መማርዎን ይቀጥሉ

ሎግ ኢን አላደረክም
መማር ለመጀመር፣ እድገትን ለመከታተል፣ ነጥቦችን ለመሰብሰብ እና ወደ ውድድር ለመግባት አሁኑኑ በታ ፕላትፎርም ይመዝገቡ፡ ከተመዘገቡ በኋላ ለሚማሯቸው ርዕሶች የኤሌክትሮኒክስ ሰርተፍኬት ይደርስዎታል።

የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል

ትምህርት የሞተን ሰው መጣብ እና መከፈን

አንድ ሙስሊም ሰው በህይወት ሳለ እስልምና እንዳከበረው ሁሉ ሲሞትም አክብሮታል፡፡ በዚህ ትምህርት ውስጥ የሞተን ሰው ከማጠብ እና ከመከፈን ጋር የተያያዙ አህካሞችን ትማራላችሁ፡፡

1 አንድ ሙስሊም ሰው በሚሞት ጊዜ ማድረግ የተወደደ ነገር ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ፡፡2 የሞተ ሰው እንዴት እንደሚታጠብ ታውቃላችሁ፡፡3 የመከፈን አህካሞችን (ብያኔዎችን) ታውላችሁ፡፡

አንድ ሙስሊም ሰው በሚሞት ጊዜ ማድረጉ የተወደደ ተግባር ምንድን ነው?

ሞቱ ከተረጋገጠ እና ነፍሱ ከአካሉ ከተለየች በኋላ የተወሰኑ ነገሮችን ማድረጉ የተወደደ ነው፡፡

1 ለሱ ክብር ስባል ቀስ ተብሎ የሟቹን ሰው አይን መክደን

በእርግጥ! ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ አቡ ሰላማ ቤት ገብተውሞቶ አይኖቹ ተከፍተው ኣዩ አይኖቹን ከከደኑ በኋላ ‹‹ወደ ሟቻችሁ ሰው በመጣችሁ ጊዜ አይኖቹን ክደኑ፡፡››ኣሉ። (ኢብን ማጃ 1455)

2 መታገስ እና ነፍስን መግታት

ጮሆ አለማልቀስ አስፈላጊ ነው፡፡ የሟቹ ሰው ዘመዶች እና ቤተሰቦች እንዲታገሱ ማፅናናት ያስፈልጋል፡፡ በእርግጥ! ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከልጆቻቸው አንዷ ወንድ ልጇን ባጣች ጊዜ እንድታታገስ እና ምንዳን ከአሏህ እንድትፈልግ አዘዋታል፡፡ (ቡኻሪ 1284 ፣ ሙስሊም 923)

3 ለእሱ የአሏህን እዝነት እና ምህረት መለመን እና ቤተሰቦቹ እንዲታገሱ ማድረግ እና ማፅናናት

ከተከበሩ ሶሃቦች አንዱ የሆነው አቡ ሰላማ በሞተ ጊዜ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዳደረጉት ማለት ነው፡፡ እሳቸውነም አንዲህ አሉ፡ ‹‹ነፍስ በምትወሰድ ጊዜ የሰውየው እይታ ይከተላታል፡፡ ከዚያም አሉ፡ ‹‹አሏህ ሆይ! አቡ ሰላማን ማረው ፣ በትክክል ከተመሩት መካከል ደረጃውን ከፍ አድርገው ፣ ዘሩን ሚንከባከብ ተተኪም ስጠው፡፡ እኛንም እሱንም ማረን፡፡ቀብሩን አስፋለት አብራለትም ›› (ሙስሊም 920)

4 የሟቹን ሰው አስክሬን ለማዘጋጀት ፣ ለማጠብ እና በእሱ ላይ ለመስገድ እና ለመቅበር መቻኮል

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ አስክሬኑን ለመቅበር አቻኩሉ፡፡ በጎ (መልካም) ከነበረ ወደ መልካም ነገር እያስተላለፋችሁት ነው፡፡ ይህ ካልነበረ ደግሞ ክፉን ነገር ከትከሻችሁ ማውረድ ነውና፡፡›› (ቡኻሪ 1315በ ፣ ሙስሊም 944)

5 የሟቹን ሰው ቤተሰቦች መርዳት

ይህ ማለት አንዳንድ ስራዎቻቸውን መገዝ ማለት ነው፡፡ ጃዕፈር አቢ ጧሊብ (ረ.ዐ) በተገደለ ጊዜ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሶሃቦች ለቤተሰቦቹ ምግብ እንዲዘጋጅ ሲያዙ፡ ‹‹ለጃዕፈር ቤተሰቦች ምግብ አዘጋጁ፡፡ ምክኒያቱም እነሱን የያዛቸውን የሆነ ነገር ደርሶባቸዋልና፡፡›› (አቡዳውድ 3132 ፣ ትርሚዚ 998 ፣ ኢብን ማጃ 1610)

ሬሳን ማጠብ

ማቹን በከፈን ከመጠቅለል በፊት ማጠቡ ግዴታ ነው፡፡ ከቤተሰብ አባሎቹ ወይም ከዘመዶቹ አንዱ ወይም ሌላ አንድ ሙስሊም ሰው ሊያጥበው ይችላል፡፡ በእርግጥ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በጣም ንጽህ ሆነው እንኳ በሞቱ ጊዜ ታጥበው ነበር፡፡

የሟቹ ሰው አስክሬን የሚታጠብበት መንገድ

የሞተን ሰው አስክሬን ሰውነቱን ሙሉ በውሃ ማጠቡ እና ቆሻሻ ነገር ካለ እሱን ማፅዳቱ በቂ ነው፡፡ በሚያጥቡ ጊዜ ሃፍረተ ገላውን በመሸፈን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን ጉዳዮች ከግምት ውስጥ ማስገባትም ይወደዳል፡፡

ሬሳው በሚታጠብበት ግዜ ከእይታ ርቆ ልብሶቹ ይወልቃሉ፡፡ በእንብርቱ እና በጉልበቱ መካከል ያሉትን ሃፍረተ ገላዎች መሸፈን፡፡

2 የሟቹን ብልት በሚያጥቡ ጊዜ የእጅ ጓንት ወይም እራፊ ጨርቅ መልበስ ይኖርባቸዋል፡፡

3 ከአስክሬኑ ቆሻሻ ወይም የተበከለ ነገር ካለ እሱን በማፅዳት መጀመር ያስፈልጋል፡፡

4 በመቀጠል የሚታወቀውን የውዱዕ ቅደም ተከተል በመከተል የውዱእ አካላት ማጠብ ያስፈልጋል፡፡

5 ከዚያም እራሱን እና ቀሪው የሰውነቱን ክፍል ማጠብ ነው፡፡ ሆኖም በቁርቁራ ቅጠል ወይም በሳሙና ማጠቡ የተወደደ ነው፡፡ ከዚያም በእሱ ላይ በቂ ውሃ ማፍሰስ ያስፈልጋል፡፡

6 በመጀመሪያ የቀኝ ጎኑን ከዚያም የግራ ጎኑን ማጠብ የተወደደ ነው፡፡

7 አስፈላጊ ከሆነ የገላ ትጥበቱን ሶስት ጊዜ ወይም ከዚያ በላይ መድገም ይወደዳል፡፡

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ልጃቸው ዘይነብ (ረ.ዐ) የምታጥበውን ሴት ሰሲናገሩ እንዲህ አሉ፡ ‹‹አስፈላጊ ነው ብለሽ ካሰብሽ ሶስት ጊዜ ፣ አምስት ጊዜ ወይም ከዚያ በላይ ደግመሽ እጠቢያት፡፡›› (ቡኻሪ 1904 ፣ ሙስሊም 1151)

8 እራፊ ጨርቅ ፣ ጥጥ ወይም ሌላ ነገር ማስቀመጥ

ደም ወይም ሌላ ንፁህ ያልሆነ ፈሳሽ ነገር እንዳይወጣ ፊንጢጣ ውስጥ ፣ ብልት ውስጥ ፣ ጆሮ ፣ አፍንጫ እና አፍ ውስጥ እራፊ ጨርቅ ፣ ጥጥ ወ.ዘ.ተ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡

9 የሞተን ሰው ሽቶ መቀባት የተወደደ ነው፡፡

በሚታጠብ ጊዜ እና ከታጠበ በኋላ ማለት ነው፡፡ በእርግጥ! የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ልጃቸው ዘይነብ በሞተች ጊዜ አካሏን ያጥቡ ለነበሩ ሴቶች ካፉር (ለሽቶ መስሪያ የሚያገለግል) የመጨረሻው ትጥበት ላይ እንዲጠቀሙ አዘዋል፡፡ (ቡኻሪ 1253 ፣ ሙስሊም 939)

ትጥበቱን የሚያከናውነው ማን ነው

١
1 ሟች በህይወት እያለ የሆነ ሰው እንዲያጥበው እና እንዲከፍነው ተናዞ ከነበረ ምርጫውን አጥብቀን እንይዛለን፡፡
٢
2 ከሰባት አመት በታች የሆኑ ወንዶች እና ሴት ልጆች በወንዶች ወይም በሴቶች ሊታጠቡ ይችላሉ፡፡ ተመራጩ ግን ወንዱን ልጅ ወንዱ ቢያጥብ እና ሴቷን ልጅ ደግሞ ሴቷ ብታጥባት ነው፡፡
٣
3 ሟቹ ከሰባት አመት ዕድሜ በላይ ከሆነ ሊታጠብ የሚገባው ወንዱ በወንድ እና ሴቷ በሴት ብቻ ነው፡፡
٤
4 ባል ሚስቱን ማጠብ ይፈቀድለታል፡፡ ሚስት ደግሞ ባሏን ማጠብ ይፈቀድላታል፡፡ በእርግጥ! አሊ ኢብን አቢ ጧሊብ (ረ.ዐ) ሚስቱን ፋጢማ (ረ.ዐ) አጥቧል፡፡

በሌላ በኩል አኢሻ (ረ.ዐ) እንዲህ አለች፡ በህይወቴ ውስጥ ያጋጠሙኝ ቀድሜ የማውቅ ብሆን ኖሮ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከሚስቶቹ ውጭ በሌላ ሰው አይታጠቡም ነበር፡፡›› (አቡዳውድ 3141 ፣ ኢብን ማጃ 1464)

ሬሳን መገነዝ

ሟቹ ሰው አካሉን በሚሸፍን ነገር መከፈን (መጠቅለል) መብቱ ሲሆን በቤተሰብ አባላቶቹ እና በሙስሊሞች የሚፈፀም የማህበረሰቡ የጋራ ግዴታ ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹ነጭ ልብሶቻችሁን ልበሱ፤ ምክኒያቱም ምርጦቹ ልብሶቻችሁ ናቸውና፡፡ የሞተ ሰዋችሁንም በእሱ ከፍኑ፡፡›› (አቡዳውድ 3878)

ሟቹ ገንዘብ ካለው የከፈኑ ወጭው የሚሸፈነው ከገንዘቡ በማንሳት ነው፡፡ ገንዘብ ከሌለው ደግሞ በህይወት እያለ ወጭውን መሸፈን የሚገደዱት ቤተሰቦቹ ልክ እንደ አባት ፣ አያት ልጅ ወ.ዘ.ተ ያሉት የከፈኑ መግዣ ወጭ የመሸፈን ግዴታ አለባቸው፡፡ ይህ መሆን ካልቻለ ሃብታም ሙስሊሞች እንዲሸፍኑት ይደረጋል፡፡

ሟቹ ወንድም ሆነ ሴት፤ ግዴታ የሆነው ከፈን የሟቹን ሰው አካል የሚሸፍን ንፁህ ጨርቅ መሆንኑ በራሱ በቂ ነው፡፡

በከፈን በሚጠቀልልሉ ጊዜ ማድረጉ የተወደደው ተግባር

١
1 ለወንድ በሶስት ነጭ ጨርቅ መጠቅለል ሲሆን ለሴት ደግሞ በደንብ መጠቅለል ይቻል ዘንድ በአምስት ጨርቅ መጠቅለል ነው፡፡
٢
2 ከተቻለ ጨርቁ ነጭ ቢሆን ይወደዳል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ስለዚህ ጉዳይ እንዲህ ብለወል፡ ‹‹ከልብሶቻችሁ ነጩን ልበሱ፤ ምክኒያቱም ምርጦቹ ልብሶቻችሁ ናቸውና፡፡›› (አቡዳውድ 461 ፣ ትርሚዘኢ 994 ፣ ኢብን ማጃ 3566)
٣
3 የተፈቀዱ የሽቶ አይነቶችን መቀባት የተወደደ ነው፡፡
٤
4 የሞተን ሰው በጥንቃቄ መከፈን ይመከራል፡፡ ቁጥሩ የሚቋጥረው ደግሞ መጀመሪያ ከእራሱ ከዚያም ከእግሩ ነው፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በዚህ ጉዳይ ላይ እንዲህ ብለዋል፡ ‹‹አንዳችሁ ወንድሙን በሚጠቀልል ጊዜ በልቅና እና በክብር ያድርገው፡፡›› (ሙስሊም 943)

ትምህርቱን አጠናቅቀሃል


ፈተና ጀምር