መማርዎን ይቀጥሉ

ሎግ ኢን አላደረክም
መማር ለመጀመር፣ እድገትን ለመከታተል፣ ነጥቦችን ለመሰብሰብ እና ወደ ውድድር ለመግባት አሁኑኑ በታ ፕላትፎርም ይመዝገቡ፡ ከተመዘገቡ በኋላ ለሚማሯቸው ርዕሶች የኤሌክትሮኒክስ ሰርተፍኬት ይደርስዎታል።

የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል

ትምህርት ኢማን እና ክረምት

ሙስሊም ሰው አለም አቀፋዊ ምልክቶችን ማየት ፣ ቆም ብሎ ማሰላሰል እና ማስተንተን ይኖርበታል። ከዝንጉዎች መሃል አንዱ መሆን የለበትም። በዚህ ትምህርት ውስጥ ክረምቱን አስመልክቶ የኢማን አቋሞችን እንወስዳለን።

1 ክረምትን አስመልክቶ የሃያሉ አሏህን ጥበብ እና በአመቱ የወቅቶች መፈራረቅን ትማራላችሁ።2 የክረምት ወቅትን በማስመልከት ኢማናችሁን ትጨምራላችሁ።

ክረምት ከአመቱ ወቅቶች ውስጥ አንዱ ነው። ሃያሉ አሏህ ትልቅ ጥበብ እና ምልክት ያደረገበት ነው።

ክረምት በቁርአን ውስጥ

ክረምት የሚለው ቃል በቁርአን ውስጥ የተጠቀሰው አንድ ጊዜ ብቻ ነው። ያም በሱረቱል ቁርይሽ ውስጥ ነው። አሏህ እንዲህ ይላል፡ "ቁረይሽን ለማላመድ (ባለዝሆኖቹን አጠፋ)። የክረምት እና የበጋን ወራት ጎዞ ሊያላምዳቸው ይህን ሰራ።" (አል-ቁርአን 106፡1-2) የክረምት ጎዞ፡ ቁረይሾች በክረምት ውስጥ ለንግድ ያደርጉት የነበረው እንቅስቃሴ ነው። እናም ወደ የመን ይሄዱ ነበር። በበጋ ወቅት ደግሞ ወደ ሻም (ፈለስጢን ፣ ጆርዳን ፣ ሌባኖስ ፣ ሶሪያ) ያመሩ ነበር።

ክረምቱ ከበጋው ጋር ይቆራኛል። የመጸው እና የፀደይ ወቅትም ልክ በመካከላቸው እንዳለ ክፍተት ነው። በዚህም ምክኒያት አንዳንድ ሊቃውንት "አመቱ ሁለት ወቅቶች አሉት። እነሱም ክረምት እና በጋ ናቸው" ይላሉ።

ክረምት ከሃያሉ አሏህ ሃያልነት ፣ ጥበብ እና እዝነት ማሳያዎች ውስጥ አንዱ ነው።

ልቅና የሚገባው አሏህ ብቻ ነው። ሌሊት እና ቀን ፣ ሙቀት እና ብርድ ፣ ክረምት እና በጋን የሚያፈራርቀው ሃያሉ አሏህ ነው። አሏህ እንዲህ ይላል፡ "በእርግጥ! በሰማያት እና በምድር ፍጥረት ውስጥ፤ በቀን እና በሌሊት መፈራረቅ ውስጥ ለሚረዱ ሰዎች ምልክቶች አሏቸው።" (ሱረቱል ኢምራን ፡190) ምንም እንኳ ይህ ልዩነት የተለመደ ተፈጥሯዊ ክስተት ቢመስልም ይህን ተፈጥሯዊ ክስተት የፈጠረው አሏህ ነው።

ክረምት ዘመናትን ለመያዝ እና የአሏህን በረካ (ችሮታ) ለማስታወስ ትልቅ እድል ነው።

ክረምት እና የጊዜ መቀያየር የዘመናትን ማለፍ ፣ የዘመናትን ተሸጋሪነት እና የሰው ልጅ ሊይዘው (ሊገታው) ወይም ሊያስቀረው የማይችለው የመሆኑ ማሳያ ነው። የሰው ልጅ ብዙ ጊዜ አላፊን ጊዜ እና አላፊውን ክረምት እንዴት በፍጥነት እንደሚያልፍ ያስተውል። በክረምት የሰራውን እንከን ለማረም እና ለማካካስ የመጭውን ጊዜ እንደ ጥሩ እድል ይጠቀምበታልና።

አሏሁ ተአላ እንዲህ ይላል፡ "እሱ ያ (ያመለጠውን ስራ) ማስታወስን ለሚፈልግ ወይም ማመስገን ለሚፈልግ ሰው ቀን እና ሌሊትን ተተካኪ ያደረገ ነው።" (ሱረቱል ፉርቃን ፡62) ኡመር ኢብን ኸጧብ (ረ.ዐ)፡ "ከሌሊታችሁ ያለፈውን ነገር በቀናችሁ ውስጥ ያዙት (አግኙት)። አሏህ ሌሊት እና ቀንን ያደረገው (እሱን) እንድታወሳበት እና እንድታወደስበት ወይም እንድታመሰግንበት ነውና›› ብሏል።

ክረምት የአሏህን ፀጋ የምናስታውስበት አጋጣሚ ሲሆን የክረምቱን ቅዝቃዜ ለመወጣት ሙቀት የሚሰጡንን ነገሮችንም ያስገኘን አሏህ ነው። ለምሳሌ እንደ ጥጥ ጨርቆጭ ያሉ ፣ ማሳሪያዎች እና ሌሎች ነገሮችንም ማለት ነው። አሏህ እንዲህ ይላል፡ "ግመልን ፣ ከብትን ፣ ፍየልንም በርሷ (ብርድ መከላከያ) ሙቀት ጥቅሞች ያሉባት ስትሆን ለእናንተ ፈጠረላችሁ። ከእሷም ትበላላችሁ።" (ሱረቱ ነህል ፡5) የዚህ ፀጋ ሃቁ አሏህን ሊያመሰግኑበት ነው። ሃያሉ አሏህ እንዲህ ይላል፡ "ጌታችሁም አለ፡ በእርግጥ ብታመሰግኑ እጨምርላችኋለሁ። ብትክዱም እቀጣችኋለሁ። በእርግጥ ቅጣቴ ብርቱ ነው።" (ሱረቱ ኢብራሂም ፡7)

ክረምት የመጭውን አለም ህይወት (አሂራን) ለማስታወስ ጥሩ እድል ነው።

የብርዱ ክብደት ፣ የቅዝቃዜው ብርታት አስመልክቶ ከነብዩ (ሰ.ዐወ) ሐዲስ ትምህርት እንወስዳለን። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ "እሳት ወደ ጌታዋ እንዲህ ስትል ቅሬታ አቀረበች፡ ‹‹ጌታየ ሆይ አንዳንዶቹ አንዳንዶቹን ይበላሉ አለች። እናም ሁለት እስትንፋስን እንድትወስድ ፈቀደላት። አንደኛው በክረምት ሲሆን አንደኛው ደግሞ በበጋ ነው። ከሙቀቱ በላይ በጣም ትከብዳለችና። ከቅዝቃዜውም በጣም ከባዱ ይህ የምታገኙት ነው" አሉ። (ቡኻሪ 3260፣ ሙስሊም 617)

የጀሐነም ሰዎች በእሳት እየተቀጡ እንኳ ቀዝቃዛን ነገር ባለማግኘትም ይቀጣሉ። ሃያሉ አሏህ እንዲህ ይላል፡ "በውስጧ ቀዝቃዛ መጠጥ አይቀምሱም። ተምዘግዛጊ ሙቅ ውሃን እንጅ አይቀምሱም። ተስማሚ ምንዳንም ይመነዳሉ።" (ሱረቱ ነበዕ ፡ 24-26) ንጋቱ በቅዝቃዜ ሲያገሳ ቅዝቃዜው ያቃጥላል። የጀሐነም ሰዎች ከእሳቱ ንዳድ የሚረዳቸው ያለ ይመስል ይጮሃሉ። አጥንትን የሚሰነጥቅ የሆነ ብርዳማ ነፋስ ይመጣል። እነሱም ከጀሃነም ባህር ሆነው እርዳታን በመፈለግ ይጮሃሉ። አሏህ ይጠብቀን!

አንዳንድ ልቃውንቶጭ............

ትምህርቱን አጠናቅቀሃል


ፈተና ጀምር