የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት የሴቶች መብት በእስላም
የእስልምና ሃይማኖት በመለኮታዊ አስተምህሮቶቹ እና ጥበባዊ በሆነው መመሪያው ሙስሊም ሴትን ይንከባከባል ፣ ክብሯን ይጠብቃል ፣ ልቅናዋን እና ደስታዋን አረጋግጦላታል ፣ ከጥርጣሬ ፣ ከፈተና እና ከክፉ ነገር ሁሉ አርቆ ምቹ እና የተደላደለ ህይወትን አዘጋጅቶላታል። ይህ እንክብካቤ ብዙ መልክ እና ቅርፅ አለው።
የሴት ልጅ ክብር እና ከፍ ያለ ደረጃ
ኡመር ኢብን ኸጧብ (ረ.ዐ) እንዲህ አለ፡ ‹‹በአሏህ ይሁንብኝ በጃሂልያ ውስጥ ሴቶችን እንደ ጉዳይ አንቆጥራቸውም ነበር። አሏህ የገለጠውን ነገር እስኪገልጥ ድረስ እና የሰጠውንም እስኪሰጥ ድረስ።›› (ቡኻሪ 4913 ፣ ሙስሊም 1479) የእስልምና ብርሃን ብቅ ያለው ከ1400 አመት በፊት ነው። ሆኖም የሴትን ልጅ ደረጃ ከፍ አድርጓል። በእነሱ ላይ የተቃጣን በደል ሁሉ ሽሯል። ከእነዚህ በደሎች እና ኢፍትሃዊነት መካካል የንብረት ባለቤት የመሆን እና ውርስ መውረስ ይከለከሉ ነበር። ሚስት ባሏ ከሞተ በኋላ ትወረስ ነበር። እንዲሁም ከአስክሬኑ ጋር አብራ እንድትቃጠል እና እንድትቀበር ይደረግ ነበር። ከዚህ በተጨማሪ ትሸጥ ትለወጥ ነበር። ይህ ተግባር እስከ ሃያኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ድረስ በእንግሊዝ ውስጥ መተግበሩን ቀጥሎ ነበር።
የወንዶች እና የሴቶች እኩልነት
በመሰረታዊ አፈጣጣር
እስልምና ወንዶች እና ሴቶችን በሃይማኖታዊ ተግባራት እና ግዴታዎች ፣ በሽልማታቸው እና በቅጣታቸው በዚህ አለም እና በመጭው አለም ህይወት እኩል አድርጓቸዋል። አሏህ እንዲህ አለ፡ "ከወንድ ወይም ከሴት አማኝ ሆኖ በጎ የሰራን መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን። ይሰሩትም ከነበሩት ነገር በመልካም ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን።" (ሱረቱ ነህል 97) ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡ "ከወንድ ወይም ከሴት እሱ አማኝ ሆኖ ከበጎ ስራዎች አንዳችን የሚሰራም ሰው እነዚያ ገነትን ይገባሉ። በተምር ፍሬ ላይ ያለችን ነጥብ እንኳ አይበደሉም።" (ሱረቱ ኒሳዕ 124) በአንድ ወቅት ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በህልሙ ግኑኝነት ያደረገ መሆኑን ሳያስታውስ ረጥቦ ስለ ተነሳ ሰው ተጠይቀው ሲመልሱ እንዲህ አሉ፡ ‹‹መታጠብ ይገባውል አሉ።›› በህልሙ ግኑኝነት ሲያደርግ አይቶ ነገርግን ምንም አይነት ምልክት ስላላገኘ ሰው ተጠይቀው ሲመልሱ ደግሞ እንዲህ አሉ፡ ‹‹መታጠብ አይጠበቅበትም አሉ።›› ኡሙ ሱለይም ‹‹ሴት ያን ካየችስ ገላዋን ትታጠባለችን?›› አለች። እሳቸውም ‹‹አዎ! ሴቶች የወንዶች እህቶች ናቸው›› አሉ።›› (አቡዳውድ 236)
በአሏህ መልዕክተኛ መልዕክት ያመነችው የመጀመሪያዋ ሴት ነበረች። እሷም የሙዕሚኖች እናት የሆነችው ኸድጃ (ረ.ዐ) ናት። ሴቶች ወደ ሀበሻ የተደረገውን የመጀመሪያ ስደት ተጋርቷል፤ ከየስሪብ መቶ ነቢይን ቃልክዳን የገባ ልኡካን ቡድንም ተጋርቷል
በእስልምና ታሪክ ውስጥ ሴቶች ደማቅ እና አንፀባራቂ ምሳሌን ፅፈው አልፈዋል። በመልካም ባህሪያቶቻቸው ፣ ጥልቅ በሆነ እውቀታቸው እና የእስልምናን መልዕክት በመረዳት አቅማቸው በደንብ ይታወቃሉ። በተለያዩ ዘርፎች ፣ በሃይማኖታቸው ፣ በሳይንስ እና በትምህርት የላቁ ስመጥሮች ነበሩ። ከእነሱ መካከል ደግሞ በጣም የምትታወቀው የምዕመናን እናት የሆነቸው አኢሻ (ረ.ዐ) ናት።
ሴቶች ልክ እንደ ሐጅ እና ኡምራ ሁሉ ግዴታ ፣ የተወደደ እና የተፈቀደ በሚለው ሁክም መሰረት በህብረት ሶላት ፣ የዝናብ ልመና ሶላት ፣ በሁለቱ ኢዶች በጀመአ (ህብረት) ሶላት ፣ በጁምአ ሶላት ከወንዶች ጋር አብረው ይሳተፋሉ። ከዚህ በተጨማሪ ወደ እስልምና ጥሪ እንዲያደርጉ ፣ በመልካም እንዲያዙ እና ከመጥፎ ነገር ሁሉ እንዲከለክሉ ታዘዋል። ብዙ ሃይማኖታዊ ተግባራትን እንዲፈፅሙ ታዘዋል። ይህ የሚያመለክተው ሁለቱም ፆታዎች በሃይማኖት ጉዳይ እኩል መሆናቸውን ነው። ብቸኛው ልዩነታቸው በእነሱ መካከል ያለው አካላዊ ጾታዊ አፈጣጠር ጋር የተያያዘ ልዩነት ብቻ ነው።
የእኩልነት መርህ በሃይማኖታዊ ተግባራት ውስጥ ሁለቱ ፆታዎች እንደጥቅል በተቀመጡ በተፈጥሮ ያላቸውን ልዩነትም ከግምት ውስጥ ያስገባል። ከዚህ የሚገኘው ውጤት በተልዕኮዎቻቸው መለያየት ነው። እያንዳንዱን ግለሰብ በትክክለኛው እና በሚገባው ቦታ ላይ ያስቀምጣል። ይህ ደግሞ በህይወት ውስጥ ውህደትን ይፈጥራል። ወንድ የሴትን እና የልጆችን ወጭ የመሸፈን ግዴታ አለበት። እነሱን መጠበቅ እና ቤተሰቡን መንከባከብ አለበት። ሴት ደግሞ በቤቷ ፣ በባሏ እና በልጆቿ ላይ ሃላፊነት አለባት። ልትወጣው የሚገባ የራሷ የሆነ ሃላፊነት አለባት።
እስልምና ከ1400 አመታት በፊት መልዕክቱ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ለሴቶች የተረጋገጡትን የዜጎች ፣ የማህበራዊ እና የግል መብቶቻቸውን ሰጥቷቸዋል፡፡ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በዚህ ዘመን ለሴቶች መብት ጥብቅና ከመቆማቸው በፊት እስልምና ለሴቶች ዋስትና ሰጥቷል።
የሴቶች የሲቪል እና የማህበራዊ መብቶች
የሴት ልጅ መብቶች በግል እና በትዳር ጉዳይ ውስጥ
ከላይ የተጠቀሱት ሴቶች በእስልምና ውስጥ ያላቸውን መብት የሚያንፀባርቁ ምሳሌዎች ናቸው። ከዚህ ባሻገር እስልምና ለሴቶች ያጎናፀፋቸው መብቶች በጣም በርካታ ናቸው።