የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት የላኢላሀ ኢለላሀ ምስክርነት ቃል
እስልምና ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም የሚለውን የተውሂድ ቃል ትልቅና የተከበረ ደረጃን ይሰጣል።
የላኢላሀ ኢለላህ ቃል ደረጃ
•ይህ በመሆኑም ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ አለመኖሩን ማወቀና መመስከር የግዴታዎች ሁሉ ተላቁ ግዴታ ነው፡፡
“ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም” የሚለው ቃል ትርጉም
ይህ ማለት ብቸኛ ከሆነው አላህ በስተቀር በዕውነት የሚመለከ አምላክ የለም ማለት ነው፡፡ ከተቀደሰውና ከፍ ካለው አላህ በስተቀር ከማንም ላይ መለኮታዊነትን መሻር ማለት ሲሆን መለኮታዊ ስልጣንን አንድና አጋርለሌለው አላህ ብቻ ማረጋገጥ ማለት ነው፡፡
«አል-ኢላህ» (አምላክ)! ማለት የሚመለክ ማለትነው፡፡ ቀልቦች በመተናነስ በማክበር በመማጸን፤በመፍራት፣ በርሱ ላይ በመመካት ያመልኩታል፡፡ አንድን ነገር ያመለከ ሰው የተናነሰ፤ የወደደ፤ የከጀለ፤ ያንን ነገር ከአላህ ሌላአምላክ አድርጎ ይዞታል፡፡ ከተቀደሰው፣ ከፍ ካለውናፈጣሪ ከሆነው አንዱ ጌታ በስተቀር የሚመለኩ ነገሮችበሙሉ ባጢል (ሐሰት) ናቸው፡፡አምልኮ የሚገበው ከጉድለት የጠራውና ከፍ ለለው ለአላህ ብቻ ነው፡፡
አምልኮ የሚገባው ከጉድለት የጠራውና ከፍ ያለው አላህ ብቻ ነው፡፡ ቀልቦች በውዴታ፣ በማላቅ፣ በማክበር፣በመተናነስ፣ ዝቅ በማለት፤ በመፍራት፣ በርሱ ላይ በመመካት ያመልኩታል፡፡ ለልመናም እርሱን ይጠሩታል፡፡ ከአላህ ውጪ ለልመና የሚጠራ የለም፡፡ እርዳታ የሚጠየቀው እርሱ ብቻ ነው፡፡ በርሱ ካልሆነ በማንም መመካት አይቻልም፡፡ ለርሱ ካልሆነ ለማንም አይሰገድም፡፡የአምልኮ እርድ ለርሱ ካልሆነ ለማንም አይታረድም፡ አምልኮ የተባለን በሙሉ ለርሱ ብቻ ማጥራት ግዴታ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፡፡ “አላህን ሃይማኖትን ለርሱ ብቻ አጥሪዎች ቀጥተኞች ሆነው ሊገዙት፣ ሶላተንም አስተካክለው ሊሰግዱ ዘካንም ሊሰጡ እንጅ ያልተዘዙ ሲኾኑ (ተለያዩ)፡፡” (አል-በይናህ፡4)
ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም የሚለው ቃል በማረጋገጥ፥ አላህን ጥርት አድርጎ ያመለከ ሰው፥ ታላቅ የሆነ ደስታን ይጎናፀፋል፡፡ እርጋታና ስክነት ያለው መልካም ህይወት ይኖራል፡፡ አላህን በብቸኝነት ከማምለክ ሌላ፥ ለቀልብ ትክክለኛ የሆነ መረጋጋትን፣እርካታንና ረፍት የሚሰጥ ሌላ ነገር የለም፡፡ አላህ እንዲህ ብሎዋል፡፡ “ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ሆኖ በጎን የሠራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን…”(አል-ነሕል፡97)
“ከአላህ በስተቀር በእውነተ የሚመለክ አምላክ የለም” የሚለው ቃል መሠረቶች
የአምልኮ ዓይነቶችን በሙሉ ልንሰጥ የሚገባው አንድና አጋር ለሌለው አላህ ብቻ ነው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አንዱን እንኳ ከአላሀ ውጪ ላለ ነገር አሳልፎ የሰጠ ከሃዲ ይሆናል፡፡ አላህ እንዲሀ ይላል …“ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ ለርሱ በርሱ ማስረጃ የሌለውን የሚግገዛ ሰው ምርመራው ጌታው ዘንድ ብቻ ነው፤ እነሆ ከሀዲዎች አይድኑም፡፡” (አል-ሙእሚን፡117)
ከአላሀ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም የሚለው ቃል ትርጓሜና መሠረቶች እንዲህ በሚለው የአላህ ቃል ውስጥ ተገልጿል… “በጣዖትም የሚክድና በአላህ የሚያምን ሰው ለርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡”(አል-በቀራህ፡256) በዚህ የአላህ ቃል ውስጥ “በጣዖትም የሚክድ” የሚለው ቃል የመጀመሪያ መሠረት የሆነውን “አምላክ የለም” የሚለውን ቃል ሲሆን ያረጋገጠው “በአላህ የሚያምን” የሚለው የጌታችን ቃል ደግሞ ሁለተኛ መሠረት የሆነውን ከአላህ በስተቀር የሚለውን ቃል የረጋግጥልናል፡፡