መማርዎን ይቀጥሉ

ሎግ ኢን አላደረክም
መማር ለመጀመር፣ እድገትን ለመከታተል፣ ነጥቦችን ለመሰብሰብ እና ወደ ውድድር ለመግባት አሁኑኑ በታ ፕላትፎርም ይመዝገቡ፡ ከተመዘገቡ በኋላ ለሚማሯቸው ርዕሶች የኤሌክትሮኒክስ ሰርተፍኬት ይደርስዎታል።

የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል

ትምህርት የቅዱስ ቁርአን ትሩፋት (ምንዳ)

የቅዱስ ቁርአን ታላቅነት እና ክብሩን የሚገልፁ ብዙ ትሩፋት አሉት። በዚህ ትምህርት ውስጥ የተወሰኑትን ትማራላችሁ።

የቅዱስ ቁርአን ታላቅነት እና ክብሩን የሚገልፁ የተወሰኑ ትሩፋትን ማወቅ

የቅዱስ ቁርአን ትሩፋት (ምንዳዎች)

ቅዱስ ቁርአን የሚከተሉትን ጨምሮ ብዙ ትሩፋቶች አሉት።

1 ቁርአንን ተምሮ የማስተማር ችሮታ

ኡስማን ቢን አፋን (ሰ.ዐ.ወ) እንዳስተላለፈው የአሏኅ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹ከእናንተ መካከል በላጩ ቁርአንን ተምሮ ያስተማረ ነው።›› (ቡኻሪ 5027)

2 የቁርአን ሰዎች የተመረጡ የአሏህ ሰዎች ናቸው።

አነስ ቢን ማሊክ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹በእርግጥ አሏህ ከሰዎች ቤተሰብ አለው። እነሱም (ሶሃቦቹ)፡ ‹‹የአሏህ መልዕክተኛ ሆይ! እነሱ እነማን ናቸው?›› አሏቸው። እሳቸውም አሉ፡ ‹‹እነሱ የቁርአን ሰዎች፤ የአሏህ ቤተሰቦች የእሱ ምርጦች ናቸው።›› (ኢብን ማጃ 215)

3 አንድን የቁርአን ፊደል ማንበብ ብዙ እጥፍ ትሩፋት ሽልማት ይዟል።

አብዱሏህ ኢብን መስኡድ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹ከአሏህ ኪታብ አንዲትን ፊደል ያነበበ ሰው መልካም ስራ አለው። መልካም ስራውም በአስር እጥፍ ይባዛል። አሊፍ ላም ሚም አንድ ፊደል ነው አልልም። አሊፍ አንድ ፊደል ፣ ላም አንድ ፊደል ሚም አንድ ፊደል ቢሆን እንጅ።›› (ትርሚዚ 2910)

4 ቁርአን ለማንበብ እና ለማጥናት በተሰበሰቡ ሰዎች ላይ የመላኢኮች በዙሪያቸው መሆን ፣ ሰላም እና እዝነት በእነሱ ላይ መሆኑ

አቡ ኹረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹በአሏህ ቤት ውስጥ (መስገድ) የአሏህን መጽሐፍ ለማንበብ እና ለማጥናት የሚሰባሰቡ ሰዎች የሉም፤ ሰላም ፣ መረጋጋት እና እዝነት በእነሱ ላይ የሆነ ፣ መላኢካዎች በዙሪያቸው ያካበቧቸው ፣ አሏህ እሱ ዘንድ ባለው ስብስብ መሃል ያወሳቸው ቢሆን እንጅ።›› (ሙስሊም 2699)

5 ቁርአን ለወዳጁ አማላጅ መሆኑ

አቡ ኡማማ አል-ባሂሊ እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ አለ፡ ‹‹ቁርአንን አንብቡ በትንሳኤው ቀን ለወዳጆቹ አማላጅ ሆኖ ይመጣልና።›› (ሙስሊም 804)

6 ቁርአን ከመላኢኮች ጋር መቅራት የተካነ እና ሲያነብ የሚንተባተብ ሰው ሁለት ምንዳ (ሽልማት) አለው

አኢሻ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈችው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹በቁርአን የተካነ (የሰለጠነ) ሰው ከተከበሩት እና ቀጥ ካሉት ነው። ቁርአን ሲያነብ የሚንተባተብ እና የሚከብደው ሰው ለእሱ ሁለት ምንዳ ሽልማት አለው።›› (ሙስሊም 798)

7 ቁርአን ወዳጆቹን ከፍ ያደርጋል

ኡመር (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹በእርግጥ! በዚህ ቁርአን አሏህ ሰዎችን ከፍ ያደርጋል፤ ከፊሉን ደግሞ ዝቅ ያደፈርጋል።›› (ሙስሊም 817)

8 ቁርአንን የሀፈዘ (የሸመደደ) ሰው ከቁርአን በልቡ የያዘውን ያህል በጀነት ደረጃው ከፍ ይላል

አብዱሏህ ቢን ኡመር ቢን አል-አስ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ "ለቁርአን ወዳጅ እንዲህ ይባላል፡ አንብብ፤ ከፍ በልም። በዱንያ ስታነብ እንደነበረው አንብብ፤ መኖሪያህ በምታነበው የመጨረሻው አንቀፅ ላይ ነውና።" (አቡዳውድ 1464)

9 የቁርአን ባለቤት በቂያማ ቀን የክብር ልብስ እና የክብር አክሊል ይለብሳል

አቡ ኹረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ "በፍርዱ ቀን ቁርአን ይመጣና ‹‹ጌታየ ሆይ! አስውበው›› ይላል። ከዚያም የክብር አክሊል ይደፋለታል። ይለብሳልም። ከዚያም ‹‹ጌታየ ሆይ! ብዙ ስጠው›› ይላል። ከዚያም የክብር ልብስ ይለብሳል። ከዚያም ‹‹ጌታየ ሆይ! ተደሰትበት›› ይላል። በእሱ (በባሪያው) ይደሰትና ‹‹አንብብ፤ ከፍበልም። በእያንዳንዷ አያም ሽልማትህ ይጨምራል›› ይላል።" (ትርሚዚ 2915)

10 ሃያሉ አሏህ በታላቅ የአክብሮት የቁርአን ሰው ወላጆችን ያከብራል

ሰሃል ቢን ሙአዝ ከአባቱ ይዞ እንዳስተላለፈው (ረ.ዐ) የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡ ‹‹ቁርአንን ያነበበ እና በእሱም የሰራበት ሰው በፍርዱ ቀን ለወላጆቹ አክሊል ይደፋላቸዋል (ይለበሳሉ)። ብርሃኑም ከፀሐይ ብርሃን ይበልጣል። በዱንያ ውስጥከላችው የፀሐይ ብርሃን የበለጠ ብርሃንን ይጎናፀፋሉ።›› (አቡዳውድ 1453) እናም በዚህ (ቁርአን) ስለሚሰራበት ሰው ምን ታስባላችሁ?

11 ቁርአን መማር እና መሸምደድ ዱንያ እና ዱንያ በውስጧ ከያዘችው ነገር ሁሉ ይበልጣል

ኡቅባ ቢን አምር(ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ፡ "በሱፋ ውስጥ ሆነን እያለ የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ውድኛ ወጡ። ከዛም እንዲህ አሉ፡ ‹‹ከእናንተ መካከል በየቀኑ ጧት ጧት ወደ ቡሳን እና አል-አቂቅ ሄዶ ሁለት ሴት ግመሎችን ያለ ሃጢያት እና ዝምድናን ሳትቆርጡ ወስዳችሁ ማምጣት የምትፈልጉ ማንኛችሁ ናችሁ? አሉ። እኛም አልን፡ የአሏህ መልዕክተኛ ሆይ! እኛ እንፈልጋለን አልናቸው። እሳቸውም፡ ‹‹ከእናንተ መካከል አንዳችሁ ወደ መስጅድ ሄዶ ከሃያሉ አሏህ መጽሐፍ ለመማር እና ሁለት አንቀፆን ለማንበብ አይሄድም፤ ያ ከሁለት ሴት ግመሎች የሚበልጥ ቢሆን አንጅ። ሶስት አንቀፅ ደግሞ ከሶስት ግመሎች ይበልጣል። አራት አንቀፆ ከአራት ግሞሎች ይበልጣል። እንዲሁ ከግመል እንደ ቁጥራቸው ይበልጣል አሉ።" (ሙስሊም 803)

ትምህርቱን አጠናቅቀሃል


ፈተና ጀምር