የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት ትምህርት፡ ክረምት እና ንፅህና
የዝናብ ውሃ ንፁህ እና የሚያነፃ (ለመታጠቢያ የሚሆን) ነው። ሃያሉ አሏህ እንዲህ ይላል፡ "ከሰማይም አጥሪ ውሃን አወረድን።" (አልፉርቃን ፡48) ልክ እንደዚሁ በሙዕሚን ሰጋጅ ልብስ እና ጫማ ላይ ያረፈ የዝናብ ውሃ ፣ በአፈር ወይም በአስፓልት መንገድ ላይ የሚፈስ የዝናብ ውሃ ንፁህ ነው።
በብርዳማው የክረምት ወቅት ውዱዕ ማድረግ
ውሃው ቢቀዘቅዝም ወይም ቢሞቅም ውዱዕ (ከፊል ትጥበት) በደንብ ማድረግ አንዱ የአምልኮ (የኢባዳ) ተግባር ነው። የአሏህ ሶላት እና ሰላም በእሳቸው ላይ ይሁንና ነብያችን እንዲህ አሉ፡ "አሏህ ሃጢያትን የሚያብስበትን (የሚምርበትን) እና ደረጃን ከፍ የሚያደርግበትን ነገር አላመላክታችሁምን? አሉ። እነሱም አዎ ንገሩን የአሏህ መልዕከተኛ አሉ። እሳቸውም፡ ውዱዕ ማድረግ በከበደ ጊዜ ውዱዕ በደንብ ማድረግ ፣ ወደ መስጅድ (ሲሄዱ) እርምጃዎችን ማብዛት ፣ ከሶላት በኋላ ሶላትን (በጉጉት) መጠባበቅ፤ ያን ማወቅ (መጠንቀቅ) ነው አሉ።" (ሙስሊም 251) እናም ውዱዕ በደንብ ማድረግ ተሟላ ማለት ነው።
ውዱዕ ሲያደርጉ ከሚስተዋሉ ስህተቶች ውስጥ ቅዝቃዜውን በመፍራት እና ከእሱ ለመሸሽ ሲሉ የሰውነት ክፍልን በደንብ ያለማጠብ ቸልተኝነት ይታያል። ለምሳሌ አንዳንድ ሰዎች ፊታቸውን ሙሉ በሙሉ ያልታጠቡ ልታገኙ ትችላላችሁ ወይም ማበሱ ብቻ በቅቷቸው ሊሆን ይችላል። ወይም ደግሞ እጃቸውን ወይም እግራቸውን አሟልተው ያልታጠቡም ታገኛላችሁ። ይህ ግን አይፈቀድም። ማድረግ እስከቻለ ድረስ ውዱዕን አሟልቶ በደንብ ማድረግ ግዴታ ነው። ካልሆነ ግን አሙቆ እና መሰል ነገሮችን ተጠቅሞ ውዱዑን ያድርግ።
በክረምት ወቅት ውዱዕ ለማድረግ ውሃን ማሞቅ ይፈቀዳል። ይህ ምንዳውን (ሽልማቱን) አይቀንሰውም። ልክ ከውዱዕ በኋላ የአካል ክፍልን ማዳረቅ እንደተፈቀደው ይህን በማድረጉ ምንዳውን (ሽልማቱን) እንደማይቀንሰው ሁሉ ማለት ነው።......................
ተየሙም የሚያደርገው ሰው በእጆቹ (አፈር ያለበት) መሬቱን መታመታ በማድረግ በእጆቹ ፊቱን ያብሳል። ከዛም የቀኝ እጁን በግራ እጁ፤ የግራ እጁንም በቀኝ እጁ ያብሳል ማለት ነው።
ተየሙም የተፈቀደው ሙሉ በሙሉ ውሃ ከጠፋ ፣ ውሃ በጣም አስፈላጊ ሆኖ (ለመጠጥ ፣ ለምግብ) እጥረት ካጋጠመ እና በአቅራቢያ ምንም አይነት ውሃ ከሌለ ወይም ደግሞ በእሱ ውዱዕ በማድረግ ጉንፋኑ ወይም በሽታው የሚያባብስበት እስከሆነ ድረስ ነው።
እንደ ካልሲ ጥልቅ የሚል (ሁፍ) ላይ ማበስ፡ ጥልቅ የሚል እግርን የሚሸፍን ከቆዳ የተሰራ ጫማዎች ወይም ካልሲዎች ወይም ደግሞ መሰል ነገሮች ላይ ሲሆን ንፁህ ሆኖ ሙሉ እግርን የሚሸፍን እና ከትንሹ እና ከትልቁ ሐደስ (ብክለት-ንፅህና ጉድለት) የጠራ ከሆነ ነው። የላይኛውን የእግሩን ክፍል ካልሲው (ኹፉ) ላይ ማበስ በነው። ውዱዕ በሚያደርግ ጊዜ ራሱን እና እጆቹን ካበሰ ካልሱን (ሁፉን) ማውለቅ አይጠበቅበትም። ይልቁንም ከካልሲዎቹ ላይ የላይኛውን የእግሩ ክፍል ያብሳል።
በካልስ ላይ ማበስ እና የተፈቀደው
በካልስ ላይ የማበስ የጊዜ ገደብ
በካልስ ላይ የማበስ የጊዜ ስሌት የሚጀምረው መጀመሪያ ላይ ካልሱ ላይ ካበሰበት እና ተፈጥሯዊ ክስተት እስከ ሚፈፅምበት ያለው ጊዜ ነው።
በሁፍ (ካልሲ) ላይ ማበስ አይበቃም (አይፈቀድም)።ሙሉ ንፅህና ሳይኖራቸው የተለበሱ ከሆነ ፣ በነሱ ላይ የማበሻ ጊዜው እስካበቃ ወይም በንፅህና ጉድለት ምክኒያት ጉሱል (የገላ ትጥበት) ማድረግ ያለበት ሰው ከሆነ ማለት ነው። ይህ ከሆነ ካልሲውን አውልቆ እግሩን በማጠብ እራሱን ማንፃት ግዴታ ነው።