የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት የሶላት አሰጋገድ
1 ማሰብ (ኒያ)
ለሠላት እንደቆመ አላሁ አክበር (አላህ ትልቅ ነው፡፡) ይላል፡፡ በዚህን ጊዜ፣ የውስጥ መዳፉን ወደ ቂብላ አቅጣጫ በማዞር፣ እጁን በትከሻው ልክ ወይም በጆሮው ልክ ከፍ ያደርጋል፡፡
የአላሁ አክበር ትርጉም
3 አላሁ አክበር ካለ በኋላ፣ ቀኝ እጁን በግራ እጁ ላይ በማነባበር በደረቱ ላይ ያስቀምጣል፡፡ ምንጊዜም ሲቆም ማድረግ ያለበት ይህንን ነው፡፡
7 የፋቲሓን ምዕራፍ ያነባል፡፡ ፋቲሓ በአላህ መፅሐፍ ውስጥ ባለው ክብርና ደረጃ ታላቁ ምዕራፍ ነው፡፡
ሙስሊም ሁሉ ይህንን ምዕራፍ መማር አለበት፡፡ ምክንያቱም፣ ብቻውን ወይም ኢማሙ ድምጹን ከፍ አድርጎ በማያነብባቸው ሠላቶች ውስጥ ተከታይ ሆኖ የሚሰግድ ሰው፣ በሠላቱ ውስጥ እሷን ማነብነቡ ከሠላት ማዕዘናት መካከል አንዱ በመሆኑ ነው፡፡
የፋቲሓ ምዕራፍ
10 ከዚያም፣ ልክ በመጀመሪያው ተክቢራ ላይ እንዳደረገው እጆቹን በትከሻዎቹ ትክክል ወይም ትንሽ ከፍ አድርጎ በማንሳትና የመዳፎቹን ውስጣዊ ክፍልዳ ቂብላ በማቅጣጨት ለሩኩዕ ‹‹አላሁ አክበር›› ይላል፡፡
11 በመዳፎቹ ጉልበቶቹን በመያዝ ወደ ቂብላ እንደተቅጣጨ ከወገቡ ጎንበስ በማለት ሩኩዕ ያደርጋል፤ ጭንቅላቱና ወገቡ ወጣ ገባ መሆን የለበትም፤ እንዲህም ይላል፡ - ‹‹ሱብሓነ ረቢየል ዐዚም›› (ታላቁ ጌታዬ ከእንከንና ከጉድለት ጠራ፡፡) ይህን ውዳሴ ሦስት ጊዜ መደጋገም የተወደደ ነው፤ ግዴታው ግን አንድ ጊዜ ብቻ ማለት ነው፡፡ ሩኩዕ አላህን የሚያልቁበትና የሚያወድሱበት ዒባዳ ነው፡፡
‹‹ሱብሓነ ረቢየል ዐዚም›› - ‹‹ታላቁን አላህ ከእንከንና ከጉድለት አጠረዋለሁ፤ እቀድሰዋለሁ፤›› ማለት ሲሆን፣ አንድ ሰጋጅ ይህንን የሚለው ከወገቡ ጎንበስ በማለት ለአላህ ያጎበደደና የተዋረደ ሆኖ ነው፡፡
ልክ እንደ ከዚህ በፊቱ እጆቹን በትከሻዎቹ ትክክል ከፍ በማድረግና የመዳፎቹን ውስጠኛ ክፍል ወደ ቂብላ በማቅጣጨት ካጎነበሰበት ቀጥ ብሎ ይቆማል፡፡ ኢማም ወይም ብቻውን የሚሰግድ ከሆነ ደግሞ፣ ‹‹ሰሚዐላሁ ሊመን ሐሚደሁ›› - (አላህ ያመሰገነውን ሰው ሰማው) ይላል፡፡ከዚያም ሁሉም ረበና ወለከል ሀምዱ ይላሉ
ከዚያም ሁሉም ፡ ‹‹ሐምደን ከሲረን ጠይበን ሙባረከን ፊሂ ሚልኣሰማኢ ወል አርዲ ወሚልአ ማሺእተ ሚን ሸይኢን በዕድ›› - (በርካታ፣ መልካምና በውስጡ በረከት ያለው፣ በሰማያት ሙሉ፣ በምደር ሙሉ፣ ከነዚህም ሌላ አንተ በምትሻው ነገሮች ሙሉ የሆነ ምስጋና ይድረስህ) ይላሉ፡፡
በማስከተል፣ በሰባት የሰውነት ክፍሎቹ መሬት ላይ በመደፋት ሱጁድ ያደርጋል፡፡ እነኚህም የሰውነት ክፍሎች ግንባር ከአፍንጫ ጋር፤ ሁለት መዳፎች፤ ሁለት ጉልበቶች እና ሁለት እግሮች ናቸው፡፡ ሱጁድ ሲያደርግ እጆቹን ከጎኖቹ ማራራቅ፣ ሁዱንና ጭኖቹን አለማጣበቅና እንዲሁም ጭኖቹንና ባቶቹን አለማገናኘት ይወደድለታል፡፡
ሱጁድ፣ አላህን ከመለመኛ ስፍራዎች ሁሉ በላጩ ነው፡፡ ሰጋጆች በሱጁድ ውስጥ መባል ያለባቸውን ውዳሴዎችንካሉ በኋላ የሚፈልጉትን የዱንያም ሆነ የኣኺራ ጉዳዮችን መለመን ይችላሉ፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹አንድ ባሪያ ለጌታው እጅግ ቅርብ የሚሆንበት ስፍራ ሱጁድ ነው፤ ስለሆነም በርሱ ውስጥ ዱዓን አብዙ፡፡›› (ሙስሊም 482)
አቀማመጡም ግራ እግሩን በማንጠፍና ቀኝ እግሩን በመቸከል ቢሆን ተወዳጅ ነው፡፡ መዳፎቹን ከጉልበቱ ቀጥሎ ባለው የጭኑ ጠረፍ ወይም ጫፍ ላይ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
በሠላት ውስጥ የሚቀመጡበት ሁኔታ
16 በሁለቱ ሱጁዶች መካከል ሲቀመጥ፡ ‹‹ረቢ ኢግፊር ሊ፣›› - (ጌታዬ ሆይ ምሕረትህን ስጠኝ፤ ) ማለት ይኖርበታል፡፡ ሶስት ግዜ ይደጋግመዋል
17 ከዚያም ልክ በመጀመሪያው ሱጁድ መልኩ ለሁለተኛ ጊዜ ሱጁድ ያደርጋል፡፡
18 በመቀጠልም ከሁለተኛው ሱጁድ ‹‹አላሁ አክበር›› በማለት ተነስቶ ይቆማል፤
19 ልክ እንዲሁ የመጀመሪያውን ረከዓ በሰገደው መልኩ ሁለተኛውንም ረከዓ ይሰግዳል ወይም ያስከትላል፡፡
ቁጭ ባለበት እንዲህ ይላል፡- ‹‹አትተሒይያቱ ሊልላሂ፣ ወሥሠለዋቱ፣ ወጥጠይባቱ፣ አስሰላሙ ዐለይከ አይዩሀ ንነቢይዩ ወረሕመቱልላሂ ወበረካቱሁ፣ አስሰላሙ ዐለይና ወዓላ ዒባዲልላሂ አሣሊሒነ አሽሐዱ አን ላ ኢላሃ ኢልለ ላህ ወአሽሃዱ አንነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉሁ፡››
በመጀመሪያው ተሸሁድ የሚባለውን በሙሉ ካለ በኋላ በሚከተለው መልኩ ለነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ዱዓ ያደርጋል፡ ‹‹አላሁምመ ሠሊ ዐላ ሙሐመድ ወዓላ ኣሊ ሙሐመድ ከማ ሠልለይተ ዓላ ኢብራሂመ ወዓላ ኣሊ ኢብራሂመ ኢንነከ ሐሚዱን መጂድ፤ ወባሪክ ዐላ ሙሐመዲን ወዓላ ኣሊ ሙሐመድ ከማ ባረክተ ዓላ ኢብራሂም ወዓላ ኣሊ ኢብራሂመ ኢንነከ ሐሚዱን መጂድ፡፡››
አንድ ሰጋጅ በዚህ መልክ በማሰላመት ስግደቱን ያጠናቅቃል፡፡ ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ሠላትን አስመልክተው፡ ‹‹በተክቢር ይታሰራል፤ በተስሊም ይፈታል›› ብለዋል፡፡ (አቡ ዳውድ 61/ አቲርሚዚ 3) ከሐዲሱ እንደምንረዳው ወደ ሠላት የሚገባው በመጀመሪው ተክቢራ ሲሆን ከርሱ የሚወጣው ወይም እርሱ የሚጠናቀቀው ደግሞ በተስሊም ወይም በሰላምታ መሆኑን ነው፡፡
24 አንድ ሙስሊም የግዴታን ሠላቶች ከሰገደ በኋላ የሚከተሉትን ማለት ይወደድለታል፡፡
ግዴታ የሆኑ የሠላት ውስጥ ውዳሴዎችንና ሙገሳዎችን በቃሉ ለመያዝ ከፍተኛ ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ የሚከተሉት ውዳሴዎች በዐረብኛ ቋንቋ መሆን አለባቸው፡፡ ፋቲሐና ተክቢር፤ ሱብሐነ ረቢየል ዐዚም፤ ሰሚዐላሁ ሊመን ሐመዲሁ፤ ረበና ወለከል ሐምድ፤ ሱብሐነ ረቢየል አዕላ፤ ረቢግፊርሊ፤ ተሸሑድ፤ ሠላት ዐለ ነቢይ፤ አሰላሙዐለይኩም ወራሕመቱላህ፡፡
አንድ ሙስሊም እነኚህን ውዳሴዎችንና ሙገሳዎችን በቃሉ እስከሚይዝ ወይም እስከሚሸመድድ ድረስ በሠላት ውስጥ የሚችለውን ተስቢሕ (ሱብሓነላህ)፣ ተሕሚድ(አልሐምዱሊላህ) እና ተክቢር(አላሁ አክበር) ደጋግሞ ማለት፣ ወይም በቃሉ የያዘውን የቁርኣን አንቀፅ እየደጋገመ ማንበብ አለበት፡፡ ምክንያቱም አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏልና ነው፡ - ‹‹አላህንም የቻላችሁትን ያክል ፍሩት፡፡›› (አል ተጋቡን 16)
ይህ ሰው በዚህ ቆይታው ሠላቱን በተሟላ መልኩ ለመካናወን ይረዳው ዘንድ በጀመዓ መስገድን ላይ ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡ ይህም ኢማሙ በተከታዩ ሰው በኩል የሚከሰቱ ክፍተቶችን ስለሚያሟላ ነው፡፡