መማርዎን ይቀጥሉ

ሎግ ኢን አላደረክም
መማር ለመጀመር፣ እድገትን ለመከታተል፣ ነጥቦችን ለመሰብሰብ እና ወደ ውድድር ለመግባት አሁኑኑ በታ ፕላትፎርም ይመዝገቡ፡ ከተመዘገቡ በኋላ ለሚማሯቸው ርዕሶች የኤሌክትሮኒክስ ሰርተፍኬት ይደርስዎታል።

የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል

ትምህርት በሞተ ሰው ማዘን እና መፅናናት

በሞተ ሰው ማዘን ፣ መፅናናት እና መቃብሩን ሄዶ ማየት ጋር የተያያዙ አንድ ሙስሊም ሰው ሊከተላቸው የሚገቡ አህካሞች እና ስነ-ስርአቶች አሉ፡፡ በዚህ ትምህርት ውስጥ ስለ ተወሰኑት ትማራላችሁ፡፡

የሟቹን ሰው ቤተሰቦች እና ዘመዶች ማፅናናት እና መቃብሩን ሄዶ ማየት ጋር የተያያዙ አህካሞችን እና ስነ-ስርአቶችን ትማራላችሁ፡፡

ሐዘንተኛን ማጽናናት (ተዕዝያ)

የሟቹን ሰው ቤተሰቦች ማፅናናት የተወደደ ነው፡፡ በመልካም ንግግር ከደረሰባቸው ነገር እንዲበረቱ ማድረግ ፣ ለሟቹ ሰው ዱአ ማድረግ ፣ ቤተሰቦቹን እና ዘመዶቹን ማበረታታት እና እንዲታገሱ ማድረግ የተወደደ ነው፡፡ እንዲሁም ከአሏህ ምንዳ እንዲፈልጉ ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹አሏህ የሚወስደው ማንኛውም ነገር የእሱ ነው፡፡ እሱ የሰጠው ማንኛውም ነገር የእሱ ነው፡ በዚህ አለም ውስጥ ከእሱ የሆነ ማንኛውም ነገር በጊዜ የተገደበ ነው፡፡ እናም ታገሱ፤ የአሏህን ምንዳ (ሽልማት) ተስፋ አድርጉ፡፡ (ቡኻሪ 1284 ፣ ሙስሊም 923)

የሟቹ ቤተሰቦች እና ዘመዶች ከቀብር በፊትም ሆነ በኋላ በማንኛውም ቦታ ማለትም መስጅድ ውስጥ ፣ የመቃብር ቦታ ፣ ቤት ፣ የስራ ቦታ ወ.ዘ.ተ ማፅናናት ይቻላል፡፡

የሃዘን መግለጫ ድንኳን በመትከል ወይም የእራት ግብዣ በማድረግ እና ለእነዚህ አላማ መሰባሰባቸው በጣም መጋነን የለበትም፡፡ ምክኒያቱም የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እና የእነዚያ እንቁ ሶሃቦች ሱና አይደለምና፡፡

ለሟቹ ሰው ማዘን

ማልቀስ ተፈጥሯዊ እዝነት እና የማጣት እና የሐዘን ስሜት መግለጫ ነው፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ልጃቸው ኢብራሂም ሲሞት እንባቸውን አፍሰዋል፡፡ (ቡኻሪ 1303 ፣ ሙስሊም 2315)

በሞተው ሰው ማዘን እና መገለል በተመለከተ እስልምና ህገ ደንቦችን አስቀምጧል

١
1 ከመጠን በላይ እና ድምፅ ከፍ አድርጎ ማልቀስ እንዲሁም ከእስልምና ህግጋት ጋር የሚጣረሱ ድርጊቶችን መፈፀም ለምሳሌ ፀጉርን መላጨት ፣ ደረት መምታት ፣ ፊትን መንጨት ወ.ዘ.ተ እስልምና ከልክሏል፡፡
٢
2 አንዲት ሴት የሞተባት ባሏ ካልሆነ በቀር ከዘመዶቿ አንዱ በመሞቱ ምክኒያትከ3 ቀን በላይ ጌጧን መተው አይፈቀድላትም፡፡
٣
3 የሚስት ሐዘን፡ ባሏ የሞተባት ሴት በመጠበቂያዋ ጊዜ (በኢዳዋ) የተወሰነ ነገሮችን ማክበር እና መጠበቅ አለባት፡፡

ባሏ የሞተባት ሴት የመጠበቂያ ጊዜ

ይህም አራት ወራት ከአስር ቀን ወይም ነፍሰጡር ከሆነች ደግሞ አስክትወልድ ድረስ ነው፡፡

ባሏ የሞተባት ሴት በመጠበቂያ ጊዜዋ ምን ማድረግ አለባት

١
1 ሽቶ መቀባት ፣ ጌጣ ጌጥ መልበስ ፣ ሜካፕ ፣ ሂና መቀባት ሁሉንም አይነት ኮስሞቲክስ መጠቀም የለባትም፡፡
٢
2 ማንኛውም አይነት ቀለም እና ቅርፅ ያላቸውን የተለመዱ ልብሶችን መልበስ ይፈቀድለታል፤ የመዋቢያ እና የማጌጫ አስካልሆነ ድረስ፡፡ ገላዋን ከመታጠብ ፣ ፀጉሯን ከማበጠር አትከከለከልም፡፡ ባስፈለገ ጊዜ ማታ ሳይሆን ቀን ላይ ከቤት ወጥታ መሄድ ትችላለች፡፡ ያለ ጥርጣሬ የማታቃቸውንም ወንዶች ማናገር ትችላለች፡፡

መካነ መቃብርን መጎብኘት በ 3 ይከፈላል

1 የተወደዳ የመቃብሮችን መጎብኘት

ለመገሰጽና ለሙታኑ ዱዓእ ለማድረግ ዓላማ መቃብሮችን መጎብኘት ለወንዶች ሱንና ነው፡፡ ነቢዩﷺ ‹‹መቃብሮችን ከመጎብኘት ከልክያችሁ ነበር፣ኣኽራን (የወዲያኛውን ዓለም) ስለሚያስታውሷችሁ ጎብኟቸው፡›› [በሙስሊም የተዘገበ] ብለዋልና፡፡

በመቃብር ጉብኝት ዱዓዎች

በመቃብር ጉብኝት ጊዜ ከተላለፉት ዱዓዎች መካከል የሚከተሉትን እናገኛለን ፡- ‹‹አስ’ሰላሙ ዐለይኩም ዳረ ቀውምን ሙእምኒን፣ወእን’ና እንሻአል’ሏሁ ብኩም ላሕቁን፡፡›› [በሙስሊም የተዘገበ]ወይም ‹‹አስ’ሰላሙ ዐላ አህል አድ’ዲያር ምነል ሙእምኒነ ወልሙስሊሚን፣ወየርሐሙል’ሏ አልሙስተቅድሚነ ምን’ና ወልሙስተእኸሪን፣ወእን’ና እንሻአል’ሏሁ ብኩም ላሕቁን፡፡›› [በሙስሊም የተዘገበ]..........

ትምህርቱን አጠናቅቀሃል


ፈተና ጀምር