መማርዎን ይቀጥሉ

ሎግ ኢን አላደረክም
መማር ለመጀመር፣ እድገትን ለመከታተል፣ ነጥቦችን ለመሰብሰብ እና ወደ ውድድር ለመግባት አሁኑኑ በታ ፕላትፎርም ይመዝገቡ፡ ከተመዘገቡ በኋላ ለሚማሯቸው ርዕሶች የኤሌክትሮኒክስ ሰርተፍኬት ይደርስዎታል።

የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል

ትምህርት ጾሙን እንዲያፈርሱ አላህ የፈቀደላቸው።

አላህ በረመዳን የተወሰኑ አይነት ሰዎች ለእነሱ ምህረት እና እዝነት ስባል ጾምን እንዲፈቱ ፈቅዷል። በዚህ ትምህርት ውስጥ ስለእነዚህ ዓይነቶች ሰዎች ታውቃለህ።

አላህ በረመዳን ጾምን እንዲፈቱ የፈቀደላቸው የሰዎች አይነት ማወቅ።

በችግር ምክኛት ጾምን እንድተው የተፈቀደላቸው

አላህ (ሱ.ወ) ከሰዎች መካከል ለተወሰኑ ሰዎች በረመዳን ወር አለመጾም እንዲችሉ ፍቃድ ሰጥቷል፡፡ ይህንንም ያደረገው ለነርሱ ከማዘን፣ ከማግራትና ከማቅለል አንፃር ነው፡፡ እኚህ ሰዎች የሚከተሉት ናቸው:-

1 በመጾሙ የሚጎዳ ታማሚ፡-

ለርሱ ማፍጠር ይፈቀድለታል፡፡ ከረመዳን በኋላ ሲሻለው ያፈጠረውን ይከፍላል፡፡

2 መጾም የማይችል ደካማ

በሽምግልና ወይም ይድናል ተብሎ በማይከጀል በሽታ ምክንያት መጾም የማይችል ደካማ ማፍጠር ይፈቀድለታል፡፡ ለእያንዳንዱ ቀን አንድ ሚስኪን ያበላል፡፡ ይኸውም፣ በሀገሩ ከሚበላ የምግብ ዓይነት አንድ ኪሎ ተኩል በመስጠት ይሆናል፡፡

3 የወር አበባና የወሊድ ደም ላይ ያሉ ሴቶች፡፡

በነኚህ ሁለት ሁኔታዎች ላይ ያሉ ሴቶች መጾም በነሱ ላይ እርም ነው፡፡ መጾማቸው ትክክለኛ አይደለም፡፡ ከረመዳን በኋላ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡

4 እርጉዝና አጥቢ፡፡

በራሳቸው፣ወይም በልጃቸው ላይ ጉዳትን ከሰጉ ወይም ከፈሩ፣ ማፍጠርና ቀኖቹን መክፈል ይችላሉ፡፡

5 ተጓዥ መንገደኛ

ተጓዥ መንገደኛ በጉዞው ላይ እያለ ከአራት ቀን ለማይበልጥ ጊዜ ሲያርፍ ማፍጠር ይችላል፡፡ ያንን ጾም የፈታበትን ቀን ከረመዳን በኋላ ሀገሩ ሲመለስ ይከፍላል፡፡

አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹በሺተኛ ወይም በጉዞ ላይ የኾነም ሰው ከሌሎች ቀኖች ቁጥሮችን (በልኩ) መጾም አለበት፡፡ አላህ በናንተ ገሩን (ይሻል) በናንተም ችግሩን አይሻም፡፡›› (አል በቀራ 185)

በረመዳን ጾሙን ያበላሸ ሰው ፍርዱ ምንድን ነው?

ማንኛውም ያለ በቂ ምክንያት ጾሙን ያበላሸ ሰው፣ ከባድ ወንጀል ፈጽሟል የፈጣሪውን ትዕዛዝ ጥሷል፡፡ ስለዚህም፣ በተውበት ወደ አላህ መመለስ ይኖርበታል፡፡ ጾሙን ያበላሸው በግብረ ስጋ ግንኙነት ካልሆነ፣ ከዚህ ከተውበቱ በተጨማሪ ያንን ጾም የፈታበትን ቀን መክፈል ይጠበቅበታል፡፡ ጾሙን የፈታው በግብረ ስጋ ግንኙነት ከሆነ ግን፣ ያንን ቀን መክፈል፣ እንዲሁም ለሠራው ወንጀል ማበሻ፣ ባሪያን ነፃ ማውጣት አለበት፡፡ ይህም፣ ሙስሊም ባሪያን በመግዛትና ከባርነት በማላቀቅ ይተገበራል፡፡ እናስተውል! ኢስላም፣ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ለሰው ልጅ ከባርነት ቀንበር ነፃ መውጣት ትኩረት ይሰጣል፡፡ ለምሳሌ አሁን እንዳለንበት ዘመን ዓይነት ባሪያን ነፃ ማውጣት የማይቻል ከሆነ፣ ሁለት ወሮችን በተከታታይ ይጾማል፡፡ ይህንንም ካልቻለ ስልሳ ሚስኪኖችን ያበላል፡፡

ትምህርቱን አጠናቅቀሃል


ፈተና ጀምር