የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት አራጣ (ወለድ)
ከሃያሉ አሏህ ጥበብ መካከል አራጣን በእስልምና ህግ ውስጥ ከትልልቅ ወንጀሎች ውስጥ አንዱ ማድረጉ ነው። ከእኛ በፊት በነበሩ ህዝቦች ላይም እርም ተደርጓል (ተከልክሏል)። ምክኒያቱም በማህበረሰቡ እና በአባላቶቹ ላይ ከፍተኛ ጥፋት እና ውድመትን ስለሚያስከትል ነው። አሏህ እንዲህ አለ፡ "(160) ከእነዚያ ይሁዳውያን በሆኑትም በተገኘው በደል ሰዎችንም ከአሏህ መንገድ በመካከላቸው በብዙ ምክኒያት ለእነሱ ተፈቅደው የነበሩትን ጣፋጭ ምግቦች በእነሱ ላይ እርም አደረግንባቸው። (161) ከእሱ በጥብቅ የተከለከሉ ሲሆኑ አራጣንም በመያዛቸውና የሰዎችን ገንዘብ ያለ አግባብ በመብላታቸው ምክኒያት እርም አደረግንባቸው (ከለከልናቸው)።" (ሱረቱ ኒሳእ 160-161)
የአራጣን አሳሳቢነት ከሚያሳዩት መካከል አራጣን በሚጠቀሙ ሰዎች ላይ ያደረሰው ዛቻ ነው። በእርግጥ አሏህ እንዲህ አለ፡ "(278) እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አሏህን ፍሩ። ከአራጣም የተቀረውን ተው። አማኞች እንደሆናችሁ ተጠንቀቁ። (279) የታዘዛችሁትን ባትሰሩ ከአሏህ እና ከመልዕክተኛው በሆነች ጦር መወጋታችሁን እወቁ።" (ሱረቱል በቀራ 278-279) ሆኖም ሃያሉ አሏህ አራጣን (ወለድን) ከልክሏል፤ ባለቤቷንም በጦር ዝቶበታል።
ከዚህ በተጨማሪ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መከልከሉ ላይ ትልቅ አፅንኦት እና ከባድ ዛቻ ሰጥተዋል። ጃቢር (ረ.ዐ) እንዲህ አለ፡ ‹‹የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) አራጣ ተቀባዩን ፣ ከፋዩን ፣ መዝጋቢዋን እና ሁለቱን ምስክሮች ረግመዋል። እናም አሉ፡ ‹‹እነሱ ሁሉም እኩል ናቸው።›› (ሙስሊም 1598)
የአራጣ ትርጉም
የወለድ ትርጉም
የአራጣ አይነቶች
ሪባ አል-ፈድል (የማበላለጥ አራጣ)
የብድር አራጣ
የአራጣ ብያኔ
የአራጣ ክልከላ ጥበብ
2 ያለ ሃሳብ ገቢ ማግኘትን ይከለክላል፡ እስልምና ሁለት ወገኖች ጥቅም በሚያገኙበት መልኩ የገነዘብ ለውውውጥን ይቆጣጠራል። ሁለቱም የሆነ ነገር አስተዋፅኦ ማድረግ እና በመልሱ የሆነ መገር መውሰድ አለባቸው። ይህ ደግሞ በአራጣ ውስጥ የለም።
3 አራጣ በሰዎች መካከል ያለውን መልካም ነገር የሚያጠፋ ነው። ይህ ደግሞ ውለታን ፣ በመካከላቸው በጎ ስራን እና ቅንነት በማስፋፋት ውስጥ የእስልምና አላማ ጋር የሚቃረን ነው።
4 ብዝበዛን ይከላከላል፡ አበዳሪው ብዙ ጊዜ አራጣን በመጫን የተበዳሪውን ፍላጎት ደህና አድርጎ ይበዘብዛል።
5 ኢፍትሃዊነትን ያስቀራል፡ አራጣ አንደኛው ወገን የሚቸገርበት እና የሚበዘብዝበት ኢፍትሃዊነት ነው። አሏህ ሁሉንም የኢፍትሃዊነት (የበደል) አይነቶች ከልክሏል።
አራጣ የሚያደርሰው ጉዳት
1 የግብረገብ እና መንፈሳዊ ጉዳት
አራጣ ማህበረሰቦችን ከሚያጠፉ ነገሮች ውስጥ አንዱ ነው። አንድን ማህበረሰቦችን የተፈረካከሱ እና የተበታተኑ ያደርጋቸዋል። በእሱ ውስጥ ጠንካራው ደካማውን ያደቀዋል። አንድም ሰው ጎረቤቱን አይረዳም፤ ይህን በማድረጉ ጥቅም የሚያገኝበት ካልሆነ በቀር።