የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት የኢስቲንጃ ሥነ-ስራዐት እና መጸዳዳት
የመጸዳዳት ስርዓት
አንድ ሰው ሽንት ቤት ሲገባ፣ ግራ እግሩን ማስቀደምና ‹‹ቢስሚላህ፣አላሁመ ኢኒ አዑዙ ቢከ ሚነል ኹቡሲ ወል ኸባኢስ›› - በአላህ ስም፣ አምላኬ ሆይ ከእርኩሱና ከእርኩሲቷ (ሰይጣን) በአንተ እጠበቃለሁ- ማለቱ ይወደዳል፡፡
አንድ ሙስሊም በሚጸዳዳበት ጊዜ ሀፍረተ ገላውን ከሰዎች እይታ የመከለል ግዴታ አለበት፡፡
ሰዎች በቆሻሻው በሚጎዱበት ስፍራ መጸዳዳት ክልክል ነው፡፡
የሚጸዳዳው ከቤት ውጭ ባለ መስክ ውስጥ ከሆነ፣ እርሱ ሊጎዳቸው ወይም እነሱም ሊጎዱት የሚችሉ ነፍሳት የሚኖሩበት በሆነ ጉድጓድ ውስጥ መጸዳዳት ክልክል ነው፡፡
የሚጸዳዳው በሜዳ ላይ ከሆነና የሚከልለው ግርዶሽ የሌለ ከሆነ፣ ፊቱን ወደ ቂብላ ማዞር ወይም ለቂብላ ጀርባውን መስጠት አይገባውም፡፡ ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ)፡- «በምትጸዳዱበት ጊዜ፣ ስትሸኑም ሆነ ዓይነምድር ስታስወግዱ፣ ፊታችሁን ወደ ቂብላ አታዙሩ ጀርባችሁንም ለቂብላ አትስጡ፡፡» ብለዋል፡፡ (አል ቡኻሪ 386/ ሙስሊም 264)
የሚፈናጠሩና የሚረጩ ነጃሳዎች ልብሱና ሰውነቱን እንዳይነኩት ጥንቃቄ ማድረግ፣ ከነኩት ደግሞ የማጠብ ግዴታ አለበት፡፡
ተጸዳድቶ ሲያበቃ ከሁለት አንድ ነገር መፈፀም አለበት
የሽንትና የዓይነምድር መውጫ አካሎቹን በውሃ ማጠብ (ኢስቲንጃእ)
እስትጅማር ማለት በሶስት ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ ደንጋዮች፣ ለስላሳ የመጸዳጃ ወረቀቶች፣ ወይም ሰውነቱን ከነጃሳ ሊያጸዳለት በሚችል መሰል ነገር ማጽዳት ነው፡፡
ሐደስ (ምናባዊ ቆሻሻ)
ሐደስ፡ ማለት ምናባዊ የሆነ፣ ሰው ከርሱ ከመጥራቱ በፊት ሠላት መስገድን የሚከለክል ነገር ነው፡፡ እንደ ነጃሳ በግልፅ የሚነካ ነግር አይደለም፡፡
ሐደስ ከአንድ ሙስሊም ላይ የሚወገደው ሊያጠራ በሚችል ውሃ ወዱእ ሲያደርግ ወይም ገላውን ሲታጠብ ነው፡፡ ሊያጠራ የሚችል ውሃ የሚባለው ነጃሳ ነክቶት መልኩን ወይም ጣዕሙን ወይም ሽታውን ያልቀየረው ውሃ ነው፡፡
ሐደስ በሁለት ይከፈላል፡፡
ትንሹ ሐደስና ከሱ ውዱ መድረግ
አንድ ሙስሊም ምናባዊ ጸዱዕነቱን አጥቶ ውዱእ ማድረግ የግድ የሚሆንበት ከሚከተሉት ነገሮች አንዱ በሚከሰበት ጊዜ ነው፡፡
1 ሽንት፣ ዓይነምድርና ማንኛውም ከሁለቱ መጸዳጃ ብልቶች የሚወጣ ንፋስና መሰል ነገሮች ከወጡ፡፡ አላህ (ሱ.ወ) ጽዱዕነትን የሚያፈርሱ ነገሮችን ሲዘክር፡- «ወይንም ከናንተ አንዱ ከዓይነምድር ቢመጣ» ብሏል፡(ኒሳእ 43)። ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ) በሠላት ውስጥ ሆኖ ሐደስ እንደተከሰተበት የተጠራጠረን ሰው በማስመልከት፡- «ድምጽ እስካልሰማ ወይም ሽታ እስካለገኘ ድረስ አቋርጦ አይሂድ!» ብለዋል፡፡ (አል ቡኻሪ 175/ ሙስሊም 361)
2 ያለግርዶ በስሜት ብልትን መንካት፡ ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ)፡- «ብልቱን የነካ ሰው ወዱእ ያድርግ» ብለዋል፡፡ (አቡ ዳውድ 181)
3 የግመል ስጋ መብላት፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)፣ «የግመል ስጋን በመብላቴ ውዱእ ላድርግን?» የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው፣ «አዎን» በማለት መልስ ሰጥተዋል፡፡ (ሙስሊም 360)
4 አእምሮ በእቅልፍ ወይም በአእምሮ ህመም ወይም በስካር መሳት