መማርዎን ይቀጥሉ

ሎግ ኢን አላደረክም
መማር ለመጀመር፣ እድገትን ለመከታተል፣ ነጥቦችን ለመሰብሰብ እና ወደ ውድድር ለመግባት አሁኑኑ በታ ፕላትፎርም ይመዝገቡ፡ ከተመዘገቡ በኋላ ለሚማሯቸው ርዕሶች የኤሌክትሮኒክስ ሰርተፍኬት ይደርስዎታል።

የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል

ትምህርት የሱና ጾም

አላህ በዓመት ለአንድ ወር ጾምን ግዴታ ደነገገ፤ ነገር ግን ሰው ምንዳውን ያበዛ ዘንድ ሌሎች ቀናትን መጾም እንድችል ፈቀደ። በዚህ ትምህርት ስለ ሱና ጾም ዓይነቶች እና ስለ ትሩፈታቸው ትማራለህ።

ስለ አንዳንድ የሱና ጾም ዓይነቶች ማወቅ።ስለነዚህ ዓይነቶች መፆም ትሩፋቶች ማወቅ።

አላህ (ሱ.ወ) እንዲጾም ግዴታ ያደረገው በዓመት አንድ ወርን ብቻ ነው፡፡ ይሁን እንጂ የቻለና ፍላጎት ያለው፣ ከአላህ ተጨማሪ ምንዳን ለማግኘት የሚከጅል ሰው፣ ሌሎች ቀናትንም እንዲጾም ያበረታታል፡፡ ከነኚህ ቀናት መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡-

1 የዐሹራን ቀን

የዐሹራ ዕለት የሚባለው በኢሰላማዊው ቀመር መሰረት፣የወርሃ ሙሐረም አስረኛው ቀን ነው፡፡ ይህ ዕለት፣ አላህ(ሰ.ወ) ነብዩላህ ሙሳን(ዐ.ሰ) ከፈርዖን የገላገላቸውና፣ ፈርዖንን በባሕር ውስጥ ያሰጠመበት ዕለት ነው፡፡ ሙስሊሞች አላህ (ሱ.ወ) ነብዩላህ ሙሳን(ዐ.ሰ) ነፃ ስላወጣ፣ እርሱን ለማመስገንና የነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) ፈለግ ለመከተል ሲሉ ይጾሙታል፡፡ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ስለዚህ ዕለት ጾም ተጠይቀው፣ ‹ያለፈውን ዓመት ወንጀል ያስምራል፡፡›› ብለዋል፡፡ (ሙስሊም 1162) ከበፊቱ 9ኛውን ቀን መጾምም የተወደደ ነው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ ለሚቀጥለው ዐምት ከኖርኩኝ 9ኛውን እጾማለሁ" (ሙስሊም 1134)

2 የዐረፋ ቀን፡

ዐረፋ፣ የወርሃ ዙልሒጃ ዘጠነኛው ቀን ነው፡፡ ዙልሒጃ፣ በኢስላማዊ ቀመር መሰረት አስራ ሁለተኛው ወር ነው፡፡ ይህ ቀን ሐጃጆች ዐረፋ በሚባል ቦታ ላይ በመሰብሰብ አላህን ሲለምኑና ሲማጸኑ የሚውሉበት ዕለት ነው፡፡ ከዓመቱ ቀናት ሁሉ የላቀና የበለጠ ቀን ነው፡፡ ሐጅ ላይ ላልተሳተፈ ሰው ይህን ቀን መጾም ይወደድለታል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ስለ ዐረፋ ዕለት ጾም ተጠይቀው ሲመልሱ፡- ‹‹ያለፈውንና የመጪውን ዓመት ወንጀል ያስምራል፡፡›› ብለዋል (ሙስሊም 1162)

3 ስድስቱ የሸዋል ቀኖች፡

ሸዋል አስረኛው ወር ነው፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ረመዳንን የጾመ፣ ከዚያም ከሸዋል ስድስት ቀናትን አስከትሎ የጾመ ሰው፣ አንድ ዓመት ሙሉውን እንደጾመ ይቆጠርለታል፡፡›› (ሙስሊም 1164)

....................።

....................።

ትምህርቱን አጠናቅቀሃል


ፈተና ጀምር