መማርዎን ይቀጥሉ

ሎግ ኢን አላደረክም
መማር ለመጀመር፣ እድገትን ለመከታተል፣ ነጥቦችን ለመሰብሰብ እና ወደ ውድድር ለመግባት አሁኑኑ በታ ፕላትፎርም ይመዝገቡ፡ ከተመዘገቡ በኋላ ለሚማሯቸው ርዕሶች የኤሌክትሮኒክስ ሰርተፍኬት ይደርስዎታል።

የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል

ትምህርት በነፍሶች ውስጥ አጉል እምነትን መዋጋት

እስልምና ጤናማ አፈጣጠር እና ጤናማ ኣእምሮ የሚስማማ ሀይማኖት በመሆኑ የሰዎችን ሀይማኖት እና አለማዊ ህይወት የሚያበላሹትን ሁሉንም አይነት አጉል እምነቶች እና ማታለያዎችን ይዋጋል። በዚህ ትምህርት ስለዚሁ ይማራሉ

  • እስልምና በአጉል እምነቶች እና ውዥንብር ላይ ያለውን አቋም ማወቅ።
  • በአንዳንድ የሐሰት እምነቶች የእስልምናን ፍርድ ማወቅ።

ከኢስላም በፊት ዐረቦች፣ እንዲሁም የዓለም ሕዝብ በአጠቃላይ የተረት ተረትና መሰረት የለሽ አመለካከቶችና ቅዠቶች ሰለባ ነበሩ፡፡ ይህ ደግሞ ምድርን ከጫፍ እስከ ጫፍ ያጥለቀለቃት፣ አንድ ሕዝብ ከሌላኛው ያልተሻለበት ሁኔታ ነበር፡፡ በመሆኑም፣ ዐረቦች በመጀመሪያ ሰሞን ቁርኣንን ተረት ተረት ወይም ድግምት ነው ብለው ገምተው ነበር፡፡

ኢስላም ብርሃኑን ይዞ በመጣ ጊዜ አዕምሮን ከመሰረት የለሽ አመለካከት፣ ከተረት ተረትና ቅዠት ቀንበር ነፃ አወጣው፡፡ ይህም የሆነው በሕግጋቱና ጥቅል መመሪያዎቹ ሲሆን፣ እነርሱም የአዕምሮንና የነፍስን ጤናማነት የሚጠብቁ እንዲሁም ከርሱ ሌላ ያለን በመተው ወደ አላህ ብቻ ወደ መንጠልጠል የሚያመላክቱ በመሆናቸው ነው፡፡

ድግምትና አስማተኝነትን መዋጋት

ኢስላም ድግምትን ሟርትንና ጥንቆላን በሙሉ እርም አድርጓል፡፡ የማጋራትና የጥመት ዓይነት አድርጎ መድቦታል፡፡ ድግምተኛ በቅርቢቱም ሆነ በወዲያኛው ዓለም ለስኬት እንደማይበቃ ተናግሯል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «ድግምተኛም በመጣበት ስፍራ ሁሉ አይቀናውም፡፡» ጦሃ 69

በአንድ ሙስሊም ላይ ወደ ድግምተኞች መሄድን፣ እነርሱን መጠየቅን፣ ከነርሱ በሽታ መፈወስን መከጀል፣ ወይም ሕክምና ወይም መፍትሄ መፈለግን እርም አድርጓል፡፡ ይህን ያደረገ ሰው በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ በተወረደው የካደ መሆኑንም ገልጿል፡፡ ምክንያቱም መጥቀምም መጉዳትም በአላህ እጅ ነው፡፡ የሩቅን ምስጢር ከርሱ ሌላ የሚያውቅ የለም፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- «አንድን ጠንቋይ የመጣና የጠየቀው ከዚያም እውነት ብሎ የተቀበለው ሰው በርግጥ እሱ በሙሐመድ ላይ በተወረደው ክዷል፡፡» ሃክም 15

መጥቀምና መጉዳት በአላህ እጅ ነው፡፡

ኢስላም ፍጡራን በጠቅላላ፣ ሰውም፣ ዛፎችም፣ ድንጋዮችም፣ ከዋክብትም፣ ምንም ያህል ቢገዝፉም፣ የአላህን ኃያልነት የሚያስረዱ ምልክቶች እንጂ ሌላ አለመሆናቸውን ገልጿል፡፡ ከሰው ልጅ አንድም በፍጥረተ-ዓለም ላይ ጫና ሊያሳድር የሚችል፣ አስደናቂ ኃይል ያለው የለም፡፡ መፍጠር፣ ማዘዝና ማዘጋጀት በርሱ ትዕዛዝ ስር ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «ንቁ! መፍጠርና ማዘዝ የርሱ ብቻ ነው፡፡ የዓለማት ጌታ አላህ ላቀ፡፡» (አል-አዕራፍ፡ 54)

የእነዚህን ፍጥረታት ግዝፈትና [ቂቅ አፈጣጠራቸውን ያስተዋለ ሰው፣ ፈጣሪያቸው ቻይና አስተናባሪ ጌታ መሆኑን ይገነዘባል፡፡ ስለሆነም እርሱ የአምልኮ ዓይነቶች በሙሉ ሊፈፀሙለት የሚገባ እንደሆነም ያውቃል፡፡ እርሱ ፈጣሪ ነው፡፡ ከርሱ ሌላ ያለ ሁሉ ፍጡር ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «ሌሊትና ቀንም ፀሐይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው፡፡ ለፀሐይና ለጨረቃ አትስገዱ፡፡ ለዚያም ለፈጠራቸው አላህ ስገዱ፤ እርሱን ብቻ የምትገዙ እንደኾናችሁ (ለሌላ አትስገዱ)፡፡» ፉስለት 37

ስውርንና የወደፊትን ከአላህ ሌላ ማንም አያውቅም፡፡

ኢስላም ከአላህ ሌላ ስውርንና የወደፊትን የሚያውቅ እንደሌለ ተናግሯል፡፡ ከጠንቋይም ሆነ ከሟርተኞች መካከል ይህን አውቃለሁ ብሎ የሚል ውሸታምነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «የሩቅ ነገርም መክፈቻዎች እርሱ ዘንድ ናቸው፡፡ ከርሱ በስተቀር ማንም አያውቃቸውም፡፡»

ከፍጡራን ሁሉ የተከበሩትና የላቁት ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) እንኳን ለራሳቸው ጉዳትንም ሆነ ጥቅምን አያስገኙም፡፡ ስውርና የወደፊትንም የሚያውቁ አልነበሩም፡፡ በክብርም ሆነ ደረጃ ከርሳቸው በታች የሆነማ እንዴት (ሊያውቅና ሊኖረው) ይችላል?!! አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- «አላህ የሻውን በስተቀር ለራሴ ጥቅምንም ጉዳትንም ማምጣት አልችልም፡፡ ሩቅንም (ምስጢር) የማውቅ በነበርኩ ኖሮ ከመልካም ነገር ባበዛሁና ክፉም ነገር ባልነካኝ ነበር፡፡ እኔ ለሚያምኑ ህዝቦች አስፈራሪና አብሳሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም በላቸው፡፡» (አል-አዕራፍ፡ 188)

ኢስላም በአዕዋፍ ገድ ማለትንና ማሟረትን እርም አድርጓል፡፡

ኢስላም በአዕዋፍ፣ በመልክ፣ በንግግርና በተለያዩ ነገሮች ገድ ማለትን፣ ማሟረትንና መሰል ነገሮችን እርም አድርጓል፡፡ መልካም ምኞትንና ለመጪው ብሩህ ተስፋና አመለካከት ማሳደርን አዟል፡፡

በአዕዋፍ ገድ የማለት ምሳሌ፡- አንድ የወፍ ዓይነትን ሲመለከት፣ ከመንገዱ ወይም ከጉዞው በማሟረት የሚስተጓጎል ወይም የሚቀር፣ ወይም የወፉን ድምፅ በጉዞ ላይ ሆኖ ሲሰማ ጉዞውን ሳያጠናቅቅ አቋርጦ መመለስ ገድን በወፍ የመተንበይ ምሳሌ ነው፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እነኚህ ነገሮች ማጋራት(ሺርክ) እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ «በአዕዋፍ ገድ ማለት ማጋራት ነው፡፡» (አቡዳውድ 3912፣ ኢብኑ ማጃህ 3538) ምክንያቱም ይህ ነገር አንድ ሙስሊም ውስጥ ከሰረፀ፣ አላህ የፍጥረተ-ዓለም አስተናባሪ ነው፤ የሩቅን የሚያውቅ እርሱ ብቻ ነው፤ ከርሱ ሌላ ማንም አያውቅም ከሚለው እምነቱ ጋር ይቃረናል፡፡

በዚህ ተቃራኒ ደግሞ ኢስላም መልካም ግምትንና ጥሩን መጠበቅን፣ በአላህ ላይ መልካም ግምት ማሳደርን አዟል፡፡ ይህን የሚጠቁሙ ቃላቶችን ምርጫ ማድረግ እንዳለብንም ነግሯል፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) መልካም ምኞትን ወይም ግምትን ይወዱ ነበር፡፡ እሱም መልካም ቃል ነው፡፡ (አህመድ 8393)

ትምህርቱን አጠናቅቀሃል


ፈተና ጀምር