መማርዎን ይቀጥሉ

ሎግ ኢን አላደረክም
መማር ለመጀመር፣ እድገትን ለመከታተል፣ ነጥቦችን ለመሰብሰብ እና ወደ ውድድር ለመግባት አሁኑኑ በታ ፕላትፎርም ይመዝገቡ፡ ከተመዘገቡ በኋላ ለሚማሯቸው ርዕሶች የኤሌክትሮኒክስ ሰርተፍኬት ይደርስዎታል።

የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል

ትምህርት ዘካ ማውጣት ግዴታ የምሆንባቸው ንብረቶች

ዘካት እነሱን ለማጥራት በተወሰኑ የገንዘብ ዓይነቶች ላይ ተደንግጓል። በዚህ ትምህርት ዘካ የተደነገገባቸው የንብረት አይነቶች ትማራለህ።

ዘካ የተደነገገባቸው የንብረት አይነቶች ማወቅ።

ምጽዋት ሊወጣለት ግዴታ የሚሆን ንብረት የትኛው ነው?

አንድ ሰው ለራሱ በሚጠቀምበት ንብረቱ ላይ ምጽዋት የማውጣት ግዳጅ የለበትም፡፡ ለምሳሌ፣ ዋጋው ምንም ያህል ቢወደድም የሚኖሪያ ቤቱ፣ እንዴትም ያለ ዘመናዊና የቅንጦት ቢሆንም ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀስበት መኪናው ላይ፣ ምጽዋት የማውጣት ግዴታ የለበትም፡፡ በሚለብሰው፣ በሚበላውና በሚጠጣውም ነገር ላይ እንዲሁ የግዴታ ምጽዋት የለበትም፡፡

አላህ (ሱ.ወ) ምጽዋትን ግዴታ ያደረገው በግል ጉዳይ ላይ ግልጋሎት የማይሰጡ በሆኑ የተለያዩ ንብረቶች ላይ ሲሆን እነኚህ ንብረቶች በባሕሪያቸው እየጨመሩና እየፋፉ የሚሄዱ ናቸው፡፡ እነሱም የሚከተሉት ናቸው፡-

1 ለጌጥነትና ለውበት የማይለበስ የሆነ ወርቅና ብር

የወርቅና የብር ክምችትም ሆነ ማንኛውም ንብረት፣ ኢስላማዊው ሕግ የገደበውን መጠን (ሂሣብ) ካልሞላ፣ እንዲሁም ሳይቀንስ አንድ የጨረቃ ዓመት ማለትም 354 ቀናቶች ካልዞረበት በስተቀር ምጽዋት(ዘካ) ሊወጣበት ግዳጅ አይሆንም፡፡

በሁለቱ ማዕድናት ምጽዋት የማውጪያ መጠን (ሂሣብ)

١
ለወርቅ 85 ግራምና ከዚያ በላይ
٢
ለብር 595 ግራምና ከዚያ በላይ ነው፡፡

አንድ ሙስሊም ይህን መጠን የሚደርስ ወርቅ ወይም ብር ካለውና አንድ ዓመት ከዞረበት፣ ከንብረቱ 2.5 ፐርሰንቱን ይመጸውታል(ዘካ ያወጣል)፡፡

2 ተቀማጭ ገንዘብ

ተቀማጭ ገንዘብና የተለያዩ የመገበያያ ኖቶች በካሽ በእጁ ያለ ወይም በባንክ አካውንት ውስጥ የሚገኝ ገንዘብ ዘካ ይወጣለታል፡፡

የግዴታ ምጽዋት(ዘካ) አወጣጥ፡

የገንዘቡንና የመገበያያውን ነገር ሊገዛ ከሚችለው የወርቅ መጠን ጋር በማስላት፣ መጠኑ ወርቅ ዘካ ከሚወጣበት ሂሣብ ጋር እኩል ከሆነና ከዚያም ከበለጠ ዘካ ያወጣለታል፡፡ ገንዘቡ ከ85 ግራም ወርቅ ጋር ከተስተካከለ ወይም ከበለጠ፣ እንዲሁም በሰውዬው ይዞታ ስር ኾኖ ሳይቀንስ አንድ የጨረቃ ዓመት ካለፈበት፣ የንብረቱን 2.5 ፐርሰንት ዘካ ያወጣል፡፡

የገንዘብ ዘካ ህሳብ በምሳሌ

የወርቅ ዋጋ ከፍ፣ ዝቅ ሊል፣ ሊወዋወጥ ይችላል፡፡ በአንድ ሰው ላይ ዘካ ማውጣት ግዳጅ በሚሆንበት ወቅት የአንድ ግራም ወርቅ ዋጋ 25 ዶላር ነው ብለን ብናስብ፣ በዚያ ወቅት የዘካ ማውጫ መጠን ወይም ሂሣብ የሚከተለው ይሆናል፡፡ 25 ዶላር/ግ.ም X 85ግ.ም = 2125 ዶላር ይሆናል፡፡

3 ለንግድ የቀረቡ ዕቃዎች

ለንግድ የተዘጋጁ፣ እንደ ሪል ኢስቴቶች፣ ቤቶች፣ ሕንፃዎች ያሉ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች፡ ወይንም ምግብ ነክ አና አላቂ ሸቀጦች በዚህ ስር ይገባሉ፡፡

ለንግድ ዕቃዎቹን የዘካ አወጠጥ

የዘካው አወጠጥ፡ ነጋዴው ለንግድ ዕቃዎቹን በሙሉ ዓመት ዞሮባቸው ከሆነ ዋጋቸውን ያሰላል፡፡ የሚያሰላበት ዋጋም ዘካውን ሊያወጣ በተነሳበት ዕለት ባለው የገበያ ዋጋ መሰረት ነው፡፡ የቃዎቹ ዋጋ የዘካ ማውጫ መጠን (ሂሣብ) ከደረሰ፣ ከሱ ላይ 2.5 ፐርሰንት ዘካ ያወጣለታል፡፡

4 ከምድር የሚበቅሉ፡ አዝመራ፣ ፍራፎዎችና የእህል አይነቶች

አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ ካፈራችሁትና ከዚያም ለናንተ ከምድር ካወጣንላችሁ ከመልካሙ ለግሱ፡፡›› (አል በቀራ 267)

ዘካ ማውጣት ግዴታ የሚሆነው በተወሰኑ የአዝርዕት ዓይነቶች ላይ እንጂ በሁሉም አይደለም፡፡

የሰዎችን ልፋትና ድካም ከግምት ውስጥ ከማስገባት አንጻር፣ ዘካ የሚወጣው ብዛት በዝናብና በወንዝ ውሃ በለሙና በሰው ኃይል ወይም መስኖ በለሙት መካከል ልዩነት አለው፡፡

የአዝመራ፣ ፍራፎዎችና የእህል አይነቶች ዘካ ቅድመ ሁኔታ

1 ዘካ የሚወጣለትን መጠን መድረስ

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዘካ ማውጣት ግዳጅ የሚሆንበትንና ከርሱ በታች ከሆነ ዘካ ማውጣት ግዳጅ የማይሆንበትን መጠን (ሂሳብ) ወሰን አበጅተውለታል፡፡ ይህንኑ ሲገልጹ እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ከአምስት አውሱቅ በታች የሆነ የተምር ምርት፣ የዘካ ግዳጅ የለበትም፡፡›› (አል ቡኻሪ 1405 / ሙስሊም 979) አውሱቅ ማለት የስፍር መለኪያ ሲሆን፣ ከ580 እስከ 600 ኪሎግራም የሚደርስ የስንዴና የሩዝ መጠንን ይመዝናል፡፡ ስለዚህም፣ መጠኑ ከዚህ በታች በሆነ ፍሬ ላይ ዘካ ግዴታ አይሆንም፡፡

2 ዘካ ግዴታ የሚሆንባቸው የአዝርዕት ዓይነቶች

የሰው ልጅ እንደምግብነት በምርጫው የሚጠቀምባቸውና በክምችት መልክ ለረዥም ጊዜ ሳይበላሹ ሊቀመጡ የሚችሉ፣ እንደ ስንዴ፣ ገብስ፣ ዘቢብ፣ ተምር፣ ሩዝና በቆሎ የመሳሰሉ አዝርዕቶች ናቸው፡፡ ለመሰረታዊ ምግብነት የማያገለግሉና ሳይበላሹ፣ ሊከማቹ የማይችሉ የሆኑ ፍራፍሬዎችና አትክልቶች ላይ የዘካ ግዴታ የለም፡፡ እንደ ማንጎ ሩማን፣ ዱባ ድንች የመሳሰሉትን ማለት ነው፡፡

3 ምርቱ የተሰበሰበ መሆን አለበት

በአዝርዕትና በጥራጥሬዎች ላይ ዘካ ግዴታ የሚሆነው ምርቱ ሙሉ ለሙሉ ከተሰበሰበና ከተለቀመ በኋላ ነው፡፡ ዓመት መቆጠሩ መስፈርት አይሆንም፡፡ ምርቱ በተሰበሰበበት ወቅት የሚፈፀም ይሆናል፡፡ በዓመት ውስጥ ሁለት ጊዜ ምርቱ የሚሰበሰብ ከሆነም በእያንዳንዱ የምርት ለቀማ ወቅት ዘካ ማውጣት ግዴታ ይሆናል፡፡ በዚሁ መልክ በየ ምርት ለቀማ ወቅት ዘካ ይወጣል ማለት ነው፡፡ ዘካ አውጥቶለት ለረዥም ዓመታት ቢያከማቸው በዚያ ክምችቱ ላይ ዘካየማውጣት ግዴታ የለበትም፡፡

5 የእንሰሳት ሃብት፡

የእንሰሳት ሃብት፣ሰዎች የሚገለገሉባቸው የቤት እንሰሳት ማለት ነው፡፡ እነሱም ግመል፣ ላምና ፍየል ወይንም በግ ናቸው፡፡

አላህ (ሱ.ወ) እነኚህን እንሰሳት በመፍጠር ለሰዎች ትልቅ ውለታ ውሎላቸዋል፡፡ ሰዎች ስጋዎቻቸውን ይመገባሉ፤ ከቆዳዎቻቸው ልብስን ይለብሳሉ፤ በመንገድ ሲጓዙና ከቦታ ቦታ ሲዘዋወሩ እነሱንና ጓዛቸውን ይሸከሙላቸዋል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡- ‹‹ግመልን፣ ከብትን፣ ፍየልንም፣ በርሷ (ብርድን መከላከያ) ሙቀት፣ ጥቅሞችም ያሉባት ስትኾን ለናንተ ፈጠረላችሁ ከርሷም ትበላላችሁ፡፡ ለናንተም በርሷ ወደ ማረፊያዋ በምትመልሷት ጊዜ፣ በምታሰማሩዋትም ጊዜ ውበት አላችሁ፡፡ ጓዞቻችሁንም በነፍሶች ችግር እንጂ ወደማትደርሱባት አገር ትሸከማለች ጌታችሁ በእርግጥ ርኀሩኅ አዛኝ ነውና፡፡ (አል ነሕል 5-7)

የእንሰሳት ዘካ ጥቅላዊ መስፈርቶች

١
1 ብዛታቸው የኢስላማዊውን ዘካ የማወጫ መጠን(ሂሣብ) መድረስ፡ ምክንያቱም ዘካ በባለሃብቶች ላይ እንጂ በሌላው ላይ ግዴታ አይደለም፡፡ ለግል ጉዳያቸው የሚጠቁሙባቸው ቁጥራቸው ጥቂት የሆኑ እንሰሳት ያሉት ሰው የዘካ ግዴታ የለበትም፡፡ ከግመል ዘካ የሚወጣው ቁጥራቸው አምስት ሲደርስ ነው፡፡ ለፍየል አርባ፣ ለላም ደግሞ ሰላሳ ነው፡፡ ቁጥራቸው ከዚህ ቁጥር በታች ከሆነ የዘካ ግዴታ የለበትም፡፡
٢
2 በይዞታነት ባለሀብቱ ዘንድ አንድ ሙሉዕ የጨረቃ ዓመት ሊዞርባቸው ወይም ሊያስቆጥሩ ይገባል፡፡
٣
3 በግጦሽ ላይ ተሰማርተው የሚበሉ መሆን አለባቸው፡ እንሰሰዎቹ በግጦሽ ላይ የሚኖሩ፣ ድርቆሽና ግጦሽ በማቅረብ ባለንብረቱ ወጪ የማያደርግባቸው መሆን አለበት፡፡
٤
4 እንሰሳቱ በስራ የተጠመዱ መሆን የለበትም፡፡ ባለቤቱ ማሳውን የሚያርስበት ወይም ዕቃ የሚያጓጉዝበት ወይም እራሱ የሚጓጓዝበት መሆን የለበትም፡፡ ይህ ከሆነ ዘካ የማውጣት ግዳጅ የለበትም፡፡

ትምህርቱን አጠናቅቀሃል


ፈተና ጀምር