የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት ወቅፍ (ችሮታ)
አሏህ ትልቅ ሃብት የሰጣቸው አንዳንድ ሃብታም እና ከበርቴ ሰዎች ከጥሪያቸውን የማይለወጥ እና ሁልጊዜም አገልግሎት የሚሰጥ ልክ እንደ መሬት እና የጋራ መኖሪያ ቤት ያለ ቋሚ ነገር ሰርተው ይሰጣሉ። ይህም በህይወት እያሉም ሆነ ከሞቱ በኋላ በስማቸው መልካም ስራዎች እንዲኖራቸው ያደርጋል። ይህ ችሮታ ለተቸገሩ ሰዎች ትልቅ ጥቅሞችን ያስገኛል።
የአሏህን ምንዳ (ሽልማት) በመፈለግ የአንድን ንብረት ባለቤትነት የህዝብ በማድረግ ሁሉም ሰው እንዲገለገልሉበት ማድረግ ነው።
የወቅፍ ሁክም
ወቅፍ (ችሮታ) የተወደደ ተግባር ነው። ከምፅዋት ሁሉ በላጩ ነው። ከላቁ እና ጠቃሚ ከሆኑ የበጎ አድራጎት ስራዎች መካከል አንዱ ነው። ምክኒያቱም ከሞት በኋላ ከማያቆሙ (ከማይቋረጡ) ስራዎች አንዱ ነውና።
የወቅፍ (የችሮታ) ጥበብ
ወቅፍን በሃይማኖት ጉዳይ ውስጥ ፣ በዱናያ ህይወት እና በመጭው አለም ህይወት ብዙ ጥቅሞች ያሉት በመሆኑ አሏህ ደንግጎታል። አንድ የአሏህ ባሪያ ገንዘቡን ለአሏህ ብሎ በመስጠቱ ምንዳውን ይጨምርለታል፤ ከሞተም በኋላ መልካም ስራው ይቀጥላል። ከዚህ በተጨማሪ የችሮታው ተጠቃሚዎች አገልግሎቱን ሲያገኙ ዱአ ያደርጉለታል። ማህበረሰቡም አንድነቱን ያጠናክራል።
ከምፅዋቶች ሁሉ በላጩ ነው። ምክኒያቱም ዘላቂ ነውና። የበጎ አድራጎት እና የቸርነት ስራ ላይ የዋለ የማይለወጥ የምፅት ስጦታ ነው።
አሏህ እንዲህ አለ፡ "የምትወዱትን እስከምትለግሱ ድረስ በጎ ስራን አታገኙም። ከምንም ነገር ብትለግሱ አሏህ ያውቀዋል።" (ሱረቱል ኢማራን 92)
ኢብን ኡመር (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ፡ ኡመር ቁራጭ መሬት ኸይበር ውስጥ ባገኘ ጊዜ ወደ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መጣና ‹‹አግንቸው ከማላቀው የበለጠ ቁራጭ መሬት አገኘሁ አለ። እናም እሱን በተመለከተ ምን ትመክሩኛለሁ ሲልም ጠየቀ። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አሉ፡ ከፈለክ ለበጎ አድራጎት አላማ እንዲውል እንደ ችሮታ (ወቅፍ) ልታውለው ትችላለህ። ይህን ተከትሎ ኡመር መሬቱን በበጎ አድራጎት መልክ ሰጠ። (ያ ማለት ላይሸጥ ፣ ላይለወጥ እና በስጦታ መልክ ላይሰጥ ነው) አገልግሎቱ የሚውለው ለድሆች ፣ ለሚስኪኖች ፣ ባሪያዎችን ነፃ ለማውጣት ፣ ለጅሃድ እና ለእንግዶች እና ለመንገደኖች ማረፊያ ነው። ንብረቱን የሚያስተዳድረው ሰው ከሱ የሚበላው ምክኒያታዊ እና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ነው። እንዲሁም በማንኛውም መንገድ ሃብታም ለመሆን ሳያስብ ጓደኞቹንም መመገብ ይችላል።›› (ቡኻሪ 2772 ፣ ሙስሊም 1632)
የወቅፍ (የችሮታ) ክፍሎች
ለምሳሌ መስጅድ ፣ ለእውቀት ፈላጊ ተማሪዎች ትምህርት ቤት ፣ ለድሆች ፣ ለወላጅ አልባ ልጆች እና ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶች (ለእመበለቶች) የጋራ መኖሪያ ቤት ሰርቶ መስጠት ነው።
ቤት ሰርቶ ለወራሾቹ እንደሚቸር ወይም አንድን የእርሻ ማሳ እና ምርቱን እንደሚቸር ሰው ነው።
ወቅፍ (ችሮታ) ተፈፃሚነት እና ህጋዊነት የሚኖረው በሁለት መንገዶች ነው።
የወቅፍ (የችሮታ) ቅድመ ሁኔታዎች
ችሮታው ልዩ የዋጋ ተመን አይኖረውም። ይልቁንም የዋጋ ተመኑ የሚወሰነው እነደ ሃብቱ እና እንደ ገንዘቡ አቅም ነው። ሆኖም ሃብታም የሆነ እና ወራሽ የሌለው ሰው ሁሉንም ሃብቱን ለወቅፍ ማዋል ይችላል። ሃብታም ሆኖ ወራሽ ያለው ደግሞ ከሃብቱ ከፊሉን ለወቅፍ ከፊሉን ለወራሾቹ ማዋል ይችላል።
ወቅፉ(ችሮታው) ፍፁም ፣ ዘላቂ እና አሏህን ለማስደሰት ተብሎ መሆን አለበት። ሆኖም ለዚ ያህል ጊዜ ተብሎ የጊዜ ገደብ አይኖረውም። መሬትን ፣ ቤትን ወይም የእርሻ ማሳን ለወቅፍ ብሎ ያዋለ ሰው የዚህ ንብረት ባለቤት አይሆንም። አይሸጥም ፣ አይለውጥም ፣ ለውርስ ተብሎ አይተላለፍም፤ እንዲሁም ወቅፉ ብሎ የሰጠ ሰው ውሳኔ እንደገና ያስብበት ሊባል አይችል። ልክ እንደዚሁ ወራሹ ሊሸጠው አይችልም። ምክኒያቱም የሟቹ ሰው ንብረት አይደለምና፤ ምንም እንኳ ከፊሉን ንብረት ቢወርስም ማለት ነው።
አንድ ሰው ወቅፍን (ችሮታን) ሰጥቻለሁ ብሎ የተናገረ ወይም ችሮታውን የሚያመላክት ስራ የሰራ ሰው ወቅፉ የፀና ነው። ወቅፉን የሰጠው ሰው ተገልጋዮቹ ማን እንደሆኑ የመቀበል ወይም ሃላፊነቱን የተቀበለው ሰው ፈቃድ ማግኘት አያስፈልግም።
ሃያሉ አሏህ መልካም ነው የሚቀበለውም መልካም ነገርን ነው። ሆኖም አንድ ሙስሊም ሰው አሏህን ለማስደሰት ብሎ ንብረቱን ለወቅፍ ማዋል ሲፈልግ ከንብረቱ ሁሉ በላጩን ፣ ለእሱ በጣም ውድ እና አብልጦ የሚወደውን መሆን አለበት። ይህን በማድረጉ የበጎ አድራጎትን እና የልግስና የመጨረሻውን ሞገስ ያገኛል።
ምርጥ ችሮታ ማለት ብዙ ሙስሊሞች በሁሉም ቦታ እና ጊዜ የሚገለገሉበት ነው። ለምሳሌ መስጅድ ፣ ትምህርት ቤት (መድረሳ) ፣ በአሏህ መንገድ የተዋደቁ ሙጃሂዶች ፣ ዘመድ አዝማድ ፣ ድሆች እና ለአቅመ ደካማ ሙስሊሞች የሚያገለግሉ እና ሚያርፉበት ቤቶች ናቸው።