መማርዎን ይቀጥሉ

ሎግ ኢን አላደረክም
መማር ለመጀመር፣ እድገትን ለመከታተል፣ ነጥቦችን ለመሰብሰብ እና ወደ ውድድር ለመግባት አሁኑኑ በታ ፕላትፎርም ይመዝገቡ፡ ከተመዘገቡ በኋላ ለሚማሯቸው ርዕሶች የኤሌክትሮኒክስ ሰርተፍኬት ይደርስዎታል።

የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል

ትምህርት በሞተው ሰው ላይ መስገድ እና አስክሬኑን መቅበር

በሟች ሰው ላይ መስገድ ሟቹ በሙስሊም በወንድሞቹ ላይ ያለው መብት ነው፡፡ አንድ ሙስሊም ሰው በእስልምና ውስጥ የመከበሩ መገለጫ ነው፡፡ በዚህ ትምህርት ውስጥ ስለ ሶላቱል ጀናዛ እና ከቀብር ጋር የተያያዙ ሁክሞችን ትማራላችሁ፡፡

1 በሞተ ሰው ላይ የሚሰገድ ሶላት ገለፃን ትማራላችሁ፡፡2 ከቀብር ጋር የተያያዙ አህካሞችን ትማራላችሁ፡፡

የጀናዛ ሶላት

ሶላቱል ጀናዛ በአካባቢው ባለ ሙስሊም ማህበረሰብ ላይ የጋራ ግዴታ ነው፡፡ የጋራ ግዴታ የሆነበት ምክኒያት የተወሰኑ ሰዎች ከሰገዱበት ከቀሪዎቹ ሰዎች ይቅር የሚባሉ በመሆኑ ነው፡፡ ይህን ሶላት የሰገደ ሰው የአንድ ተራራ ያህል መጠን ያለው ሽልማት እንዲሚያገኝ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የምስራች ሰጥተዋል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹የቀብር ስነ-ስርአት ላይ ተገኝቶ ከዚያም ሶላቱል ጀናዘ እስከሚሰገድበት ድረስ የቆየ ሰው ከአንድ ቂራት ጋር እኩል የሆነ ምንዳ (ሽልማት) ያገኛል፡፡ እስኪቀበር ድረስ የቆየ ሰው ደግሞ ከሁለት ቂራት ጋር እኩል የሆነ ሽልማት ያገኛል፡፡›› ‹‹ሁለት ቂራት ምንድን ናቸው? ተብለው ተጠየቁ፡፡ እሳቸውም፡ ‹‹ልክ እንደ ሁለት ትልልቅ ተራሮች ያሉ ናቸው ሲሉ መለሱ፡፡›› (ቡኻሪ 1325 ፣ ሙስሊም 945)

የቀብር ስነስርአት ላይ የመገኘት ትሩፋት

የቀብር ስነስርአት ላይ መገኘት እና አስክሬኑን መሸኘት ብዙ ጥቅሞች አሉት፡፡ ከእነዚህም መካከል የሟቹን ሰው መብት በእሱ ላይ መስገድ ፣ ለእሱ ዱአ ማድረግ ፣ የቤተሰቦቹን መብት መጠበቅ ፣ ሟች ዘመዳቸውን ስላጡ እንዲፅናኑ ማድረግ ወ.ዘ.ተ ናቸው፡፡ በቀብር ስነ-ስርአቱ ላይ የተገኘ ብዙ ሽልማቶችን ያገኛል፡፡ የቀብር ስነ-ስርአቱ ላይ በመገኘት ፣ ስነ-ስርአቱን በማየት እና ወደ መቃብሩን በመዘየር ግሳፄን እና ትልቅ ሽልማት ያገኛሉ፡፡

የሶላቱል ጀናዛ አሰጋገድ

1 ሶላቱል ጀናዛ በጀመአ (በህብረት) መስገዱ የተወደደ ነው፡፡ ልክ የጀመአ (የህብረት) ሶላት ላይ እንደሚደረገው ኢማሙ ፊት ለፊት ላይ ይቆማል፡፡

2 የሟቹ ሰው አስክሬን በሚሰገዱት ሰዎች እና በቂብላው መካከል እንዲቀመጥ ይደረጋል፡፡ ኢማሙም በሰውየው ጭንቅላት ትይዩ እና ሴት ከሆነች ደግሞ በወገቧ ትይዩ ይቆማል፡፡ (አቡዳውድ 3194)

3 ሶላቱል ጀናዛ አራት ተክቢራዎች አሉት፡፡፡ እነሱም

-

የመጀመሪያው ተክቢራ

ሰጋጁ እጆቹን እስከ ትከሻው ድረስ ከፍ አድርጎ ያነሳል ወይም እስከታችኛው የጆሮው ክፍል ድረስ ከፍ በማድረግ የመጀመሪያውን ተክቢራ ‹‹አሏሁ አክበር›› ይላል፡፡ ከዚያም የቀኝ እጁን የግራ እጁ ላይ አደራርቦ .ደረቱ ላይ ያስቀምጣል፡፡ የሶላት የመክፈቻ ዱአ ሳያነብ የአሏህን ከለላ በመሻት ስሙን ጠቅሶ እና ድምፁን ዝቅ አድርጎ ሱረቱል ፋቲሃን ያነባል፡፡

ሁለተኛውን ተክቢራ

ከዚያም ሁለተኛውን ተክቢራው ለሁለተኛ ጊዜ ‹‹አሏሁ አክበር›› ይላል፡፡ ከዚያም በኋላ በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ሰለዋት ያደርጋል፡፡ ‹‹አሏህ ሆይ! በነብዩ ሙሐመድ ላይ ሰላም እና በረከትን አድርግ›› በማለት ሰለዋት ያደርጋል፡፡ ሙሉ ቃሉን የሚጠቀም ከሆነ ደግሞ የመጨረሻውን ተሸሁድ ያነባል፡፡ ይህ የተሟላ ነው፡፡ ይህም እንደሚከተለው ነው፡፡ ‹‹አሏህ ሆይ! ሰላምታን በኢብራሂም እና በቤተሰቦቹ ላይ እንዳደረከው ሁሉ፤ ሰላምታን በነብያችን ሙሐመድ እና በቤተሰቦቻቸው ላይ አድርግ፡፡ በእርግጥ አንተ የላቅክ እና የተወደስክ ነህ፡፡ አሏህ ሆይ! ኢብራሂም እና ቤተሰቦቹን እንደባረከው ሁሉ ነብያችን ሙሐመድ እና ቤተሰቦቻቸውን ባርክ፡፡ በእርግጥ አንተ የላቅክ እና የተወደስክ ነህና፡፡››

ሦስተኛውን ተክቢራ

ከዚያም ሶስተኛው ተክቢራ ‹‹አሏሁ አክበር›› ብሎ ለሟቹ ሰው ምህረትን ፣ እዝነትን ፣ ጀነትን እና አሏሀ በጀነት ውስጥ ደረጃውን ከፍ እንዲያደርግለት እንዲሁም ለቀልቡ እና ለምላሱ የገራለትን ዱአ ያደርጋል፡፡ ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የተላለፈ ዱአዎችን ከሸመደደ ያን ማድረጉ በላጭ ነው፡፡

ከዱዓእ ዓይነቶች የሚከተለውን እናገኛለን፡- ‹‹አልሏሁም’መ እግፍርለሁ ወርሐምሁ፣ወዓፍህ ወዕፉ ዐንሁ፣ወአክሪም ኑዙለሁ፤ወወስ’ሲዕ ሙድኸለሁ፤ወግሲልሁ ብልማእ ወሥ’ሠልጅ ወልበረድ፤ወነቅ’ቂህ ምነልኸጣያ ከማ ነቅ’ቀይተ አሥ’ሠውበል አብየደ ምነድ’ደነስ፤ወአብድልሁ ዳረን ኸይረን ምን ዳሪሂ፣ወአህለን ኸይረን ምን አህሊሂ፤ወዘውጀን ኸይረን ምን ዘውጅህ፤ወአድኽልሁ አልጀን’ነተ ወአዕዝሁ ምን ዐዛበል ቀብር ወምን ዐዛብ አን’ናር፡፡›› ትርጉሙ፡- ‹‹አሏህ ሆይ! ምህረትን ለግሰው፡፡ እዘንለት፡፡ ምቾትን ስጠው፡፡ ይቅር በለውም፡፡ መስተንግዶውን መልካም ፣ ቀብሩን ሰፊ አድርግለት፡፡ በውሃ ፣ በውርጭ እና በበረዶ እጠበው፡፡ ነጭ ልብስ ከእድፍ እንደሚፀዳው እሱንም ከወንጀል አፅዳው፡፡ ከነበረበት የበለጠ መኖሪያ ለግሰው፡፡ የተሻለ ቤተሰቦችንም አድርግለት፡፡ ጀነት አስገባው፡፡ ከቀብር እና ከእሳት ቅጣት ጠብቀው፡፡›› (ሙስሊም 963)

አራተኛውን ተክቢራ

አራተኛው ተክቢራ ይልና ትንሽ ለእስትንፋሱ እርጋታ በመስጠት በቀኝ ጎኑ ብቻ ተስሊም (አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱሏህ) ይላል፡፡

የሶላቱል ጀናዛ የመስገጃ ቦታ

ሶላቱል ጀናዛ መስጅድ ውስጥ መስገድ ወይም ደግሞ ለዚሁ አላማ ተብሎ የተመደበ ቦታ ላይ ወይም መካነ መቃብር ውስጥ መስገድ የተፈቀደ ነው፡፡ ይህ ሁሉ ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ተዘግቧል፡፡

አስከሬን መሸከም መሸኘትና መቅበር

ሱናው ለቀብር ስነ-ስርአት ለማዘጋጀት መቻኮል ፣ በሟቹ ሰው ላይ መስገድ ፣ ወደ መቃብር ቦታው መውሰድ እና መቅበር ነው፡፡ አቡ ኹረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡ ‹‹አስክሬኑን (ለመቅበር) አቻኩሉ፡፡ በጎ (መልካም) ከነበረ ደህንነቱ ወደ ተጠበቀበት እያስተላለፋችሁት ነው፡፡ ይህ ካልነበረ ደግሞ ክፉን ነገር ከትከሻችሁ ማውረድ ነውና፡፡›› (ቡኻሪ 1315 ፣ ሙስሊም 944)

ጀናዛውን (አስክሬኑን) የሚከተሉ ሰዎች እሱን በመሸከም ቢሳተፉ እና ቢተጋገዙ የተወደደ ነው፡፡ አስክሬኑን የሚሸኙት ሰዎች ከፊት እና ከኋላ ሁነው መጓዝ ሱና ነው፡፡ መካነ መቃብሩ ሩቅ ከሆነ ወይም አስክሬኑን መሸከም በጣም ከከበደ በመጓጓዧ ጭኖ ይዞ መሄድ ይፈቀዳል፡፡

ሟቹን ሰው ሲቀብሩ ከግምት ውስጥ ማስገባት የሚያስፈልጉ ነገሮች

١
1 ሟቹን ሰው ካጠቡ ፣ ከከፈኑ እና ከሰገዱበት በኋላ ለመቅበር ማቻኮል የተወደደ ነው፡፡
٢
2 መቃብሩ በአውሬ እንዳይቆፈር እና ጎርፍ እንዳይወስደው አርቆ እና አስፍቶ መቆፈር አስፈላጊ ነው፡፡
٣
3 መቃብሩ ለህድ ወይም ሽቅ ሆኖ መቆፈር ይቻላል፡፡ ወይም ደግሞ እንደየ ሐገሩ የመሬት አቀማመጥ እና የአፈሩ ፀባይ ተስማሚነት መማስ ይቻላል፡፡
٤
4 የሟቹን ሰው ፊት ወደ ቂብላ አዙሮ በቀኝ ጎኑ ለህድ ውስጥ ማስተኛት የተወደደ ነው፡፡ [ለሕድ ወደ ታች ከተቆፈረ በኋላ በቅብላ በኩል ለአስከሬኑ ማስገቢያ ወደ ጎን የሚቆፍር ጉድጓድ ነው፡፡]
٥
5 የሚቀብረው ሰው አስክሬኑን ሲያስቀምጥ ‹‹በአሏህ ስም ፣ በአሏህ እና በአሏህ መልዕክተኛ መንገድ›› ማለቱ የተወደደ ነው፡፡ (ትርሚዚ 1046 ፣ ኢብን ማጃ 1550)
١
የአስክሬኑ ማረፊያ ለህድ ወይም ሸቅ ሆኖ ጥልቅ ጉድጓድ ሲሆን መሸፈን ያለበት በጭቃ እና ከጭድ ጋር በተቦካ የሸህላ ጡብ ፣ ወፋፍራም የግንድ ጉማጅ ፣ ድንጋዮች ወይም ሌላ መሰል ነገሮችን በመጠቀም ነው፡፡
٢
እዚያ ያሉ ሰዎች ሟቹን አፈር ማልበሳቸው የተወደደ ነው፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሶስት እፍኝ አፈር መቃብሩ ላይ ያፈሱ ነበር፡፡ (አደርቁጡኒ 1565)
٣
ሰዎች እንዳይቀመጡበት እና እንዳይረማመዱበት ለማድረግ መቃብሩን ሁለት ሳንቲ ሜትር ከፍ ማድረግ የተወደደ ነው፡፡ በዚህ ላይ ግንባታ ማካሄድ የተከለከለ ነው፡፡ ምክኒያቱም ሟቹን ለማላቅ ፣ ከፍ ከፍ ላማድረግ እና በአሏህ ላይ ለማሻረረክ ሰበብ ነውና፡፡

ከተቀበረ በኋላ

የቀብር ስነ-ስርአት ላይ የተገኙ ሰዎች ለሟቹ የአሏህን እዝነት እና ምህረት መለመንናቸው የተወደደ ነው፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡ ‹‹ለወንድማችሁ ምህረትን ለምኑለት፡፡ እንዲረጋጋም ጠይቁለት ፣ አሁን እሱ እየተጠየቀ ነውና አሉ፡፡›› (አቡዳውድ 3221)

ትምህርቱን አጠናቅቀሃል


ፈተና ጀምር