የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት ትምህርት፡ ሶላት እና ፆም በጉዞ ላይ
መዝናኛ (መናፈሻ) ቦታው በመስጅድ አቅራቢያ ካልሆነ ለእያንዳንዱ ሶላት ድምፅን ከፍ አድርጎ አዛን ማድረግ ተደንግጓል።
አብዱሏህ ቢን አብዱረህማን እንዳስተላለፈው አቡ ሰኢድ አልሁድሪ (ረ.ዐ) ለእሱ እንዲህ አለው፡ ‹‹በጎችህ ጋር እና በበረሃው ቦታ በምትሆን ጊዜ እና ለሶላት አዛን ማድረግ በምትፈልግ ሰአት ድምፅህን ከፍ አድርገህ አዛን አድርግ። አዛኑ የሚሰማ ሰውም ሆነ ጅን ወይም ደግሞ ሌላ ፍጡር ለፍርድ በመቆሚያዋ ቀን ለአንተ ምስክር ይሆንልሃል አለ።›› አቡ ሰኢድ፡ ‹‹ይህን የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ሲሉ ሰምቻለሁ›› ሲል ጨመረ። (ቡኻሪ 609)
ሆኖም የአዛን ጥሪ ምንዳ (ቱሩፋት-ሽልማት) ያውቃልና በጉዞ ላይ ያለ ሰው ድምፄ አያምርም ብሎ ወይም ሌላ ምክኒያት አስቦ አዛን በማድረግ ሊያፍር አይገባም። በሐዲስ ውስጥ፡ ‹‹ሙአዚኑ በድምፁ ለሚሸፍነው እርቀት ተምሯል፤ እርጥብ እና ደረቅ ነገሮች ሁሉ ለእሱ ምህረትን ይጠይቁለታል›› ብሏል። (ኢብን ማጃ 724)
በጉዞ ወይም በጉብኝት ላይ ያለ ሰው የቂብላን አቅጣጫ ማወቅ አለበት። ይህም የመካ አቅጣጫ ነው።.........................
የቂብላ አቅጣጫን ለማወቅ ጥረት አድርጎ ሶላቱን ከጨረሰ በኋላ በቂብላ አቅጣጫ ሳይሆን አሳስቶ መስገዱን ቢረዳ ሶላቱ ተቀባይነት አለው። ሶላቱንም አይደግምም። ሶላቱን በመስገድ ላይ እያለ የቂብላ አቅጣጫውን እንደተሳሳተ ቢያወውቅ ወደ ትክክለኛው አቅጣጫ ይዞራል። ነገርግን ለማወቅ ምንም ጥረት ሳያደርግ ያለ ቂብላ አቅጣጫው ቢሰግድ ሶላቱን እንደገና ደግሞ ይሰግዳል።
የቂብላ አቅጣጫን ለማወቅ ዘመናዊ መሳሪያዎችን መጠቀም ፣ ፀሃይን እና ሌሎች ምልክቶችን መመልከት ወይም ደግሞ በአካባቢው ያሉ ታማኝ ሰዎችን ጠይቆ ማወቅ ይችላል።
በጉዞ ወቅት ሶላትን መጠበቅ አንድ ትልቅ ተልዕኮ ነው። ይህም የአሏህ ባሪያ ኢማን እውነተኛ ስለመሆኑ ማስረጃ ነው።
በሐዲስ እንደተዘገበው፡ ‹‹በጀምአ (በህብረት) መስገድ ከ 25 ሶላቶች ጋር እኩል ነው። እናም በበረሃ (በረባዳማ ቦታ) ከሰገደ ፣ ሩኩዑን እና ሱጁዱን ካሟላ የሃምሳ ሶላት ክብደት አለው።›› (አቡዳውድ 560)
ይህ ከአሏህ ጋር ያለው ቀረቤታ እና እሱን የመፍራት ማስረጃ ነው። ምክኒያቱም ከሰዎች እና ከሰዎች እይታ ቢርቅም ሶላቱን ግን አልተወምና ነው። በሐዲስ ውስጥ እንደተዘገበው፡ ‹‹ከተራራ አናት ላይ አዛን የሚያደርግ እና ሶላቱን የሚሰግድ የፍየል እረኛን አሏህ ይወዳል። ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡ ባሪያን ተመልከቱ፤ የሶላት ጥሪ አደረገ፤ ሶላቱን ሰገደ፤ ይፈራኛልም። እናም ምሬዋለሁ፤ ጀነት አስገቡት።›› (አቡዳውድ 1203)
በቀዝቃዛ እና በብርዳማ አካባቢዎች ሰዎች በጉዟቸው እሳት ይለኩሳሉ። ያ ደግሞ ሶላት በሚሰገድበት አቅጣጫ ሊሆን ይችላል። ሆኖም ሶላቱ የሚሰገደው በእሳቱ አቅጣጫ ባይሆን በላጭ ነው። ከእሳት አምላኪ ማጁሳዎች ጋር ላለመመሳሰል እና የሰጋጁን ልቦና ስለሚሰርቅ ኢማሙ ልዩ ጥንቃቄ ማደርረግ አለበት። እራሳቸውን ለማሟሟቅ ፈልገው ቦታ መቀየር የማይችሉ ከሆነ ችግር የለውም።
ሁለት ሶላቶችን ማጣመር ስንል የዝሁር ሶላትን እና የአስር ሶላትን ወይም የመግሪብ ሶላትን መስገድ እና ከኢሻ ሶላት ጋር በማጣመር (ለማፋጠንም ሆነ ለማዘግየት) በአንደኛው የሶላት ወቅት ሁለቱንም አንድ ጊዜ መስገድ ነው። ይህ የሚሆነው ግን ለማጣመር በቂ ምክኒያት ካለ ብቻ ነው።
ማሳጠር ማለት ደግሞ አራት ረከአ ሶላትን እንደ ሁለት ረከአ አድርጎ መስገድ ነው። ያም የዝሁር ፣ አስር እና የኢሻን ሶላት ነው። ነገርግን የመግሪብ እና የፈጅር ሶላትን ማሳጠር አይቻልም።
ሶላትን ማሳጠር እና ማጣመር የሚቻልበት ሰበብ ወይም በቂ ምክኒያት ጉዞ ነው። ጉዞ ከመኖሪያ አካባቢ ወደ ሌላ ቦታ ወይም ሐገር መሄድ ሲሆን አንዳንድ ሊቃውንት ጉዞው ከ80 ኪሎሜትር መብለጥ አለበት ይላሉ። በዚህም መሰረት በከተማው አቅራቢያ ሽርሽር የሄደ ሰው አያሳጥርም። የሄደበት ቦታ ግን ራቅ ያለ ሆኖ በላይኛው መስፈርት መሰረት ጉዞ ሊባል የሚችል ከሆነ ለሽርሽር ቢሄድም ሶላቱን ማሳጠር ይችላል።
ለመንገደኛ ሰው ሶላትን ማሳጠር ሱና ነው። በጉዞ ላይ ያለ ሰው ለጉዞው እንደሚመቸው ሶላቱን ቀደም ብሎ ወይም ዘግይቶ ማጣመር ይችላል። በአንድ ቦታ ላይ ተረጋግቶ ከተቀመጠ ደግሞ ሁሉንም ሶላት በወቅቱ መስገዱ በላጭ ነው። በተለይ ደግሞ ከመስጅድ ጀመአ ጋር መስገድ የሚችል ከሆነ።
መንገደኞች የጉዞ ሃሳብ ስለሚይዛቸው ሶላትን በሰአቱ መስገድ እንዳለባቸው ችላ ማለት አይኖርባቸውም። ሃያሉ አሏህ የጦርነቱን ሁኔታ ከገለፀ በኋላ እንዲህ አለ፡ "በተረጋጋችሁ ጊዜ ሶላትን አሟልታችሁ ስገዱ። ሶላት በምዕመናን ላይ በጊዜያት የተገደበች ግዴታ ናት።" (ሱረቱ ኒሳዕ 103)
በጉዞ ወቅት ለሶላት በተሰባሰቡ ጊዜ አንድ አዛን ማድረግ እና ለእያንዳንዱ ሶላት ኢቃም ማድረግ በቂ ነው። አሏህን ማውሳት (አዝካር) ከሁለተኛው ስግደት በኋላ ነው።
ከጉዞ ጋር በተያያዘ ሶላትን ማሳጠር እና መቀጠል የሚፈቀድባቸው ሰበቦች (ምክኒያቶች) ላይ ልዩነት ሊኖር ይችላል። ነገርግን ዋናው መርህ ኢማሙ እና የህብረቱ መሪ (አባትም ሊሆን ይችላል) ሃላፊነት አለበት የሚለው ነው። እናም እውቀት ካለው ተገቢ ብያኔ ላይ ለመድረስ ያቅሙን ያህል ይጥራል፤ እውቀት ያላቸውን ሰዎች ያማክራል ማለት ነው። በቂ ምክኒያት አለ ብሎ ካላሰበ እና የተፈቀደ አለመሆኑን ከተረዳ አያሳጥርም አይቀጥልምም። ህብረቱ (ጀመአው) መጨቃጨቅ አያስፈልገውም። ምክኒያቱም መስማማት አንድ የአምልኮ ተግባር ነውና።
ፆም ለጉዞና ጉብኝት የታሰበ አይደለም። ነገርግን የሆነ ሰው ሰኞ እና ሃሙስን የሚፆም ቢሆንና ከጉዞው ጋር ቢገጣጠም ፆሙን ከመፆም የሚያግደው ነገር የለም።
አነስ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ፡ ‹‹ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጋር እየተጓዝን እያለ ፆመኛ ሰው የማይፆመውን ሰው አይነቅፍም ነበር። የሚፆምም ሰው የማይፆምን ሰው አይነቅፍም ነበር።›› (ቡኻሪ 1947 ፣ ሙስሊም 1118)