የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት carraaqaafii rizqii barbaaddachuu.
የገንዘብ ጠቀሜታ
አንድ ሰው መሰረታዊ ፍላጎቶቹን ለማሟላት ገንዘብ ያስፈልገዋል። እነዚህ መሰረታዊ ፍላጎቶች ምግብ ፣ መጠጥ ፣ መጠለያ ቤት ፣ ልብስ ወ.ዘ.ተ ናቸው። ህይወትን ለማሻሻል ለሚረዳቸው አገልግሎት ክፍያ ለመክፈል ይጠቅማል። እስልምና ለገንዘብ ትልቅ ቦታ ሰጥቷል። ከገቢ እና ከወጭ ጋር የተያያዙ በርካታ የህግ ድንጋጌዎችንም አውጥቷል።
ገቢ ማግኘት እና መተዳደሪያ ገንዘብ መፈለግ ማለት ገንዘብ ለማግኘት እና ለህይወት አስፈላጊ የሆነውን ለማሟላት እና የሰው ልጆች የሚወስዷቸው ማንኛውም እርምጃዎች እና ስራዎች ማለትም ንግድ ፣ ኢንዱስትሪ ፣ ግብርና ወይም ሌላ የሥራ ዘርፎች ናቸው።
ገቢ ማግኘት እና መተዳደሪያ ገንዘብ የመፈለግ ሁክም (ሸሪአዊ ውሳኔ)
ገቢ የማግኘት አላማው ለታይታ (ለዩዩልኝ ፣ ለይስሙልኝ) እና ለመኩራራት ከሆነ የተጠላ ነው። እንደ አንዳንድ ፉቅሃዎች (የፊቅህ ሊቃውንት) ደግሞ የተከለከለ ነው።
ገቢ ለማግኘት የሚፈልግ አንድ ሙስሊም ሰው ከገንዘብ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ማወቅ እና የገንዘብ ግብይት ህግጋትን መማር አለበት። ለምሳሌ የመሸጥ ፣ የማከራየት ፣ የማጫረት ፣ የአራጣ እና ሌሎች እሱ የሚሳተፍባቸው ግብይቶች ጋር የተያያዙ ሁክሞችን ማወቅ አለበት። ምክኒያቱም መተዳደሪያ ገንዘብ በመፈለግ አሏህ ከከለከለው ነገር ላይ እንዳይወድቅ ይረዳዋልና።
ገቢ የማግኘት እና መተዳደሪያ ገንዘብ የመፈለግ ስነ-ምግባር
1 መተዳደሪያ ገንዘብ በመፈለግ ውስጥ ግዴታ ከሆኑ ስነ-ምግባሮች መካከል፡ ሃያሉ አሏህ ግዴታ ያደረጋቸውን ነገሮች አለማዘግየት ወይም መተው ናቸው። ምክኒያቱም እነዚህ ግዴታዎች ሙስሊም ሰው ጊዜውን እና ጥረቱን የሚያደርግባቸው መሰረቶች መሆን አለባቸውና።
2 መተዳደሪያ ገንዘብ በመፈለግ ዙሪያ ግዴታ የሆነው ሌላኛው ስነ-ምግባር ወደ ጉዳት የሚያመራ እና ሌሎች ላይ ጉዳት የማያደርስ መሆን አለበት የሚለው ነው።
3 ግለሰቡ ገቢ ለማግኘት ጥሩ አላማ ወይም ሃሳብ ያለው መሆን አለበት። ለምሳሌ ለእሱ መጠቃቀሚያ እና በእሱ ላይ ሃላፊነት ያለበት ወጭያቸውን መሸፈን እና ከሰዎች እጅ ያለውን ከመመኘት ለመራቅ እና ገንዘቡን ተጠቅሞ የአምልኮ ተግባራትን ለሚያከናውንበት ከሆነ ነው። ሃሳቡ ወይም አላማው ሃብት ማከማቸት ፣ መኩራራት እና መንጠባረር እና ለሌላ መጥፎ ምግባሮች መሆን የለበትም።
አንድ ሙስሊም ሰው መተዳደሪያ ገንዘብን በመፈለግ ላይ ቅን ከሆነ እና ገቢ የመፈለግ አላማው ለሰዎች ምፅዋት ለመስጠት እና ህይወታቸውን ለማሻሻል ከሆነ ይህ ተግባሩ እንደ አንድ የአምልኮ ተግባር ይቆጠራል። በዚህም ከፍ ያለ ደረጃን ያገኛል። የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹ከሰዎች አሏህ ዘንድ ይበልጥ ተወዳጁ ለሰዎች ጠቃሚ የሆነው ነው።›› (አል-አውሳት በጦበራኒ 6026)
4 መተዳደሪያ ገቢን በመፈለግ እና በቀሪ የሰው ልጅ ፍላጎት መካከል ልከኛ (መጠነኛ) እና ሚዛናዊ መሆን ያስፈልጋል። ምክኒያቱም ገቢ ማግኘት መንገዱ እንጅ በራሱ ፍፃሜ ወይም ግብ አይደለምና። ሰልማን ለአቡደርዳ (ረ.ዐ) እንዲህ አለው፡ ‹‹ጌታህ በአንተ ላይ መብት አለው ፣ ነፍስህ በአንተ ላይ መብት አላት። እናም ቤተሰብህ በአንተ ላይ መብት አላቸው። ሆኖም በአንተ ላይ መብት ላላቸው ሁሉ የሚገባቸውን መብት ስጥ።›› አቡደርዳ ይህን ንግግር ለነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ነገራቸው። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ‹‹ሰልማን እውነቱን ነው›› አሉ። የቡኻሪ ዘገባ 1968
5 ሲሳይ (ሪዝቅ) ሲፈልጉ በአሏህ ላይ መመካት ያስፈልጋል። ትክክለኛው በአሏህ ላይ የመመካት መገለጫ አንድ ሰው በልቡ ወደ አሏህ ባስጠጋው ነገር የተፈቀደ ወይም ህጋዊ መንገድን መከተሉ ነው።
6 አንድ ሰው ሲሳይ ወይም ሪዝቅ ከሃያሉ አሏህ እንደሆነ እርግጠኛ ነው። ሲሳይ ያለው ከራሱ ከገቢው አይደለም። ሆኖም ሪዝቁን (ሲሳዩን) ለማግኘት የተሸለውን መንገድ መምረጥ አለበት፤ አሏህ በሚያውቀው ጥበብ እንጅ ከስቡ ወደ እሱ አይመጣም።
7 አሏህ በሰጣችሁ ነገር ተደሰቱ። ሪዝቃችሁ በዘገየ ጊዜ ትዕግስት አትጡ፤ የሚመጣበት ጊዜ እና መጠኑ የሚወሰነው በአሏህ ነውና። ሙስሊም ሰው ሪዝቁን መጠቃቀሚያውን የሚፈልገው አሏህ በወሰነለት ነገር ፣ የተፈቀደ ነገር በመፈለግ እና የከለከለውን በመራቅ በትህትና ፣ በፀና እምነት እና በደስታ ነው። የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) "ሰዎች ሆይ! አሏህን ፍሩ፤ መተዳደሪያ (ገንዘብ) በመፈለግ ላይ መካከለኛ ሁኑ። ሁሉም ነፍስ አትሞትም ቢዘገይም አንኳ ሁሉንም ሪዝቋን እስክትቀበል ድረስ። ሆኖም አሏህን ፍሩ፤ ስንቅን (ሪዝቅን) በመፈለግም መካከለኛ ሁኑ። የተፈቀደውን ያዙ፤ የከለከሉትንም ተው።" (ኢብን ማጃ 2144)