የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት የነብዩ ሙሐመድ የህይወት ታሪክ 1
ሙስሊም ሰው ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዝርዝር ታሪኮች ጋር እራሱን ማስተዋወቅ አለበት። ያ ሲሆን በሁሉም የህይወት ጉዳዮች ምሳሌነታቸውን መከተል ይችላል። ምክኒያቱም የህይወት ታሪካቸው ተጨባጭ የእስልምና እና የህግጋቱ ስንቅ ነውና።
የዘር ሐረጋቸው
የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የዘር ሐረግ በላጭ እና የተከበረ የዘር ሐረግ ነው። እሳቸው፡ ሙሐመድ ቢን አብዱሏህ ቢን አብዱል ሙጦሊብ ቢን ሐሽም ቢን አብድ መናፍ ቢን ቁሰይ ቢን ኪላብ ቢን ኪላብ ቢን ሙራ ቢን ካአበድ ቢን ሉዋይ ቢን ጋሊብ ቢን ፋህር ቢን ማሊክ ቢን አል-ነድር ቢን ኪናን ቢን ሁዘይማህ ቢን መድረቃ ቢን ኢልያስ ቢን ሙዳር ቢን ኒዛር ቢን ማአድ ቢን አድናን ናቸው። አድናን ደግሞ የተወለደው ከኢስማኢል (ዐ.ሰ) ነው።
2 ወላጆቻቸው
አባታቸው አብዱሏህ ቢን አብዱል ሙጦሊብ ቢን ሐሽም ሲሆን የሞተው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በእናታቸው ማህፀን ውስጥ ሆነው እያለ ነው። እናታቸው አሚና ቢነት ወሃብ ቢን አብደ መናፍ ቢን ዘህራ ይባላሉ።
3 ውልደታቸው
የተወለዱት ሰኞ ቀን በረቢኡል አወል ወር ሲሆን በተለምዶ ‹‹አመል ፊል›› የዝሆን አመት ተብሎ በሚጠራው አመት ነው። ይህም ወደ 571ዓ ይጠጋል።
4 ጡት የጠቡት
ለቀናት ያህል ጡት ያጠባቻቸው የአቡ ላሃብ ባሪያ የሆነችው ሱወይባ ናት። ከዚያም ወደ በኒ ሰአድ ሄደው ከሐሊማ አሰአዲ ጠቡ፤ ለአራት አመት ያህል በበኒ ሰአዲ ውስጥ ከእሷ ጋር ሁነው አደጉ። ልባቸው ተከፍቶ የነፍሳቸው እድል እና ሸይጧን ከእሷ የወጣው እዚያው በኒ ሰአዲ ውስጥ እያሉ ነው። ከዚያም በኋላ ሐሊማ ወደ እናታቸው መለሰቻቸው።
5 አስተዳደጋቸው እና ወጣትነታቸው
ነብይ ሆነው ከመላካቸው በፊት የሰሯቸው ስራ
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ነብይ ሁነው ከመላካቸው በፊት የነበራቸው ህይወት ውስጥ ስህተት ወይም መዘንበል የሌለበት ፣ መልካም እና የተባረከ ህይወት ነበራቸው። የአሏህ መልዕክተኛ ያደጉት በሃያሉ አሏህ እንክብካቤ ነው። አሏህ ከድንቁርና እድፍ ጠብቋቸዋልም። በህዝባቸው ዘንድ ‹‹ታማኝ እና እውነተኛ›› ተብለው እስኪታወቁ ድረስ ጎረቤታቸውን አክባሪ ፣ ታጋሽ ፣ በንግግራቸው እውነተኛ ፣ አደራን ጠባቂ እና ከመጥፎ ባህሪ ሁሉ የራቁ ነበሩ።
6 የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሚስቶች
ኸድጃ (ረ.ዐ) ባገቡ ጊዜና ከመይሰራ ጋር ወደ ሻም ለንግድ ሲሄዱ ሃያ አምስት አመታቸው ነበር። መይሰራ ስብዕናቸው ፣ ታማኝነታቸው እና አደራ ጠባቂነታቸው አስደነቀው። ከጉዟቸው በተመለሱ ጊዜ ያየውን ነገር ሁሉ ነገራት። በዚህም ምክኒያት እንዲያገቧት ፈለገች። ከቁረይሽ ባለባቶች እና ከበርቴዎች ለገብች ስትጠየቅ ኖራ እንቢ ብላየቆየች ቢሆንም በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ፍቅር ተነደፈች። የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ያገቧት የመጀመሪያዋ ሴት እሷ ናት። እስከሞተችበት ጊዜ ድረስ አላገቡም። ከልጃቸው ኢብራሂም በቀር የልጆቻቸው ሁሉ እናት እሷ ናት። ኸድጃ የሞተችው ወደ መዲና ከመሰደዳቸው ከሶስት አመት በፊት ቀደም ብሎ ነው።
የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሚስቶች ስም
የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ልጆች
የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ልጆች ሰባት ናቸው። ሶስት ወንዶች እና አራት ሴት ልጆች ነበራቸው።
እነሱም፡- በቅፅል ስማቸው የሚጠራው እና ጥቂት ጊዜ ብቻ በህይወት የቆየው አለ-ቃሲም ፣ አጧሂር ተብሎ የሚጠራው አብዱሏህ ወይም አጦይብ እና ኢብራሂም ናቸው።
አራት ሴት ልጆች ነበሯቸው። እነሱም፡- ከሁሉም ትልቋ ዘይነብ ፣ ሩቅያ ፣ ኡሙ ኩልሱም እና ፋጢማ ናቸው። ከልጃቸው ኢብራሂም በቀር የነብዩ ወንድ እና ሴት ልጆች ሁሉም ከምዕመናን እናት ከሆነችው ከሚስታቸው ኸድጃ (ረ.ዐ) የተወለዱ ናቸው። ልጃቸው ኢብራሂም የተወለደው ከእቁባታቸው ማሪያ አል-ቂብጢያ ነው።