የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት በአላህ መኖር ማመን
በኃያሉ አላህ የማመን ትርጉም፡-
የኃያሉ አላህ መኖርን እውነት ብሎ አምኖ መቀበል ነው፡፡ ጌትነቱን፣ አምላክነቱን፣ ማረጋገጥ ነው፡፡ በስሞቹንና በባህሪያቱ ማመን ነው።
ለፈጣሪ ሁሉን ቻይ የመገዛት አንዱና ትልቁ መገለጫ ሱጁድ ነው።
በአላህ መኖር ማመን ሰው በተፈጥሮው የሚያረጋግጠውና ሌላ ተጨማሪ መረጃ የማያስፈልገው ነገር ነው፡፡ ይህ በመሆኑም ምንም የተለያየ ሃይማኖትና መንገድ ቢከተሉም በጣም በርካታ ሰዎች አላህ ለመኖሩ ዕውቅና ይሰጣሉ፡፡
የእርሱን መኖር የሚያረጋግጥ ጥልቅ የሆነ ስሜት በቀልባችን ይሰማናል፡፡ በተፈጥሮው አማኝ በሆነው ስሜታችን ገፋፊነት መጥፎና አስቸጋሪ ነገር ሲገጥመን ወደርሱ እንሸሻለን፡፡ አንዳንዶች ለመሸፋፈንና ለመዘናጋት ሙከራ ቢያደርጉም፥ አላህ በእያንዳንዱ ሰው ነፍስ ውስጥ ወደ ሃይማኖተኛነት የመዘንበል ስሜትን ፈጥሯል፡፡
እኛም አላህ ለተጣሪዎች ምላሸን ሲሰጥ፣ ለጠያቂዎች የጠየቁትን ሲቸር፣ ለተለማማኞች ፍላጎታቸውን ሲያሟላ ስለምናይና ስለምንሰማ፥ ይህ ሁኔታ አላህ ለመኖሩ እርግጠኛ መረጃ ይሆነናል፡፡
አላህ መኖሩ እጅግ ግልፅ የሆነ ነገር ነው፡ መረጃዎችን መዘርዘርም አያስፈልግም፡፡ ግልፅ ከሚያደርጉት ነገሮች ውስጥም፡-
• በሁሉም ሰው ዘንድ እንደሚታወቀው ማንኛውም ድርጊት አድራጊ ሊኖረው ግድ ነው፡፡ በየጊዜው የምንመለከተው ይህ እጅግ በርካታ ፍጥረት አስገኚና ፈጣሪ ሊኖረው ግድ ይላል፡፡ እርሱም ኃያሉና ታላቁ አላህ ነው፡፡ አንድ ፍጡር ያለምንም ፈጣሪ ተገኘ ማለት በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ ራሱን በራሱ ፈጥሯል ማለትም እንዲሁ አስቸጋሪ ነው፡፡ ምክንያቱም አንድ ነገር ራሱን በራሱ ሊፈጥር አይችልም፡፡ አላህ እንዲህ ይላል “ወይስ ያለ አንዳች ፈጣሪ ተፈጠሩን ወይስ እነርሱ ፈጣሪዎች ናቸውን?” (አልጡር፡35) በዚህ አንቀፅ መተላለፍ የተፈለገው መልእክት “እነርሱ ያለፈጣሪ አልተፈጠሩም፡፡ እነርሱም ራሳቸውን አልፈጠሩም፡፡ ስለዚህ ፈጣሪያቸው ሊሆን የሚችለው የተቀደሰውና ከፍ ያለው አላህ ነው” የሚል ነው፡፡
• ሰማዩ፣ ምድሩ፣ ከዋክብቱ፣ ዛፎቹና ይህ ፍጥረተ- ዓለም በአጠቃላይ የተመሠረተበት ሥርዓት ግልፅ በሆነ ሁኔታ የሚያሳየን ነገር ቢኖር፥ የዚህ ፍጥረተ- ዓለም ፈጣሪ አንድ ብቻ መሆኑን ነው፡፡ እርሱም ከፍ ያለውና ከጉድለት የጠራው አላህ ነው፡፡ “… የዚያን ነገሩን ሁሉ ያጠነከረውና የአላህን ጥበብ (ተመልከት)፡፡” (አል-ነምል፡88)
ክዋክብቶችን በምሳሌነት እንውሰድ፥ ፅኑ በሆነ አኳኋንና ስርዓት ነው የሚጓዙት፡፡ ሁሉም ኮከብ ያለምንም መሰናክልና መወላገድ በራሱ በሆነ ምህዋር ብቻ ይጓዛል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል “ፀሐይ ጨረቃን ልትደርስበት አይገባትም፤ ሌሊትም ቀንን (ያለ ጊዜው) ቀዳሚ አይኾንም፤ ሁሉም በመዞሪያቸው ውሰጥ ይዋኛሉ፡፡” (ያሲን፡40)