መማርዎን ይቀጥሉ

ሎግ ኢን አላደረክም
መማር ለመጀመር፣ እድገትን ለመከታተል፣ ነጥቦችን ለመሰብሰብ እና ወደ ውድድር ለመግባት አሁኑኑ በታ ፕላትፎርም ይመዝገቡ፡ ከተመዘገቡ በኋላ ለሚማሯቸው ርዕሶች የኤሌክትሮኒክስ ሰርተፍኬት ይደርስዎታል።

የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል

ትምህርት ጾም የምፈቱ ነገሮች

ፆምን የሚያፈርሱ ብዙ ነገሮች አሉ በፆመኛ ሰው ላይ ቢደርሱ ፆሙን ያበላሹታል። በዚህ ትምህርት ጾምን ስለሚያበላሹ ነገሮች ትማራለህ።

ጾምን ስለሚያበላሹ ነገሮች ማወቅ።

ጾምን የሚያበላሹ ነገሮች፣

ጾምን የሚያበላሹ ነገሮች፣ አንድ ጾመኛ ሊከለከላቸውና ሊቆጠባቸው የሚገቡ ነገሮች ናቸው፡፡ እነሱም የሚከተሉት ናቸው፡፡

1 መብላትና መጠጣት፡-

አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹ከጎህ የኾነው ነጩ ክርም ከጥቁሩ ክር (ከሌሊት ጨለማ) ለናንተ እስከሚገለጽላችሁ ድረስ ብሉ ጠጡም ከዚያም ጾምን እስከ ሌሊቱ ድረስ ሙሉ፡፡›› (አል በቀራ 187)

ረስቶ የበላ ወይም የጠጣ ሰው ጾሙ አይበላሽም፤ ወንጀልም የለበትም፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡- ‹‹ጾመኛ መኾኑን ረስቶ የበላ ወይም የጠጣ ሰው ጾሙን ይቀጥል፡፡ ያበላውና ያጠጣው አላህ ነው፡፡›› ብለዋል፡፡ (አል ቡኻሪ 1831/ሙስሊም 1155)

2 ምግብንና መጠጥን የሚተካ ነገር፡፡

١
በሰውነት ውስጥ የተጓደለን የጨውና የምግብ መጠን ለመጠገን የሚወሰዱ ምግብ ነክ የሆኑ መርፌዎችና መድሃኒቶች ጾምን ያፈርሳሉ፡፡ ምክንያቱም የምግብና የመጠጥን ቦታ ስለሚተኩ፣ በምግብና መጠጥ ላይያለፈው ሕግ ይመለከታቸዋል፡፡
٢
ለህመምተኛ የሚሰጥ ደም፡፡ ምክንያቱም ደምየምግብና የመጠጥ የመጨረሻው መዳረሻ በመሆኑ ነው፡፡
٣
በማንኛውም መልክ ማጨስ፡፡ ጭስን ወደ ሰውነት እያማጉ ማስገባት፣ ሰውነትን በመመረዝ እንዲጠናከር ያደርገዋል፡፡

3 የፍቶት ጠብታ ቢፈስም ባይፈስም፣ የወንዱ ብልት በሴቲቷ ብልት ውስጥ እንዲሰምጥ በማድረግ የተፈፀመ ግብረ ስጋ ግንኙነት

4 በፍላጎትና በምርጫ በመተሻሸት ወይም በእጅ በማባበልና በመሳሰሉት መንገዶች የፍቶት ጠብታን (የዘር ፍሬ ፈሳሽን) ማፍሰስ

በእንቅልፍ ልብ የሚከሰት የዘር ፍሬ መፍሰስ ጾምን አያበላሽም፡፡ አንድ ሰው ጾምን የሚያበላሹ ነገሮችን እንዳይፈጽም መጠንቀቅና ስሜቱን መቆጣጠር የሚችል ከሆነ ሚስቱን መሳም ይችላል፡፡

5 አውቆ ማስታወክ፡፡

ከቁጥጥር ውጭ በሆነ መልኩ ትውከት በራሱ ከወጣ ጾምን አያፈርስም፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ትውከት ያሸነፈው ጾመኛ፣ ጾሙን መክፈል አይጠበቅበትም፡፡ በፈቃዱ ያስታወከ ሰው ጾሙን ይክፈል፡፡›› (አል ቲርሚዚ 720 /አቡ ዳውድ 2380)

6 አበባና የወሊድ ደም መፍሰስ፡፡

የወር አበባ ወይም የወሊድ ደም በቀኑ የመጨረሻ ክፍል ላይም ቢሆን ከፈሰሰ ሴቷ ጾሟ ይበላሻል፡፡ በሌላም በኩል፣ በወር አበባ ደም ላይ ቆይታ ጎሕ ከፈነጠቀ በኋላ ብትጸዳና የዚያን ቀን ብትጾም፣ ጾሟ ትክክል አይሆንም፡፡ ያንን ቀን መጾም የለባትም፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹የወር አበባ ላይ በምትሆንበት ጊዜ አትሰግድም አትጾምም አይደል እንዴ?›› (አል ቡኻሪ 1850)

አንዲት ሴት ከተለመደው የወር አበባና የወሊድ ደም ውጭ በበሽታ ምክንያት ደም የሚፈሳት ከሆነ ከመጾም አትከለከልም፡፡

ትምህርቱን አጠናቅቀሃል


ፈተና ጀምር