለሚገኝበት ሁኔታ ነው፡፡ ስለዚህ፣ የጁምዓ ሠላት ያመለጠው ወይም በሆነ ምክንያት ከጁምዓ ሠላት የቀረ ሰው፣ በሱ ምትክ መስገድ ያለበት ዙህርን ነው፡፡ ብቻውን የሚሰግደው ጁምዓ ተቀባይነት የለውም፡፡
ከጁምዓ ሠላት የዘገየ ሰው
ከጁምዓ ሠላት የዘገየና ከኢማሙ ጋር ከረከዓ ያነሰውን ክፍል እንጂ ያልደረሰ ወይም ያላገኘ ሰው የሚሞላው ሠላት በዙህር መልክ ነው፡፡
ጁምዓ ግዴታ የማይሆንባቸው፣ ሴቶችና መንገደኛ የመሳሰሉት በሙሉ ከሙስሊሞች ጋር በመሆን ቢሰግዱ ሠላታቸው ተቀባይነት ያገኛል፡፡ በዚህም የዙህር ሰላት ግዴታ ይወርድለታል፡፡
የጁምዓ ሠላት ላይ የመገኘት ግዴታ
ኢስላማዊው ድንጋጌ፣ የጁምዓ ሠላት ላይ መገኘቱ ግዴታ በሆነባቸው ሰዎች ላይ ሁሉ በቦታው መጣድ ግዴታ መሆኑን አጥብቆ አሳስቧል፡፡ በዓለማዊ ጉዳይ ከርሱ መዘናጋትን አጥብቆ አስጥንቅቋል፡፡ አላህ (ሱ.ወ)፡- #እናንተ ያመናችሁ ሆይ በዐርብ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ መሸጥንም ተዉ፤ ይሃችሁ የምታውቁ ብትኾኑ ለናንተ በጣም የተሻለ ነው፡፡›› ይላል፡፡ (አል ጁምዓ 9)
ጁምዓን የተወ ሰው አላህ በምን አስጠነቀቀው?
ያለ ህጋዊ ምክንያት ከርሱ የሚቀርን ሰው በልቦናው ላይ መናፍቅነት መታተምን አስጥንቅቋል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡ - ‹‹ያለ ምንም ምክንያት በመዘናጋት ሦስት ጁምዓን የተወ ሰው፣ አላህ (ሱ.ወ) በቀልቡ ላይ ያትምበታል፡፡›› ብለዋል፡፡ (አቡ ዳውድ 1052 አህመድ 15498) ‹‹በቀልቡ ላይ ያትምበታል›› ማለት ይጋርደዋል፣ ይሸፍነዋል፣ በውስጡ እንደ መናፍቃንና አመጸኞች ልብ መሃይምነትንና ድርቀትን ያበቅልበታል ማለት ነው፡፡
ከጁምዓ ለመቅረት የሚያስችል ምክንያት፡ ድንገተኛና ያልተለመደ፣ እጅግ በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ወይም በኑሮ አለያም በጤና ላይ አስጊና አደገኛ ሁኔታ መከሰት ነው፡፡
በስራና ሃላፊነት ላይ ለመገኘት ሲባል ከጁምዓ መቅረት እንደ ህጋዊ ምክንያት ይታያልን?
በመሰረቱ፣ በስራና ሃላፊነት ላይ ለመገኘት ሲባል ከጁምዓ ሠላት መቅረት ህጋዊነት ወይም ተቀባይነት ያለው አይደለም፡፡ ከሁለት ሁኔታዎች በስተቀር
ከጁምዓ ሠላት ለመቅረት ህጋዊ ምክንያት ያለው ማን ነው?
1 እርሱ በቦታው ላይ በመኖሩና ከጁምዓ በመቅረቱ እንጂ ሊከሰት የማይችል ትልቅ ህዝባዊ ጥቅም ካለና ይህን ስራ እርሱ ከተወው ከፍተኛ ጉዳትና አደጋ የሚደርስ ከሆነ እርሱን ሊተካው የሚችል ማንም ከሌለ፡፡
ምሳሌ
ከጁምዓ ሠላት ለመቅረት ህጋዊ ምክንያት ያለው ማን ነው?
2 ስራው ብቸኛ የገቢ ምንጩ ከሆነ አስፈላጊ የዕለት ወጪዎቹን ምግቡን መጠጡንና ወሳኝ ጉዳዮችን ለራሱና ለቤተሰቦቹ የሚያስፈፅምበት ከዚያ ስራ ውጭ ምንም ከሌለው ሌላ ስራ እስከሚያገኝና ያለበት ችግር እስኪወገድለት ድረስ በዚያ ስራ ላይ በመቆየት ጁምዓ ሳይሰግድ ቢቀር ይፈቅድለታል፡፡ወይም ምግቡን መጠጡንና አስፈላጊ ጉዳዮችን ለራሱና ለቤተሰቦቹ የሚያስፈጽምበት እስከሚያገኝ ድረስ ይፈቀድለታል፡፡ ይሁን እንጂ ሌላ ስራና የገቢ ምንጭ ማስገኛ መንገድ የማፈላለግ ግዴታ አለበት፡፡