መማርዎን ይቀጥሉ

ሎግ ኢን አላደረክም
መማር ለመጀመር፣ እድገትን ለመከታተል፣ ነጥቦችን ለመሰብሰብ እና ወደ ውድድር ለመግባት አሁኑኑ በታ ፕላትፎርም ይመዝገቡ፡ ከተመዘገቡ በኋላ ለሚማሯቸው ርዕሶች የኤሌክትሮኒክስ ሰርተፍኬት ይደርስዎታል።

የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል

ትምህርት ሺርክ

ሽርክ በአላህ አምላክነት ማመንን ይቃረናል ይህም ከሀጢያት ሁሉ ታላቅ ነው። በዚህ ትምህርት ስለ ሽርክ ትርጉም፣ ስለ አደገኛነቱ እና ስለ ዓይነቶቹ ትማራለህ።

  • ሺርክ ምን ማለት እንደሆነ ማወቅ።
  • የሺርክን አደጋ ማወቅ።
  • የሺርክ ዓይነቶችን ማወቅ።

የማጋራት ትርጉም

ሺርክ ማለት ከአላህ ጋር ሌላን በጌትነቱ በአምላክነቱ፤ በስሞቹና በባሀረያቱ ማጋራት ማለት ነው።

የሽርክ ምሳሌዎች

١
በጌትነት ሺርክ፡- ከአላህ ሌላ ዩኒቨርስን የፈጠረ ወይም የሚያስተዳድረው አካል አለ እንደሚል ሰው
٢
'ሽርክ በመለኮት፡- ከልዑል አላህ ሌላን እንደሚያመልክ ወይም የምለምን
٣
ሽርክ በስም እና በባህሪያት፡- ሁሉን ቻይ የሆነውን አላህን ከፍጡራኑ ጋር እንደሚያመሳስለው።

የሺርክ አስከፊነት

ሺርክ በአላህ አምላክነት ላይ ያለንን እምነት የሚፃረር ነገር ነው፡፡ በአላህ አምላክነት ማመንና የአምልኮ ተግባራትን ለርሱ ብቻ ማዋል ከታላላቅና ወሳኝ ከሆኑ ግዴተዎች ውስጥ ግንባር ቀደሙ መሆኑ እርግጥ ከሆነ፥ ከዚህ በተመሳሳይ መልኩ ለአላህ ብቻ የሚገባውን የአምልኮ ተግባር ለሌላ አካል ማጋራት ደግሞ አላህ ዘንድ የወንጀሎች ሁሉ ቁንጮ ነው፡፡ ንሰሃ ካልገቡ በቀር አላህ በፍፁም የማይምረው ብቸኛ ወንጀል ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል… “አላህ በርሱ ማጋራትን በፍፁም አይምርም፤ ከዚህ ሌላ ያለውንም ኀጢአት ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡ በአላህም የሚያጋራ ሰው ታላቅን ኃጢአት በእርግጥ ቀጠፈ፡፡” (አል-ኒሳእ፡ 48) ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) አላህ ዘንድ ከወንጀሎች ሁሉ ታላቁ ምን እንደሆነ ሲጠየቁ “አላህ ፈጥሮህ ሳለ ለርሱ ተጋሪ ማድረግህ ነው” በማለት መልሰዋል፡፡ (አል- ቡኻሪ፡ 4207 / ሙስሊም፡ 86)

በአላህ ማጋራት ስራን በሙሉ ከንቱና ውድቅ ያደርጋል፡፡ አላህም እንዲህ ብሏል፡፡ "ባጋሩም ኖሮ ይሠሩት የነበሩት ከነርሱ በጠፋ ነበር፡፡” (አል- አንዓም፡88)

በአላህ አጋርቶ ንሰሃ ሳይገባ የሞተ ሰው ዕጣፈንታው ዘላለም በጀሃነም እሳት መቀጣት ይሆናል፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፡፡ …”እነሆ! በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በርሱ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ፤ መኖሪያውም እሳት ናት፤ ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም፡፡” (አል-ማኢዳህ፡72)

የሺርክ ዓይነት

١
ታላቁ ሺርክ፡-
٢
ትንሹ ሺርክ፡-

1 ታላቁ ሺርክ፡-

ታላቁ ሺርክ፡- ይህ ማለት አንድን የአምልኮ (ዒባዳ) ዓይነት ከአላህ ውጪ ላለ አካል አሳልፎ መስጠት ማለት ነው፡፡ አንድ አላህ የሚወደውን ንግግርም ሆነ ተግባር ለአላህ ብቻ ካዋልነው አንድነቱን አፀደቅን ወይም አመንበት ማለት ነው፡፡ ይህን ተግባር ከርሱ ሌላ ለሆነ አካል ካዋልነው ደግሞ፥ ክደነዋል አጋርተንበታል፡፡ ለእንዲህ ዓይነቱ የሺርክ ተግባር ምሳሌን መጥቀስ እንችላለን፡፡ ከአላህ ውጪ ያለን አካል ከህመም እንዲያሽረን፣ ሲሳይን እንዲያሰፋልን ከጠየቅነውና ከለመንነው በታላቁ የሺርክ ተግባር ላይ ወድቀናል ማለት ነው፡፡ ከአላህ ውጪ ለሆነ ነገር ብንሰግድ ወይም በርሱ ላይ ብንመካም እንደዚያው ነው፡፡

١
አላህ እንዲህ ይላል … “ጌታችሁም አለ፡- ለምኑኝ እቀበላችኋለሁና፤ እነዚያ እኔን ከመገዛት የሚኮሩት ተዋራጆች ሆነው ገሃነምን በእርግጥ ይገባሉ፡፡” (አል- ሙእሚን፡60)
٢
እንዲህም ይላል … “… ምእምናንም እንደ ሆናችሁ በአላህ ላይ ተመኩ አሉ፡፡” (አል-ማኢዳህ፡23)
٣
ሌላ ሱራ ላይም እንዲህ ብሏል…”ለአላህም ስገዱ ተገዙትም፡፡” (አል ነጅመ፡ 62)

እነዚህን ተግባራት ከአላህ ሌላ ላለ አካል ያዋለ ሰው አጋሪ እንዲሁም ከሃዲ ይሆናል፡፡ከአላህ ውጪ ያን አካል ከህመምእንዲያሽረን፣ ሲሳይን እንዲያሰፋልን ከጠየቅነውና ከለመንነው በአምልኮ አጋረን፤ ከአላህ ውጪ ለሆነ ነገር ብንሰግድ ወይም በርሱ ላይ ብንመካም እንደዚያው በጌትነት አጋረን ማላት ነው፡፡

2 ትንሹ ሺርክ፡-

ይህ ደግሞ ወደ ታላቁ ሺርክ ሊያደርስ የሚችል ንግግር ወይም ተግባር ነው፡፡ ትንሹ ሺርክ ታላቁ ሺርክ ላይ ሊጥል ይችላል፡፡

የትንሹ ሽርክ ምሳሌዎች

١
ለዚህኛው የሚሆን ምሳሌ መጥቀስም ይቻላል፡- ሰው አንዲያይለት በማሰብ ሶላትን ማስረዘም ወይም ሰዎች እንዲያደንቁት በማሰብ ቁርኣን ሲያነብ ወይም አላህን ሲዘክር ድምፁን ከፍ ማድረገና የመሳሰሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡ የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) “እኔ ለእናንተ በጣም ከምፈራላችሁ ነገር ውስጥ አንዱ ትንሹ ሺርክ ነው፡፡” በማለት ሲናገሩ ሰሃቦችም “አንቱ የአላህ መልእክተኛ ትንሹ ሺርክ ምንድ ነው?” በማለት ጠየቋቸው፡፡ እርሳቸውም “የይዩልኝ ስራ ነው፡፡” በማለት መልስ ሰጡ (አህመድ፡2363)
٢
የተውሂድን ፍፁምነት የሚቃረኑ የተከለከሉ ንግግሮች፡- ለምሳሌ ከአላህ ሌላ የሚምል እና የሚምል እና ለምሳሌ፡- (እና ህይወታችሁ) የሚል ወይም (ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ)) እና መልእክተኛው (ሶለላሁ ​​ዐለይሂ ወሰለም) በዚህ ላይ አስጠንቅቀው እንዲህ ብለዋል፡- "ከአላህ ሌላ በሆነ ነገር የሚምል ክዷል ወይም ሽርክን ሰርቷል" (ቲርሚዚ 1535)።

ከሰው መፈለግና ሰውን አንዳንድ ነገር መጠየቅ የሺርክ ተግባር ነውን?

የእስልምና ሃይማኖት የተደነገገው የሰውን አዕምሮ ከንቱ ከሆኑ እምነቶች ነፃ ለማውጣት ነው፡፡ የተደነገገው የሰው ልጅ ከአላህ ውጪ ላለ አካል ዝቅ እንዳይል ነው፡፡ ለሙታንም ሆነ ግዑዝ ለሆኑ አካላት ዝቅ ብሎ በመተናነስ ፍላጎትን መጠየቅ ህገ-ወጥ የሆነ ተግባር ነው፡፡ ይህ ከንቱ እምነትና ሺርክ ነው፡፡ ነገር ግን አጠገባችን ያለንና ህይወት ያለውን ሰው አቅሙ የሚችለውን ነገር እንዲያደርግልን ብንጠይቀው ወንጀል አይደለም፡፡ ለምሳሌ ውሃ ውስጥ የሰጠመ ሰው ህይወቱን ያተርፈው ዘንድ ሰውን መጠየቁ፣ ወይም አንድ ሰው ዱዓእ እንዲያደርግልን ብንጠይቅ እስልምና የሚፈቅደው ህጋዊ ተግባር ነው፡፡

ሙታንን ወይም ግዑዝ አካላትን መከጀልና መማፀን የሺርክ ተግባር ነው

ሙታንን ወይም ግዑዝ አካላትን መከጀልና መማፀን የሺርክ ተግባር ነው ይህ እስልምናንና ኢማንን የሚቃረን ነው፡፡ ምክንያቱም ሙታንና ግዑዛን ነገሮች፣ ጥያቄውን መስማትም ሆነ ምላሽ መስጠት አይችሉም፡፡ ልመና (ዱዓ) አምልኮ ነው። በመሆኑም ከአላህ ሌላ ለሆነ አካል አሳልፎ መስጠት ማጋራት ነው፡፡ በታወጀበት ዘመን የነበሩ ዐረቦች ያጋሩ የነበሩት ግዑዛንንና ሙታንን በመለመን ነበር፡፡

ትምህርቱን አጠናቅቀሃል


ፈተና ጀምር